Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ስለማያዋጣ ለማይሳካ ነገር አታድክሙን! - የኦህዴድ መልስ ለየአማራ ብልፅግና 'የታሪክ ምርኮኞች ቁማርተኞች' ገለ መሌ ዝባዝንኬ

Post by sarcasm » 21 Feb 2023, 09:04

የአማራ ብልፅግና እንደ ኦህዴድ!!
ይሳካለታል ? አይሳካለትም!!

By Dereje Gerefa Tullu


ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ኦህደድ
መንግስት ሆኖ
መንግስት ላይ በማመፅ
መንግስትን ጥሎ
መንግስት ሆኗል።

አሁንም የአማራ ብልፅግና ውስጥ ያሉ አንዳንድ( አንዳንድ የሚለው ይሰመርበት።በድጋሚም ይናበብ።) ወገኖችም ያንኑ መንገድ ተከትለው መንግስት ሆነው
መንግስትን ጥለው
መንግስት ለመሆን
አንዳንዴ በገደምዳሜ ሌላ ጊዜ ደግሞ በግልፅ ሙከራ እያደረጉ ነው።
ብዙ ማሳያዎች አሉ። ከዚህ መካከል የሰሞኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወህዶ አመፅ እና የአማራ ክልል አቀራረብ አንዱ ነው። የትላንትናው መግለጫ ደግሞ ተጨማሪ ነው።

ኦህደድ መንግስት ሆኖ መንግስትን ገልብጦ መንግስት እንዲሆን ያስቻሉት በቂ አስቻይ ሁኖታዎች አሉት።

ምንድናቸው ?

1 የክልሉ አቀማመጥ ከዋና ከተማዋ አንፃር አንዱ ነው። ኦሆዲድ ውስጥ ያለው አመፀኛ ቡድን መጀመሪያ አመፅ ቀስቅሶ የኦህዲድን ስልጣን በመቆጣጠር የክልሉንም ስልጣን ተቆጣጥሯል።
ኦህዲድ ይህንን ማድረግ ካስቻሉት ነገሮች መካከል ኦሮሚያ ውስጥ አመፅ መቀስቀሱ አይደለም። አንድ ክልል ውስጥ የሚቀሰቀሰው አመፅ በአመዛኙ ሊያደርግ የሚችለው የክልሉን እና የህዝቡን ኢኮኖሚ ማዳከም ነው። ይህ ደግሞ ውሎ አድሮ መጀመሪያ ህዝቡ እራሱ የክልሉን አመራር ምንም ሳይለይ ይበላዋል።ምክንያቱም አማፅው አካል የክልሉን ስልጣን እንኳን ቢቆጣጠር አጠቃላይ ተፅዕኖ ሳያሳድር አሁንም ህዝቡ ይነሳሳበታል።
የኦህዲድ ግን የተለየ ነበር። ኦህዲድ በአብዛኛው የአመፅ ስልቱ ሊሰራለት የቻለው አመፁን ወደ መናገሻ ከተማዋ በመሳብ በለስልጣኑን እና የባለስልጣናቱ ቅርብ የሆኑትን ቅንጡ ባለሃብቶች መግቢያ እና መውጫ መከልከል መቻሉ ነው።ኦህዲድ አመፁን ወደ መሃል ስቦ በማምጣት በዙሪያው ያሉትን የባለስልጣናቱን እና የአጋሮቹን ሃብት አደጋ ውስጥ መክተቱ ነው አመፁን ውጤታማ ያደረገው።ኦህዲድ አመፁን ወደ መዕከል ስቦ በማምጣት የሀገሪቷ 60% ሃብት የሚንቀሳቀስባት ቀጠና ውጥረት ውስጥ መጣሉ ነው መንግስት ሆኖ መንግስት ላይ እንዲነሳ ያስቻለው። በወቅቱ እነዚህን 60% ኢኮኖሚ የሚያንቀሳቅሱት ኦህዲዶች እና አጋሮቻቸው ሳይሆኑ በዋነነት ህወሃት እና በመጠኑም ቤአዴን ስለነበሩ በኦህዲድ የሚለኮሰው እስት በአብዛኛው የሚለበልበው ህዋሃትን እና አጋሮቹን ነበር።ኦህዲድ እዚህ አከባቢ በህዋሃት እና በተወሰና ደረጃ በቤአድን ባለስልጣናት እና አጋሮቻቸው በህገ ወጥ መልኩ ተይዘው የነበሩትን የተፈጥሮ ይዞታዎች መልሶ ለወጣቱ በማከፋፈል ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ለአመፀኛው ተስፋ መስጠት ችሏል።
አሁን የአማራ ብልፅግና ልክ ያኔ ኦህዲድ ኦሮሚያ ውስጥ እንዳደረገው አመፅ አማራ ክልል ቢቀሰቅስ በመጀመሪያ ወላፈኑ የሚለበልበው የክልሉን ባለስልጣናት እና አጋሮቹን ነው።ሙቀቱ የኦሮሚያ ብልፅግና ወይም ጠቅላዩ ጋር ለመድረስ መጀመሪያ የአማራ ብልፅግና ነዶ አልቆ አመድ መሆን አለበት።
አማራ ክልል ሃብት ያለው የኦሮሚያ ብልፅግና ወይም አጋር አለ ?
ያለ አይመስላኝም።
ስለዚህ አማራ ክልል ብልፅግና መራሽ አመፅ ማንን ይጠቅማል ?
ቢያንስ የአማራ ብልፅግናን አይጠቅምም።
በዚሁ አጋጣሚ አንድ ከምርጫው በፊት ሆኗል የሚባለውን ላካፍላችሁ ። የአማራ ብልፅግና በውሃ ቀጠነ ምክንያት የሚሄድበትን ምንጣፍ አንጥፉልኝ እያለ ጠቅላዩን ያስቸግራል አሉ። ጠቅላዩ አባበሉ ። አሁንም ደጋግመው አባበሉ። ያው አባብለው የሚመጣባቸው ነገር ሊመጣባቸው እሩብ ጉዳይ ላይ የአማራ ብልፅግናን ጠርተው ለራሳችሁ ብላችሁ ብትሰሩ ይሻላል።
እኛ ከኦሮሚያ በባሌም ሆነ በቦሌ 80% ድምፅ ይዘን እንመጣለን። ሱማሌ እና ሲዳማ ከዚህም ከፍ ያለ ያመጣሉ፣ ሎሎችም ተመሳሳይ ነው። መንግስት ለመሆን እሄ ከበቂ በላይ ነው።
ከዚያ በኃላ ከአማራ ክልል ትልቁን ድምፅ ይዞ ከሚመጣው ጋር እንሰራለን። አብን ትልቅ ድምፅ ይዞ ከመጣ ከአብን ጋር እንሰራለን። ሌላም ፖርቲ ትልቅ ድምፅ ይዞ ከመጣ በተመሳሳይ መልኩ አብረን እንሰራለን። እንዲሁም የናንተን ያህል አያስቸግሩንም። ስለዚህ ለራሳችሁ ብላችሁ ብትሰሩ ጥሩ ነው። ይህንን እምለው ብዙ በጎ እና ፈተናዎችን አብረን አሳልፈናል። በግልፅ ሳንነጋገር እንዳንተላለፍ ነው አሉ ይባላል። አሉ ነው እንግዲህ ። ባይሉም ነጥቡ ይሰራል።
ወደ ተነሳንበት ነጥብ ስንመለስ በአጠቃላይ ኦህዲድ ከስድስት ዓመት በፊት የክልሉን ስልጣን ከተቆጣጠረ በኃላ ምን አደረገ ?
የህወሃት ባለስልጣናትን ኦሮሚያ ውስጥ ሲገቡ እና ሲወጡ መኪናቸውን አስቆሞ በመፈተሽ ፣ ኮንትሮባንዱን መቆጣጠር አጣጡፎ ቀጠለ።
አሁን የአማራ ብልፅግና ውስጥ ያለው ኦህዲድን መሆን የሚመኝ አካል ኦህዴድ ያደረገውን ማድረግ ይችላል?
ይህ አስቻይ ሁኔታ አለው ?
የለውም።

2 የአማራ ብልፅግና ውስጥ ኦህዲድን መሆን የሚመኘው በድን ኦህዲድን ለመሆን ባለፉት አምስት ዓመት ያልፈነቀለው ድንጋይ ፤ያልቧጠጠው ሸንተረር የለም። ውጤቱ ግን በእጁ ላይ እየበረቀበት ነው። አማራ ክልል ላይ ስልጣን ለመቆጣጠር መሪዎችን ገሏል። በክልሉ ተከታታይ አመፅ ቀስቅሶ ሞክሯል። የተለያዩ ክልሎች ላይ የይጋባኛል ጥያቄ አንስቷል። አመፀኞችን አንዴ በአይሮፕላን ሌላ ጊዜ በአውቶብስ ጭኖ አአ ለማመጣት ጥረት አድርጓል ። ሁሉም በራስ ላይ ጎል ማስገባት ሆኖበታል።
ውጤቱም እራሱ ላይ ባስገባው ጎል ነጥብ መጣል ነው።
ስለዚህ እንደገና ሌላ እየሞከረ ነው። አመፁን ከብሄር ወደ ሃይማኖት መውሰድ ።አመፃን ከአባይ ማዶ ወደ ሸገር በሰማይ ቤት ማሸጋገር ሌላው ስልት አርጎ መርጧል።
እዚህም ላይ እሄ ኦህዲድን መሆን የሚመኘው ቡድን አንድ የሳተው ነገር አለ።
ኦህዲድ ኦሮሚያ ውስጥ የክልሉን ስልጣን ከተቆጣጠረ በኃላም ሆነ ከዚያ በፊት ኦሮሚያ ውስጥ በፈለገው ሰዓት አመፅ መቀስቀስ ቢችልም አአ ላይ አመፅ አልተቀሰቀሰም። ደቡብም ሆነ ሌሎች ክልሎች አመፅ መቀስቀስ አልተቻለም። ምክንያቱም በወቅቱ እነዚህ ክልል ውስጥ ያሉት ህዝቦች በህወሃት መራሹ ኢህአዴግ በተለየ መልኩ ደስተኞች ስለሆኑ አይደለም።ምናልባትም ከሌላው በላይ የተከፉ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን በነዚህ አከባቢ ያለው መዋቅር በህዋት ጥላ ስር ስለነበረ ነው ። በወቅቱ ሸገር ላይ አመፅ ሳይነሳ አማራ ክልል አመፅ የተነሳው የሸገር መዋቅር በአመዛኙ የተቀላቀለ መሆኑ እና በህወሃት የመጠርነፍ እድሉ ሰፊ ስለነበረ ነው። በአጭሩ ኦህዲድን ለመሆን እየተመኛ ያለው የአማራ ብፅግና ቡድን ሸገር እና ሌሎች አከባቢዎች ላይ ኦህዲድ ኦሮሚያ ላይ ወይም ቤአዴን አማራ ክልል ባደረገው መልኩ አመፅ ለመቀስቀስ የአከባቢውን መዋቅር መቆጣጠር የግድ ነው። ያ ሳይሆን ኦህዴድ ያደረገውን ለመድገም መሞከር አያዋጣም። የሚያዋጣው ሌላ ማንገድ ነው።ምንድነው? እኔ እንጃ ! እሄ ግን አያዋጣም።

3 የኃይልማሪያም ሌጋሲ ፣ የኦህዲድ አመፅ ውጤታመነት ተነስቶ የአቶ ኃይለማሪያም ድርሻን መዘንጋት በፍፁም fair አይሆንም። ህዋሃቶች አመፅ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉትን አንዳንድ ቁልፍ የኦህዲድ ሰዎች አስረን እና ገድለን አመፁን እናኮላሽ ስሉት ስንቴ አክሽቦቸዋል።ምክንያቱ ብዙ ነው። አንዱ ምክንያት የተከበሩት በወቅቱ የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚንስትር በህዋሃት ሰዎች ላይ ከፊተኛ ቁጣ እና ንዴት ነበረባቸው። ባህርያቸውም አስተዋፅኦ አድርጓል።
የሆነው ሆኖ ዛሬ አንዳንዶቻችን በስልጣን ሌሎቻችን በህይዎት ለመኖር የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር ኃይለማሪያም ድርሻ ጉልህ ነው።
አሁን ይህ እድል አለ? በፍፁም የለም። ጠቅላይ ሚንትስር አቢይ በማን ላይ ተናዶ ነው አመፅን በራሱ ላይ የሚፈቅደው? ባህሪያቸውስ ?
እንደ ኃይለማሪያም ነው? እሱን እናንተው መልሱ።


4 የአማራ ብልፅግና ኦህዲድ አይደለም። ኦህዲድ እራሱን የቻለ ፣የራሱ ሊቀማንበር ፣ ስራ አስፈፃሚ ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና ጠቅላላ ጉባዔ ያለው ድርጅት ነው። ካልፈራ በፈለገው ጊዜ ተሰብስቦ ሊቀማንበሩን መቀየር ይችላል። የፈለገውን ውሳኔ መወሰን ይችላል።

የአማራ ብልፅግና ግን የብልፅግና ቅርንጫፍ ነው። ሊቃንበር የለውም። ስራ አስፈፃሚ የለውም። ማዕከላዊ ኮሚቴም ሆነ ጠቅላላ ጉባዔ የለውም።
ብልፅግና አንድ ሊቀማንበር፣ አንድ ጠቅላላ ጉባዔ ፣ አንድ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና ስራ አስፈፃሚ ያለው ድርጅት ነው። የአማራ ብልፅግና ቅርንጫፍ ከዋናው ብልፅግና እውቅና ውጪ እንደ ኦህዲድ በራሱ ተስብስቦ ሊቀማንበር ሊመርጥ አይችልም። ከተከበሩ አደም ፋራህ እውቅና ውጪ ተሰብስቦ ቁልፍ ውሳኔ ለመወሰን አይችልም። እሄንን እኔ ሳልሆን ቤአዴን አዋክቦት የመሰረተው ብልፅግና ህገ ደንብ የሚለው ነው።

ስለዚህ የአማራ ብልፅግና ውስጥ ኦህዲድን መሆን የሚመኘው አካል መሆን እንደማይችል የወዳጅናት ምክሬን ለመለገስ ነው። ምክንያቴ ለማይሳካ ነገር አታድክሙን ነው።

5 የአመፅ ሳይንስ አይደግፋችሁም!

የአመፅ ሳይንስ እንዲህ ይናበባል። አንድ አመፅ ሲደገም የመጀመሪያውን ያህል ውጤት አያመጣም። ምክንያቱም ሁሉም ይለምደዋል። ስልጣን ላይ ያለው አካል አካሄዱን ስለሚያውቀው በጊዜ ይቀጨዋል።
ስለዚህ መላው ምንድነው ? እኔ እንጃ!!
ግን እሄ ስለማያዋጣ አታድክሙን!
Please wait, video is loading...
https://www.facebook.com/derejegerefa.t ... H8jWLDQTXl

Abere
Senior Member
Posts: 15441
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ስለማያዋጣ ለማይሳካ ነገር አታድክሙን! - የኦህዴድ መልስ ለየአማራ ብልፅግና 'የታሪክ ምርኮኞች ቁማርተኞች' ገለ መሌ ዝባዝንኬ

Post by Abere » 21 Feb 2023, 11:54

ምነው ጩኸት አበዛ ? ፈሳም ደረጀ ገረፉ እርሱ እንደሚለው በብልጽግና ትብትቦሽ የአማራ ህዝብ ትግል ይገታል መስሎት ከሆነ አፍንጫውን ይላስ። እንደ እሳተ ገሞራ ፈንዶታ በእፍጢም የሚጥል ሃይል ይፈጠራል - ወደ ላይ ወደታች ምክንያት ቢበዛ የኦነግ ትቢይ የወገዳል። ይኸ ሁሉ የጭንቀት ምክንያት ነው። እንኳን መምራት ሳይችሉ መርተውም በስልጣን መቆየት አስቸጋሪ ነው። ክህዝብ ሽንት ቤት በላይ የከረፋ ሸታታ የኦነግ ድርጅት በሚልዮኖች ላይ ሲከረፋ ሊኖር አይችልም።

Post Reply