Page 1 of 1

የተሸነቆረው መንግስት - ከመሞት መሰንበት?

Posted: 11 Feb 2023, 10:59
by Selam/
በእኔ እይታ የሰሞኑ ቀውስ የሚከተሉትን መሰረታዊ ውድቀቶችንና መነቃቃቶችን ፈጥሯ:

- ዶሮ ጭራ ጭራ መታረጃዋን ታወጣለች እንደሚባለው ሳይከካ የተቦካው የአብይ እንጭጭ መንግስት እራሱን በአደባባይ ሸርፎና ገጥቦ ሽምድምድ ያለ የውዳቂዎች ውዳቂ ሆኗል። ከመሞት መሰንበትን መርጦ ትላንትና የተፋውን መልሶ ቢውጥም፣ ከእንግዲህ በኋላ የተቃዋሚዎችና አኩራፊዎች መፈንጫ ከመሆን አይድንም።

- እንደኔ ሲጠራጠሩና በተስፋ ክር ተንጠልጥለው የነበሩ ሆደ ሰፊና ትዕግስተ-ብዙ ኢትዮዽያኖች ወደ አብይ ጠላትነት ሰተት ብለው እንዲገቡ እራሱ መንግስት በምላሱ መንገዱን ላስ አድርጎ ጠርጎላቸዋል። ዛሬ ቢይንስ ሶስት-አራተኛው የኢትዮዽያ ህዝብ የኦነግ-ሸኔን መንግስት በአጽንዎ ይቃወማል እንዲንኮታኮትም ይመኛል። ከዚህ በተያያዘ የመብት ረገጣን የመቃወሙ ዘመቻ ከየአቅጣጫው ተቀጣጥሎ ይቀጥላል፣ ማንም ሊያቆመው አይችልም። የተሸነቆረ መንግስት ማለት ይኸ ነው። መቀየር እንጂ መጠገን በፍፁም አይቻልም!

- የአናሳው የሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ አስተዳደር ከሁሉም ክፍለ ሀገራት ተነጥሎ የማፍያ ስብስብና በደምና ብቀላ የሰከረ የሲዖል ምሳሌ መሆኑን እራሱ በግልፅ ለዓለም አሳይቷል። ዛሬ ኦሮሚያ መሄድ ማለት ልክ የመንና ሶማሊያ መሄድ ማለት ነው።

- አድር ባይ የመንግስት ደጋፊዎችና አብሮ አበሮች፣ የቴሌቪዥንና ሬዲዮ አዘጋጆች ከገዳዩ መንግስት ጀርባ በመደበቃቸው እራሳቸውን አዋርደዋል። ከዚህ በኋላ፣ ከኢትዮዽያ ቴሌቪዥን ይልቅ እነ መጋዣው አበበ በለው፣ ቀውሱ ዘመድኩንና አድርባዮቹ ኤርሚያስ ለገሰና ሀብታሙ የተሻለ ተደማጭነት ቢኖራቸው አይደንቀኝም።

- ክፉ ባይኖር የመልካም ዋጋ አይታወቅም እንደሚባለው፣ ሞልቶ የፈሰሰው የህገ-አራዊቱ የኦነግ-ሸኔ ጥጋብ፣ የኢትዮዽያና የዓለም ህዝብ ስለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታላቅነትና በሳልነት እንዲማር አድርጓል። በአጭር ጊዜ ወደ 70 ሚሊዮን የሚጠጉትን ምዕመናኖቿን ሃይማኖታቸውን እንዲጠብቁ ማነቃቃቷና ማሰባሰቧ፣ እንዲሁም የሌላ ሃይማኖት ተከታዮችና የዓለም ኦርቶዶክስ ማህበርን ከጎኗ እንዲቆሙ ማድረግ መቻሏ ብቃቷንና የፈጣሪን ድንቅ ስራ ፍንትው አድርጋ አሳይታለች። በተቃራኒው አስመሳይ ሀዋርያዎችና ፓስተሮች አንሰው አንሰው ቁጫጭ አክለዋል።
እኔ የማፍረው ትልቁ የኢትዮዽያ አለት ተሰብሯል ሲባሉ ጮክ ብለው “አ ሜ ን” ላሉት ነው።

አውሬው ቆስሏል፣ ግን አሁንም አውሬ ነው!

Re: የተሸነቆረው መንግስት - ከሞመት መሰንበት?

Posted: 11 Feb 2023, 11:49
by Abere
A wounded beast is more deadly, it is good idea to stay on alert.
Selam/ wrote:
11 Feb 2023, 10:59

አውሬው ቆስሏል፣ ግን አሁንም አውሬ ነው!

Re: የተሸነቆረው መንግስት - ከሞመት መሰንበት?

Posted: 11 Feb 2023, 17:13
by Selam/
ትክክል - ህገ-አራዊቱ ፕላን B ላይ እየሰራ ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም!

Abere wrote:
11 Feb 2023, 11:49
A wounded beast is more deadly, it is good idea to stay on alert.
Selam/ wrote:
11 Feb 2023, 10:59

አውሬው ቆስሏል፣ ግን አሁንም አውሬ ነው!

Re: የተሸነቆረው መንግስት - ከመሞት መሰንበት?

Posted: 28 Dec 2023, 16:12
by Misraq
Selam/ wrote:
11 Feb 2023, 10:59
- እንደኔ ሲጠራጠሩና በተስፋ ክር ተንጠልጥለው የነበሩ ሆደ ሰፊና ትዕግስተ-ብዙ ኢትዮዽያኖች ወደ አብይ ጠላትነት ሰተት ብለው እንዲገቡ እራሱ መንግስት በምላሱ መንገዱን ላስ አድርጎ ጠርጎላቸዋል።
ሆደ ሰፊው የማረቆ ተወላጅ ግንቦቴው ሰላም February 12 ይህንን ማኒፌስቶ ጽፈህ ከኦሮሙማ ስለተገነጠልክ ከሁለት ወር በህዋላ ለምታከብረው አንደኛ አመት እንንነጋገር፥፥

ግን 5 አመት ሙሉ አብይ ወኦሮሙማ የአማራ ሕዝብን ሲያርድና ሲያሳርድ ምን ትሰራ ነበር? የስልጣን ኮርቻውን ሲያደላድል ለምን 5 አመት ሙሉ Twerk አደረግህለት? ፖለቲካን ቆርጥሜ በልቻለሁና አስተዋይ ነኝ ካልክ 5 አመት ሙሉ እንዴት ቁማር ተበላህና በካልቾ ተብለህ በመጨረሻው ሰአት ተባረርክ፥፥ ከአሳማው ነአምን ዘለቀ እና ከአንዳርጋቸው በጥቂት ወራት ቀድመህ ስለወጣህ ግን ሳላደንቕ አላልልፍም

Re: የተሸነቆረው መንግስት - ከመሞት መሰንበት?

Posted: 28 Dec 2023, 17:23
by Selam/
ቱስ ቱስ ወያኔ - ፕላኔት ሆቴል ጭር ሲልብሽ ፣ የአማራ ጭንብል ለብሰሽ ፉን ፉን ስትይ ታሳዝኝኛለሽ። ጉጥ!
Misraq wrote:
28 Dec 2023, 16:12