Page 1 of 1

በመፈንቅለ ሲኖዶሱ ላይ የዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ!

Posted: 24 Jan 2023, 14:35
by Horus
ንቅናቄ ማለት ይህ ነው! ብረት በእሳት ይፈተናል! ከዚህ የኦሮሙማ ቅዠት ኢትዮጵያ እንደ ብረት ጠንክራ ትወጣለች!

Re: በመፈንቅለ ሲኖዶሱ ላይ የዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ!

Posted: 24 Jan 2023, 14:58
by Horus

Re: በመፈንቅለ ሲኖዶሱ ላይ የዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ!

Posted: 24 Jan 2023, 16:53
by Assegid S.
በእኔ እምነት የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጠንካራና ጤነኛ እግር እያላት በክራንች ለመራመድ የመረጠች አካለ ሳይሆን አስተዳደራዊ ስንኩል ናት። የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከመንግስት የበለጠ ሀይልና ተሰሚነት እያላት ኣንድም ውስጡዋ በመሸጉ የመንግስት ቅጥረኞች፣ ሁለትም ፍፁምና ደፋር ውሳኔ ለመውሰድ በሚቸገሩ አመራሮች እንዲህ እያነከሰች ስታዘግም ሳታስበው ትወድቃለች።

ምንም እንኳ የእምነቱ ተከታይ ባልሆንም ገና ከጠዋቱ ቤተክርስቲያኗ ሀገር አቀፍ ተቃውሞ ከጠራች ቦኃላ "ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል" ብላ ስትወላውል ደስተኛ ካልነበሩትና ከተቃወሙት ሰዎች መካከል ኣንዱ ነኝ። መስቀል የነፃነት ተምሳሌት እንጂ የባርነት ቀንበር አይደለም፥ ኣማኝ ለእምነቱ ታማኝ እንጂ ለነፃነቱ ለማኝ መሆን የለበትም ባይ ነኝ።

ቤተክርስቲያን ከእነዚህ ህገ-ወጦች ጋር በምንም አይነት መልኩ መደራደር የለባትም ። ይህ ሳይሆን ቀርቶ "ጥያቄያቸው በውይይት ይፈታ" ከተባለ ግን ነገ ፍላጎቱን ለማስፈፀም ታቦት የሚያግት ካህን ልናይ ነው ማለት ነው። ይህ ክህደትና ኣንዲቷን ቤተክርስቲያን የማዳከም ሴራ በሀገር በቀል ከሀዲዎች ብቻ ሳይሆን በውጭ ሀይል ቅጥረኞች ጭምር የሚፈፀም ደባ እንደመሆኑ ... መረር እና ጠንከር ማለት ተገቢ ነው።

Re: በመፈንቅለ ሲኖዶሱ ላይ የዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ!

Posted: 24 Jan 2023, 23:10
by Horus
Assegid S. wrote:
24 Jan 2023, 16:53
በእኔ እምነት የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጠንካራና ጤነኛ እግር እያላት በክራንች ለመራመድ የመረጠች አካለ ሳይሆን አስተዳደራዊ ስንኩል ናት። የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከመንግስት የበለጠ ሀይልና ተሰሚነት እያላት ኣንድም ውስጡዋ በመሸጉ የመንግስት ቅጥረኞች፣ ሁለትም ፍፁምና ደፋር ውሳኔ ለመውሰድ በሚቸገሩ አመራሮች እንዲህ እያነከሰች ስታዘግም ሳታስበው ትወድቃለች።

ምንም እንኳ የእምነቱ ተከታይ ባልሆንም ገና ከጠዋቱ ቤተክርስቲያኗ ሀገር አቀፍ ተቃውሞ ከጠራች ቦኃላ "ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል" ብላ ስትወላውል ደስተኛ ካልነበሩትና ከተቃወሙት ሰዎች መካከል ኣንዱ ነኝ። መስቀል የነፃነት ተምሳሌት እንጂ የባርነት ቀንበር አይደለም፥ ኣማኝ ለእምነቱ ታማኝ እንጂ ለነፃነቱ ለማኝ መሆን የለበትም ባይ ነኝ።

ቤተክርስቲያን ከእነዚህ ህገ-ወጦች ጋር በምንም አይነት መልኩ መደራደር የለባትም ። ይህ ሳይሆን ቀርቶ "ጥያቄያቸው በውይይት ይፈታ" ከተባለ ግን ነገ ፍላጎቱን ለማስፈፀም ታቦት የሚያግት ካህን ልናይ ነው ማለት ነው። ይህ ክህደትና ኣንዲቷን ቤተክርስቲያን የማዳከም ሴራ በሀገር በቀል ከሀዲዎች ብቻ ሳይሆን በውጭ ሀይል ቅጥረኞች ጭምር የሚፈፀም ደባ እንደመሆኑ ... መረር እና ጠንከር ማለት ተገቢ ነው።
አሚን አሚን! በኔም እምነት ያልከው ካልሆነ ከስር ያሉት ብዙ ጠንካራ ካህናት ገፍተው እንደ ሚወጡ አልጠራጠርም ! የአማኙ ግፊት እንዲያው በቀልድ ታፍኖ ስለማይቀር!