
- የሳዌሪስ ፋሚሊ በግብጽ ኣሉ ከሚባሉ የቢዝነስ ቤተ-ሰቦች ይቆጠራል ። ኣባታቸው ከመሰረተው መንገድ ተከትለው የሳዌሪስ ወንድሞች - ነጂብና ኣነስ - በተለያዩ መስኮችና ኣገሮች ኢንቨስት ኢያደረጉ ለራሳቸው ሃብት ለሌሎች ደሞ የስራ እድል ይፈጥራሉ ።
ከባባ ሽኑዳ ልዩ ግንኙነት የነበረው መሃንድስ ነጂብ ሳዌሪስ በስዊዘርላንድ በሚማርበት በነበረው ጊዜ ኣባቱ ራስህን የመቻል ልምድ እንድትገነባ ሰርተህ የፖኬት ማኒህን ጉዳይ ፍታ ስላለው እየተማረ በኣንድ ሆቴል ይሰራ ነበር ። ወደ ግብጽ ከተመለሰ በጓላ ባጠራቀመው ገንዘብ የራሱ የቢዝነስ ፕላን ኣውጥቶ ባሁን ያለበትን ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስ ቻለ ። ኣንድ ጊዜ በቲቪ ኣሁን ብኪስህ ስንት ገንዘበ ኣለህ ተብሎ ሲጠየቅ ያለውን በጠረጴዛ ኣውጥቶ " በቅርብ ከሚያስፈልገኝ በላይ ኣልይዝም ። ሃብትም ቢኖርህም ከሚያስፈልገህና ከኣቅምህ በላይ ለመብላትና ለመጠጥ ኣትችልም ። ለኔ ቢዝነስ ከጊዜ ከሃብት የማከማቸት ፍላጎት ኣልፎ ወደ የያዝከውን እንዴት ታሳካለህ የሚለውን ትጋትና መጣጣር ተቀይረዋል ። / በቂ ገንዘብ ካለህ መልሶ የሚገፋህ የ ኣቺቭመንት ጉዳይ ይሆናል ማለቱ ነው ። /
ለምን የሳዌሪስ ፋሚሊን ኣሁን ኣነሳህ ለሚለውን ጥያቄ መልሱ ቀላል ነው ፥ የቤተ-ክርስትያኑ ኣገልጋይ ኣባታችን ሳዌሪስ ስም ።
-