Page 1 of 1

ኦርቶዶክስ ጠንክራ ወጣች! የማይገድልህ ነገር ያጠነከርሃል! What Doesn't Kill You, Will Make You Strong !!!

Posted: 15 Feb 2023, 13:38
by Horus
ጴንጤዎች ኦርቶዶክስ ሊጎዱ ሊያዳክሙ ሲንጫጩ ይህው መላ ኦሮሞ ኦርቶዶክስ እንዲሆን ገዳም በገዳም እንዲሆን ተወሰነ! ዋቃ ፌቴ ውጣ ኦርቶዶክስ ግባ !!! Actors produce unintended consequences!!

Re: ኦርቶዶክስ ጠንክራ ወጣች! የማይገድልህ ነገር ያጠነከርሃል! What Doesn't Kill You, Will Make You Strong !!!

Posted: 15 Feb 2023, 16:28
by Abere
ቤተክርስቲያኗ አሸናፊ ሁና መውጣቷ በጣም ትልቅ ነገር ነው። በዚህ ደረጃ ከሁሉም በላይ ምዕምኑ የቱን ያህል ለሃይማኖቱ ቀናኢ መሆኑን በታሪክ አስመዝግቦ አልፏል - በሌላ በኩል ይች ጥንታዊ ቤተክርስቲያን የማያርፉ ክፉ ጥላቶች በየጊዜው አድብተው እና ወቅት ጠብቀው እንደሚፈልጓት ትምህርት ሰጥቷል። ስለዚህ ምዕምኑ ዘወትር ንቁ መሆን ይገባዋል - አባቶችም ንቁ እረኞች መሆን። ይህ ዜና መልካም ቢሆንም በአንጻሩ ግን በሰማዕትነት ለተዋደቁት ክርስቲያኖች ግን ምን አልተባለም። ይህ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ወንጀለኞች ለፍትህ የሚቀርቡበት የተጎጅ ቤተሰቦች መንግስት ካሳ የሚከፍልበት አስገዳጅ ሁኔታ ስለመኖሩ አልተደመጠም። እንድሁ በዚህ ስበብ በተልካሻ ምክንያት ስለታሰሩት በርካታ ወገኖችም::

Re: ኦርቶዶክስ ጠንክራ ወጣች! የማይገድልህ ነገር ያጠነከርሃል! What Doesn't Kill You, Will Make You Strong !!!

Posted: 15 Feb 2023, 17:00
by Union
That is right. The actor's purpose was to divide, disorient, and conquer. But instead the actor is now disoriented and exposed to its bones as a result revealing Tewahido's inner power and intelligence for the whole world to see.

Tewahido full of amazing hidden power!

God bless Tewahido.

Tewahido Hiymanote!!

Horus wrote:
15 Feb 2023, 13:38
ጴንጤዎች ኦርቶዶክስ ሊጎዱ ሊያዳክሙ ሲንጫጩ ይህው መላ ኦሮሞ ኦርቶዶክስ እንዲሆን ገዳም በገዳም እንዲሆን ተወሰነ! ዋቃ ፌቴ ውጣ ኦርቶዶክስ ግባ !!! Actors produce unintended consequences!!

Re: ኦርቶዶክስ ጠንክራ ወጣች! የማይገድልህ ነገር ያጠነከርሃል! What Doesn't Kill You, Will Make You Strong !!!

Posted: 15 Feb 2023, 20:19
by Horus
Abere wrote:
15 Feb 2023, 16:28
ቤተክርስቲያኗ አሸናፊ ሁና መውጣቷ በጣም ትልቅ ነገር ነው። በዚህ ደረጃ ከሁሉም በላይ ምዕምኑ የቱን ያህል ለሃይማኖቱ ቀናኢ መሆኑን በታሪክ አስመዝግቦ አልፏል - በሌላ በኩል ይች ጥንታዊ ቤተክርስቲያን የማያርፉ ክፉ ጥላቶች በየጊዜው አድብተው እና ወቅት ጠብቀው እንደሚፈልጓት ትምህርት ሰጥቷል። ስለዚህ ምዕምኑ ዘወትር ንቁ መሆን ይገባዋል - አባቶችም ንቁ እረኞች መሆን። ይህ ዜና መልካም ቢሆንም በአንጻሩ ግን በሰማዕትነት ለተዋደቁት ክርስቲያኖች ግን ምን አልተባለም። ይህ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ወንጀለኞች ለፍትህ የሚቀርቡበት የተጎጅ ቤተሰቦች መንግስት ካሳ የሚከፍልበት አስገዳጅ ሁኔታ ስለመኖሩ አልተደመጠም። እንድሁ በዚህ ስበብ በተልካሻ ምክንያት ስለታሰሩት በርካታ ወገኖችም::
አበረ፣
እኔም ተመሳሳይ ስሜትና ሲቃ ነው የያዘኝ ። በኦሮሚያው ውስጥ ብዙ ገዳማትን አቁሞ ፣ ብዙ መንፈሳዊ ኮሌጆችን ለመክፈት መፈንቅለ ሲኖዶስ ለምን አስፈለገ? ለምን 35 ንጹሃን ተሰዉ?! የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በመላ ኦሮሚያ መስፋፋቱ የመላው ኦሮቶዶክስ አላማ አይደለምን? ይህ ነው እጅግ የሚያሳዝነው!

ያቡነ አብርሃምን ዘገባ ሁለቴ ሰማሁት ። ብቸኛው የኦሮሞ ጥያቄ ሆኖ የወጣው ጭብጥ ኦሮሞ ብዙ ደጋማት ይፈልጋል፣ ብዙ ካህናት ስለሚፈልግ መንፈሳዊ ኮሌጆች መከፈት አለባቸው፣ ይህም እንዲሆን ባጀት ይጨመረለት የሚል ነው በቃ!

ታዲያ ለነዚህ የራሷ የኦርቶዶክስ ግቦች ለምን ማቅ እንድንለብስ ተደረገ? እነዚያ 35 ሰማዕታት ሕይወት ስ?? እጅግ እጅግ ያሳዝናል ኦሮሞ የሚባሉ በሽተኛ ልሂቃን የሚሰሩት ስራ !!!!

አንተ ያልከው ነገር ማለትም የሰማዕታቱ ጉዳይ ሲኖዶሱ እንዲፈታው ግፊት መፍጠር አለብን! የሰማዕት ሃውልት እንዲቆምላቸው ! ገድላቸው በስንክሳር ለዘላለም እንዲያዝና ቤተሰቦቻቸውን የመርዳት ጉዳይ ።