ቅዱስ ሲኖዶስ ለእሑድ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ "ላልተወሰነ ጊዜ" ተራዘመ
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን በገጠማት ችግር ለእሁድ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. የጠራችውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲራዘም ወሰነች።
ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባን ተከትሎ በተሰጠው መግለጫ መንግሥት የቀረቡለትን ጥያቄዎችን ለመመለስ በመወሰኑ ሰልፉ መራዘሙ ተገልጧል።
"ሰልፉ እንዲራዘም የተወሰነው ቤተ ክርስትያኗ የአቋም ለውጥ አድርጋ ሳይሆን ለሰላም ክፍት በተደረገው በር መንግስት ችግሩን ለመፍታት በመስማማቱ ነው" ተብሏል።
Advertisement
መግለጫው አያይዞም "ነገር ኝ መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ የማይፈፅም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል" ሲል አሳስቧል።
በማከልም ሰልፉ በተጠራበት ዕለተ እሑድ የካቲት 5 ቀን የእምነቱ ተከታዮች በየአጥቢያቸው በሚገኙ ዐቢያተ ቤተክርስቲያናት ዐውደ ምሕረት ላይ ባለመቅረት የተለመደውን የዕለተ ሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ፣ የጸሎት፣ የምሕላና የትምህርት ወንጌል ከወትሮው በተለየ የመንፈሳዊ ሥርዓት በማከናወን እንዲያሳልፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ ማስተላለፉን ጠቅሷል።
Continue reading https://www.sbs.com.au/language/amharic ... /qjuc8j3c7
