እንደ ሚታወቀው አቢይ አቢይ አህመድ በእናቱ ኦርቶዶክስ አማራ በአባቱ ኦሮሞኛ ተናጋሪ የኩሎ ጎሳ ተወላጅ ነው። ለምን ይህን የዛይ ዉሸት ሊፈበርክ ፈጠረ?
የዛይ ላቄ ኦርቶዶክስ ጉራጌዎችን ዘር ያጠፋው ማነው? ልብ በሉ በ1525 ግራኝ ዝዋይን፣ ባደቄን፣ ወጅን፣ ገንዝን፣ መላ ዳሞትን ሲያቃጥል ኦርሞ (ወይም ጋላ) በጠቅላላው በዚያ አካባቢ ያልነበሩ ሕዝብ ናቸው ። በግራኝ ታሪክ ውስጥ አንድ ቦታ ጋሎችን ወግቶ ሲያሰልም የተመዘገበ አንድ ታሪክ የለም ። በሌላ በኩል የዛሬ ስልጤ የወጅ ጉራጌ እና የዛይ ኣካል የነበሩት አዘርነትና ኡልባረኝ ወግቶ ያሰለመ ግራኝ ነው። ይህ ሁሉ ሲሆን ጋላ ወይም ኦሮም ባገሩ ለሽታ የለም ።
በዛይ ሃይቅ ደሴቶች ውስጥ ታቦትና መጻህፍት ደብቀው፣ የዝቋላና ምድረ ከብድ ዋሻ ውስጥ ታቦት ደብቀው ለኦርቶዶክስ 17 አመታት የተሰዉት እነዚህ ክቡር ያቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተከታዮች ጉራጌዎች ነበሩ ።
ልክ ግራኝ እንደ ሞተና ክርስቲያኖች ሲረጋጉ የአባ ገዳ ያልተቋረጠ ወረራ በማድረግ የዛይን ሕዝብ ዘር ያጠፉት የጋላ ገዳ ወራሪዎች ናቸው ። ከዚያም ክርስትና ተዳክሞ እስከ ዛሬ ያ አገር ሁሉ እስከ አርሲ፣ ነጌሌ ስልጤና ቡታጀራ ሙስሊም የሆነው በኦሮኦ ወረራ ሳቢያ ነው።
የዛይ ላቄ ጉራጌ ዘር የጠፋው በጋላ ውረራ ነው ፣ የጋፋት ዘር የጠፋው በጋላ ወረራ ነው ። ዛሬ ላይ ያገሪቱ ጥ/ሚ ኦሮሞ በዝዋይ ሃቅ ደሴቶች ውስጥ ታቦት በመደበቅ ኦርቶዶክስን አኖረ ኦሮሞ ብሎ ሲዋሽ እንደ መስማት የሚያሳምም ቅጥፈትና የበታችነት የለም ።
ለምሳሌ ዛሬ ላይ ጉራጌዎች ዝዋይ ሃይቅን ላቂ ጀምበር ይሉታል ታላቁ ጀምበር ወይም ብርሃን ማለት ነው ! ዛይ (ጻይ) ራሱ የጸሃይ ደሴት ማለት ነው ። ምድረ ብርሃን፣ አገረ ብርሃን ምለት ነው!
ለዚህ መሰል ቅሻሻ ዉሸት የታሪክና ቤተ ክህነት ምሁራን መልስ እንደ ሚሰጡበት እገምታለሁ!
https://en.wikipedia.org/wiki/Zay_language