ኦሮሙማ አሁን ገና ከምንጊዜውም በላይ እራሱን የሚያጠፋበት ፈንጅ ቀበረ--> የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ህልውና ለመፈተን መሞከሩ።
በመጀመርያ ኦሮሞ ኦርቶዶክስ አይደለም የሚል ከፍተኛ ትርካት እና ጥላቻ ሲያናፍሱ የኖሩ ኦሮሙማዎች እንደት አሁን ኦርቶዶክስ የእኛ ነው አሉ? የእነርሱ ከሆነስ ለሁሉም ሊሆን የማይችልበት ምክንያት ምንድ ነው? ክስርትና ሰማያዊ ሃብት እንጅ ምድራዊ አይደለም፤ ታዲያ ቀምቶ ኬኛ ማለት ምን አይነት የአእምሮ ህመም ነው።
የኦሮቶዶክስ ሃይማኖት ጥንታዊ እና የምዕምናን እንጅ የግል ሃብት ወይም ጸጋ አይደለችም። ሰማያዊ እንጅ ክልላዊ ወይም ጎጣዊ አይደለችም። ይህ ጎጣዊ አስተሳሰብ ከኦነግ እና የተንኮል አስተማሪው ወያኔ የመጣ ነው። ወያኔ ስለሃይማኖቷ ርትዕትነት ጠፍቷት ሳይሆን ኦርቶዶክስን ማጥፋት ኢትዮጵያ የተሰራችበትን ድር እና ማግ መበጣጠስ ነው የሚል ፍልስፍና ስላላት ነው - አውቆ አጥፊ ናት። ኢትዮጵያን ስታጠፋ ግን ትግራይን እንደምታጠፋ አልታያትም ነበር - ይህም ድንቁርናዋ ነው። ኦነግ እንድሁ ወያኔ ስታደርግ ያየውን ነው ላድርግ ብሎ በ4 አመት ውስጥ ብቻ እንድህ ያቅበጠበጠው። ወያኔን ስትሾም ስትሽር አየ ዛሬ ኦነግ እንድሁ አድረገ።
ቁናሽ ቁናየ ነው - ትንሽ ዙሩ በዛ እንድሉ ዛሬ መፈንቅለ ፓትርያርክ እየተደረገበት ያለው እንደ ጎሳ ከትግራይ ክፍለ ሀገር የተመረጠ ፤ እንደ ክርስትና ምግባር ግን ኢትዮጵያዊ ነው - ኢትዮጵያዊ በቢላዎ እና ሜንጫ ወለጋ ፥አሩሲ ሲታረድ እንባውን ያነባ።
የኦነግ ከፋው ነገር ግን ኢትዮጵያን በማውደም ሀገረ -ኦሮምያ የምትባል ምናባዊ አገር በመፍጠር የኢትዮጵያን ሃይማኖት በመስረቅ ህገ-ወጥ የታሪክ እና የትውፊት ወንጅል ለመፈጸም መሞከር ነው። ይህ መንግስታዊ መዋቅር እና ድጋፍ ያለው ህገ-ወጥ ዝርፊያ ግን ከፍተኛ መዘዝም እንደሚያመጣ ምንም ጥርጥር የለውም። ኦነጎች የኢትዮጵያን ህዝብ ቢገፉት ቢገርፉት ዝም አላቸው ተኛባቸው ስለዚህ እጅግ ተዝናኑ ሽቅብ አስታወኩ ይህን የመጨረሻውን ሙከራ አደረጉ -እንደ ሚመስለኝ ግን የሃይማኖት ሰማዕትነት ጦርነት የሚያስነሳ እንጅ እንድሁ የባህርዛፍ ዱላ ተሸክሞ ኬኛ እያሉ ወያኔ እንደወጣችበት አይነት ቀላል አይሆንም። የወያኔም መባረር ምክንያት የባህርዛፍ ዱላ አይደለም የወልድያ፥የባህርዳ፥የጎንደር ወዘተ እጅ ለእጅ የተደረገ ፍልምያ ነው። ይህ የሰማዕትነት ጦርነት የአማራ ብቻ አይሆንም የትግሬውም ጉራጌውም ደቡቡም ኦርቶዶክስ ኦሮሙውም የሙስሊሙም ነው።