Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7392
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ጎሰ ወይም ጎሳ እና ዘር

Post by Naga Tuma » 17 Feb 2023, 18:18

ጎሰ ወይም ጎሳ ምን ማለት ነዉ?

ዘር ማለት ምን ማለት ነዉ? በእንግሊዘኛ ሲድ የሚባለዉ አይዴለም? ከሆነ ዘረኝነት ወደ እንግሊዘኛ ሲተረጎም ምን ይሆናል?

ጎሰ/ጎሳ እና ዘር ልዩነት የላቸዉም?

ኣርሶ ኣደር የነበረ ልጅ ስለሆንኩ ባህላዊ እርሻን በደንብ ኣዉቃለሁ። ያልነካሁት ባህላዊ የእርሻ ቁሳቁስ ያለ ኣይመስለኝም።

በርካታ የእህል አይነቶችን ከፍሬ እስከ እሸት እና መልሶ ፍሬ ኣዉቃለሁ።

ጎሰ ምዻኒ ወይም የእህል ጎሳ አይነቶች ጎሰ/ጎሳ ምን እንደሆነ በግልጽ ያሳያሉ። ብያንስ ሁለት የስንዴ ጎሳዎች፣ ሁለት የሰነፍ ቆሎ ጎሳዎች፣ ሁለት የጤፍ ጎሳዎችን መጥቀስ ይቻላል።

ዘር ፍሬ ነዉ። የስንዴ ዘር ቢዘራ የስንዴ ፍሬን ያፈራል። የገብስም ቢሂን እንደዛዉ። እነዚህ ምሳሌዎች ናቸዉ።

የሰዉ ዘር ቢዘራ ሰዉ ይፈጠራል። ለምሳሌ ያህል ነዉ።

ሰዉ እንዴት ይገለጻል? በጅምላ ሲገለጽ ፋናዎች ያሉት ሁለት እግሮች ያሉት፣ እያንዳንዱ እግር ላይ አምስት ጣቶች ያሉት፣ በእግሮቹ ቆሞ መራመድ የሚችል፣ ሁለት እጆች ያሉት፣ እያንዳንዱ እጅ ላይ አምስት ጣቶች ያሉት፣ መናገር የሚችል አፍ ያላዉ፣ እዛ አፍ ዉስጥ ኣንድ ምላስ እና ሲጎለምስ ሰላሳ ሁለት ጥርሶች ያሉት፣ ሁለት ቀዳዳዎች ያለዉ አፍንጫ ያለዉ፣ የምያዩ ሁለት አይኖች ያሉት፣ የሚሰሙ ሁለት ጆሮዎች ያሉት፣ ወዘረርፈ።

ኣዎ ይህን ሁሉ መደርደር እና ማንበቡ ይሰለቻል። ጎሳን እና ዘርን ኣለመለየትም ይሰለቻል።

ስለጎሳ እና ዘር ልዩነት እኔ የኣርሶ ኣደር የነበረ ልጅን እንደሚገባዉ ግልጽ ኣድርጎ ጽፎ ያስነበበዉ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ ነዉ። ዶክተር ገመቹ መገርሳም ነመ ጄዹ የሚል መልስ በድንገት ተናግሮ ነበር። ነመ ጄዹ ማለት ሰዉ ይላሉ ማለት ነዉ።

እንደነዚህ በጣም ቀላል የሚመስሉ ጽንሰሀሳቦችን በትክክል ማወቅ እና መጠቀም ኣያስፈልግም?

ኣንድ ኣብሬዉ ከሰራሁ የእንግሊዝ ሃገር ዜጋ ያስተዋልኩኝ እንደዚህ ቀላል የሚመስሉ ጽንሰሀሳቦችን ኣበጥሮ ማስቀመጥ ነዉ። ከእኔ ካልመጣ ከማለት እና እንደዚህ አይነት ማበጠርን ለግል ፋይዳ ከመሻት በተረፈ የሚከበር ሙያ ነዉ።

ታድያ ኣብዛኛዉ የሃገራችን ህዝብ በእህሎች ጎሳዎች እና ዘሮች ከሚተዳደርበት ወጥተን እንዴት ነዉ ጎሰ ወይም ጎሳን እና ዘርን ኣበጥረን የማንለየዉ፣ እንደ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ?