Page 1 of 1

የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 08 Feb 2023, 14:54
by Horus
ዲክታተር አቢይ አህመድ አሊን ደግፈው ያቆሙ 3 ቡድኖች (ደጋፊዎች) አሉ፣ ናቸው ።

ምሰሶ 1፣
እነዚህ ቁልፍ (ዋና) ደጋፊ ይባላሉ ። እነሱም ሚኒስሮች፣ ከንቲባዎች፣ የክልል ፕሬዚዳንቶች፣ የፓርቲ ሴንትራል ኮሚቴ፣ የሴኩሪቲ፣ የፖሊስ፣ የስለላ፣ የጦር ጄኔራሎች፣ ትላልቅ ባለሃብቶና ኦሊጋኮች ናቸው ። አንድ ዲክታተር ከነዚህ ቁልፍ ደጋፊዎች በብዛት ከከዱት ይወድቃል ። ዛሬ ላይ በዚህ ቁልፍ መደብ ውስጥ ብዙ መክዳት አይታይም ።

ምሰሶ 2፣
እነዚህ ተጽኖ ፈጣሪዎች (ኢንፍሉወንሰር) ይባላሉ ። የነሱ ስራ ዲክታተሩ በሕዝብ እንዲደገፍ፣ እንዲወደድ፣ እንዲከበር፣ እንዲታወቅ፣ እንዲጀግን የሚሰብኩ፣ የሚታስተምሩ፣ የሚያስረዱ፣ የሚቀሰቅሱ፣ የሚያነቁ መደብ ናቸው ። ለምሳሌ የሚዲያ፣ የአርት፣ የእስፖርት፣ የስነጽሁፍ፣ የሃይማኖት፣ የማስታወቂያ፣ የባህል
ሙያተኞች ናቸው ።

ይህ የዲክታተሩ ተጽኖ ፈጣሪ መደብ አሁን ላይ ፍርስርሱ እየወጣ ነው ። እራሱ ዲክታተሩ ከሚያዛቻው የመንግስት ተቀጣሪዎች ውጭ ያሉት እጅግ በብዛት ዲክታተሩን እየከዱት ይገኛሉ ። ኦርቶዶክስ አማኞች፣ ወንጌላዊ አማኞች፣ የግል ሚዲያዎች፣ የፊልምና ድራማ ኢንዱስትሪ ፣ ተዋኛን እያለ ዝርዝሩ ይወርዳል ። እነዚህ ናቸው የሚቀጥለው ምሰሶ 3ን ኢንፍሉወንስ የሚያደርጉ። ይህ አንዱ ትልቁ የዲክታተሩ ውድቀት ምልክትና ምክንያት ነው ።

ምሰሶ 3፣
እነዚህ ድምጽ ሰጭዎች ይባላሉ ። ዲክታተሩ ስልጣን ላይ እንዲወጣ ድምጽ የሚሰጡና ሕጋዊ ሽፋን የሚሰጡት መደብ ነው ። ይህ መደብ በመሰረቱ እንደ ወረደ ኃይል የለውም ። ይህ መደብ ኃያል የሚሆነው በእምቢተኘትና አመጽ ሲነሳ ብቻ ነው ። የምሰሶ 2 ስራ ይህ 3ኛ መደብ ዲክታተሩን ደግፎ እንዲቆም ድምጽ እንዲሰጥ ማንቃት ነው ። ነገር ግን ምሰሶ 2 ዲክታተሩን ከድቶ መደብ 3 እምቢ እንዲል ማስተማርና ማንቃት ከጀመረ የዲክታተሩ ውድቀት በተግባር ይጀምራል ።

ከዚያ የሚቀረው የምሰሶ 1 እርስ በርሱ መከፋፈልና የዲክታተሩ መነሳት ነው ።



Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 08 Feb 2023, 15:17
by Horus

Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 08 Feb 2023, 15:40
by Horus
በጥቁር ቀለም አንድ የሆነችው ኢትዮጵያ ፍጹም ባልታሰበ መንገድ ባገሪቱ ታሪካዊ የሆነ መንፈሳዊ ማዕበል አስነስቶ ግዙፍ የካልቸር ለውጥ እያመጣ ነው። ኢትዮጵያ እጅግ እጅግ መንፈሳዊ እስፒሪቿል ማህበረሰብ እየሆነች ነው። ያስገርማል !!!


Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 10 Feb 2023, 17:19
by Horus
የፖለቲካ ሳይንስ ዝንፍ አይልም። እኔ ሆረስ ደጋግሜ The Dictator's Handbook ከጃችሁ አይጥፋ ብዬ ነበር ። ከላይ ያለውን ሞዴል ደግማችሁ አጢኑት ። በ3ቱም የዲክታተሩ ምሰሶዎች ውስጥ መፍረክረክ አለ ብዬ ነበር ።

ትላንት ማታ ዋና ቁልፍ የሚባሉት ያቢይ ደጋፊ ምሰሶ አንድ ያደረገውን ስብሰብ ከኢትዮ360 ዝርዝሩን ስሙት ። አቢይ አህመድ በማንኛውም መንገድ የእሁዱን ሰልፍ በኃይል ለመደምሰስ እንዘጋጅ ብሉ ፕላን ጠየቃቸው የምሰሶ 1 አባላትን ፤ የፖሊስ፣ ሴኩሪቲ፣ ሌላም ሌላም የኃይል ኦርጋኖች! እነሱ ግን አንችልም ብለው እምቢ አሉት! በዚህም ምክኛት አቢይ አፈገፈገ!!!

ስለዚህ ልክ የዲክታተሩ መጻፍ እንደ ሚለው አንድ ዲክታተር የምሰሶ 1 ድጋፍ ካጣ መውደቅ ፣ መሸነፍ ይጀምራል ! የሆነውም ያ ነው !!!

አቢይ አህመድ አሊ የኦርቶዶክስን ተቋም ለመቆጣጠር ያቀደው እስትራየጂክ አላማ ተሸንፎ ወድቋል ። አቢይ ግዙፍ ግዙፍ የፖለቲካ ሽንፈት ደርሶበታል ።

ከዚህ በኋላ ያለው ማንገራገር ይባላል። ዳሜጅ ኮንትሮል እንዲሉ !

ከዚህ ቀጥሎ ዲክታተር አቢይ የሚያደርገው በምሰሶ 1 ውስጥ የተቃወሙትን በሹም ሽር ያነሳል ። በምሰሶ 2 ውስጥ የከዱትን ባዲስ ተጽኖ ፈጣሪዎች መተካትና ለምሰሶ 3 ድምጽ ሰጭዎች አዲስ ትርክትና ስብከት ያዘጋጃል ።

እኔ ሆረስም ይህ ትንበያ ሁሉ እውን ሲሆን ተመልሼ አስታውሳችኋለሁ ! ሳይንሱ አይስትም !!!

የማታውን ካቢኔ የምሰሶ 1 ወሳኝ ክርክር ከታች ስሙት

Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 10 Feb 2023, 17:52
by Horus

Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 10 Feb 2023, 23:57
by Horus
አንድ ዲክታተር ቁልፍ ደጋፊዎቹ ዘ ኢሴንሻልስ ወግድ ካሉት አልቆለታል! ትላንት ማታ የሆነው ያ ነው! እኛ በሰላማዊ ሕዝብ ላይ አንተኩስም አሉት! ያን ግዜ ያቢይ 4ቱም ጎማዎች ፈነዱ ! በቃ


Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 11 Feb 2023, 00:07
by Horus
የዲክታተሩ ምሰሶ 2 አባል ስዩም ተሾመ በህይወት አለ እንዴ? የኦሮማራው ንጉስ!!!

Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 11 Feb 2023, 01:42
by Horus

Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 11 Feb 2023, 02:33
by Horus
Here is the entire book for free! A person can't consider himself or herself political animal without having this book!


Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 11 Feb 2023, 16:11
by Horus
ምን ብዬ ነበር? አቢይ አህመድ በፖለቲካ መግዛት ከዚህ በኋላ አላልኩም? አሁን እሱ የቀረችው ያችው ማስፈራሪያ ጭራቅ ኮማንድ ፖስት ነው

Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 14 Feb 2023, 01:09
by Horus
ትላንት ሌላ ሃረግ ላይ ዲክታተሩ ከዚህ በኋላ ብዙ በኦርቶዶክስነት የሚጠረጥራቸውን ደጋፊና ካድሬዎቹ ላይ ሹም ሽር ማድረግ ይጀምራል ብዬ ነበር!!! ይህው ስሙ ስለ ቀይ ቀይ ኮፊያ አማኝ ዘቦቹ ሁኔታ !

Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 16 Feb 2023, 21:49
by Horus
የእነ ታማኝ በየነ፣ ነአምን ዘለቀ፣ መሳይ መኮንን፣ የኔአለም አይነቶች አቢይን በምሰሶ ሁለት (ተጽኖፈጣሪነት) ደጋፊነት ወደ ተቃዋሚ ጎራ መግባት የዲክታተሩ ምሰዎች መነቃነቅ ብቻ ሳይሆን የዜግነት ፖለቲካው ጎራ መቀላቀላቸ አዲሱ የሃይል አሰላለፍ ምን እንደ ሚመስል እያሳየን ነው ። ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ ! በቃ !! የአቢይ የመምራት ፣ ተቀባይነት፣ ተሰሚነት፣ ታማኘነት ያበቃለት ጉዳይ ነው ፣ ከራሱ ቅልብ አሽከሮች ውጭ!!!

Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 16 Feb 2023, 21:55
by sun
Horus wrote:
11 Feb 2023, 02:33
Here is the entire book for free! A person can't consider himself or herself political animal without having this book!




Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 16 Feb 2023, 22:02
by Abere
ሆረስ፥

ድንቅ አገላለጽ ነው።የኦሮሙማው ጭራቅ መቆሚያ ሶስቱም ዋልታ ከዘራዎች (canes) ተሰንጠቀው እየተሰባበሩ ነው።
በአፈጢሙ መደፋቱ አይቀሬ እየሆነ ነው። በትንሽ በትልቁ እባብ እንደነከሰው እየባተተ ነው - ውሃ ጀሪካን እና እንስራ ላይ መተኮስ ተያያዟል፤ ንጹሃን እየገደለ ነው። ይህ የመውደቅ ጣጣ ነው። መቆሚያው እየተሰባበረ ነው።

Re: የዲክታተሩ መቆሚያ 3 ምሰሶዎች ተራ በተራ እየፈረሱ ነው!

Posted: 16 Feb 2023, 22:03
by sun
Horus wrote:
11 Feb 2023, 01:42