የኦሮሞሙማ ዻዻሶች ብዙ ኦሮሞዎችን ወደ ኦርቶዶክስ እምነት ካመጡ እሰይ ነው!
Posted: 31 Jan 2023, 06:40
ሰው ከአረማዊነትና እና ከባዕድ እምነት ወደ እግዚአብሄር ሲመለስ እንደማየት የሚያስደስት ነገር የለም። ሰማያዊ ነገር ነው።
በተለይም ወደ ኦርቶዶክስ ሲመጡ በሩን ወለል አድርገን ከፍተን፣ እሰይ እንኳን ጣዖታችሁን ወርውራችሁ ጥላችሁ ወደእኛ መጣችሁልን ብለን ጉንጫቸውን መሳም ነው ያለብን። ፈጣሪ ቋንቋ ስለሌለው፣ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ በእኩልነት ነውና የሚያው፣ በፈቀዱት ቋንቋ ይዘምሩ ይፀልዪ። እኔ ምን አገባኝ። “አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።” ገላትያን ፫፥፪፰
ችግር የሚሆነው እምነትን ለአናሳነት ስሜት ማካካሻ ወይንም እንደፖለቲካ ዱላ ስንጠቀምበት ነው። አንድ የሃይማኖት መሪ፣ ‘የታባታችሁ እኔም እንደናንተ የራሴ ቤተ እምነት አለኝ‘ ብሎ ሜንጫውን እየሰበቀ ከወንድሞቹ ከአፈነገጠ፣ በምድርም በሰማይም ድብን አድርጎ ከሽፏል። በተለይም የሰማይ ቤት ‘በኬኛ‘ አይገኝም። “ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ” ፊል ፪፥፫
ከሰኞ እስከአርብ በጎጥ ፖለቲካ ንትርክ ውስጥ ከተልከሰከስኩኝ፣ የማደርገው ሁሉ ከአናሳነት ስሜት የተነሳና ሌሎችን ለመምሰል ወይንም ለመብለጥ ከሆነ፣ የሰው ልጅ እንደበግ ሲታረድ እንዳልሰማ ፀጥ ለጥ ካልኩኝ፣ ዛፍንና የአተቴ ጨሌን ቅቤ መቀባት ካላቆምኩኝ፣ ሺህ ጊዜ እሁድ ለፎቶ ቤተክርስቲያን ደጃፍ ብኮለኮል፣ እምነት ከሌላቸው ያልተሻልኩኝ እንሰሳና ድውይ ነኝ።
“ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።” ማቴ ፩፮፥፪፫