በ3000 አመታት የንጉሠነግስት ዘመን እኔ አማራ ነኝ፤ እኔ ትግሬ ነኝ እኔ ኦሮሞነኝ ወዘተ በእራሱ አንደበት የተናገረ መሪ የለም። ከመለስ ዜናዊ እና ዐብይ አህመድ በስተቀር - 2ቱ ያሳፍራሉ
በ3000 አመታት የንጉሠነግስት ዘመን ማንም መሪ እኔ አማራ ነኝ፤ እኔ ትግሬ ነኝ እኔ ኦሮሞነኝ ወዘተ በእራሱ አንደበት የተናገረ የለም። ከመለስ ዜናዊ እና ዐብይ አህመድ በስተቀር - 2ቱ ያሳፍራሉ ።በጥንት ዘመን የነበሩ መሪዎች እና ህዝባቸው ጎሰኝነትን እጅግ የሚጸየፉ በመሆናቸው ሰው የእግዜር ክቡር ፍጡር እንደሆነ በመረዳት ለአፍታ እንኳን የጎሳ ቅራቅንቦ ከምላሳቸው ይሁን ከአእምሯቸው አይገባም። ስለዚህ ነው በቅርብ ጊዜ እንኳን የነበሩትን መሪዎች የቤተሰብ ግንድ ፓለቲከኞች እንደፈለጋቸው ይህ የአያት ስም ይህ ጎሳ ሊሆን ይችላል ይህ ደግሞ እንደዚህ አይነት እያሉ ትንበያ እና ትርክት ላይ ጊዜያቸውን ያጠፉት። እነኝህ የጥንት ነገስታት እጅግ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል።ባለጌን እና ዋንጫ ከወደ አፉ ይሰፋል እንድሉና እንደነ መለስ ዜናዊ ያሉት ደግሞ ትግሬ ነኝ ብሎ ድፍን ኢትዮጵያን ትግሬ እንደሚገዛው አስመስሎ በንግግሩ ይደልቅ ነበር፤ በተራው እንድሁ አብይ አህመድ በእናቴም በአባቴም ንጹህ ኦሮሞ ነኝ የኦሮሞ መሪ ይለናል ።እንዳው ለመሆኑ ንጹህ ትግሬ ወይ ንጹህ ኦሮሞ የሚባል ነገር አለ እንደ?