Page 1 of 1

ኦሮሙማ ማለት ምን ማለት ነው?

Posted: 18 Jan 2023, 14:46
by Wedi
ኦሮሙማ ማለት ምን ማለት ነው?


አንድ ጨርቁን የጣላ የኦሮሞን ብሔርተኛ ብትጠየቅው "ኦሮሙማ ማለት ኦሮሞነት ማለት ነው" ብሎ አቃሎ ይነግርሀል፣ ኦሮሞነት ማለትስ ምን ማለት ነው ብለህ ብትጠይቀው የራሱን version ይነግርሀል፣ ሳያውቀው/ሳይገባው ሊሆን ይችላል፣ ኦሮሙማ ግን "ኦሮሞ" ብሎ የሚገልፀው/መገለጫ አለው፣ ለማንኛው ኦሮሙማ ምንድን ነው?

"ኦሮሙማ" [Oromumma] የሚባለውን ቃል የፈጠሩትና የኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ ያስተዋወቁት አብዱል ከሪም ኢብራሂም አሚድ [ጃራ አባ ገዳ]ና የትግል አጋሩ ሳይድ ሳሚር ጂሳ ናቸው፤ የIslamic Front for the Liberation of Oromia (IFLO) መስራቾች ናቸው፣ ቃሉ የተመሰረተው ሁለት ቃላትን በማዳቀል ነው፤ “ኦሮሞ/Oromo" እና “ኡማ/Ummah” የሚሰኙትን ቃላቶች አዳቅለው [ኦሮሙማ/Oromumma] የምትሰኝ ቃላት ፈጠሩ፤

“ኡማ/Ummah” የአረብ ቃል ነው፤ የቃሉን ትርጉም በእንግሊዝ አፍ እንደወረደ እንዲህ ይነበባል:-

Ummah (Arabic: أمة‎ [ˈʊm.mæ]) is an Arabic word. In the Quran the ummah typically refers to a single group that shares common religious beliefs, specifically those that are the objects of a divine plan of salvation. In the context of pan-Islamism and politics, the word ummah can be used to mean the concept of a Commonwealth of the Believers (أمة المؤمنين ummat al-muʼminīn).

በመጨረሻው አረፍተ ነገር ላይ እንደተገለፀው ቃሉን ፖለቲካ ውስጥ ስትጠቀመው የሀይማኖት አንድነት ወሳኝ የመሰባሰቢያ ጥላ ነው፣ ይህን የምለው ከልቦናዬ አንቅቼ አይድለም፣ ማስረጃ መቁጠር እችላለሁ፣

በTerje Østebø [ኖርዌጂያዊ ነው] ተጠንቶ “Journal of Religion in Africa” የሚሰኝ ጆርናል ላይ "The Question of Becoming: Islamic Reform Movements in Contemporary Ethiopia” በሚል ርዕስ የታተመው የጥናት ወረቀት (ገፅ 15) የሚከተለውን ይላል

“ Interesting to note is that rather than the idea of the Ummah– a community based on religious exclusiveness, it is Oromumma – a community based on ethnic exclusiveness that is advocated by many of the ulama of Robe”

እዚሁ የጥናት ወረቀት ላይ የኦሮሞ ትግል ከጅሀድ ጋር መሳ ለመሳ ተቀምጦ ይጠብቅሀል፤

'One of the sheikhs went as far as saying; ‘what we are talking about is a struggle for the freedom of the Oromo; an ethnic jihad’

ኦሮሙማ ከቋንቋና ከባህል በተጨማሪ የራሱ ሀይማኖት አለው፣ ሀይማኖቱ እስልምና ነው፣ ክርስቲያ (በተለይ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን) ሁነህ ኦሮሞ መሆን አትችልም፣ በኦሮሞ ጥናት ላይ "አንቱ" የተባሉት Terje Østebø እና Kjetil Tronvoll የዛሬ 9 ወር “Interpreting contemporary Oromo politics in Ethiopia: an ethnographic approach” በሚል ርዕስ ያሳተሙት ጥናት ላይ የሚከተለው ሰፍሯል፣

“The importance of religion was moreover noticeable during Haacaaluu Hundeessaa’s funeral, when Muslim Oromo in Bale expressed surprise that he was buried in an Orthodox Church – saying, “We thought he was Oromo”, reflecting their view that Orthodox Christianity is equated with the Amhara"

"ሀጫሉ ሁንዴሳ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያ ሲቀበር አይተው ሀጫሉ ኦሮሞ ይመስለን ነበር" ነው ያሉት፣ በሌላ አባባል ኦርቶዶክስ ኦሮሞ የለም፣ ይህ የተራው የባሌ ኦሮሞ አስተሳሰብ ብቻ አይደለም፣ ዶ/ር ገመቹ መገርሳ LTV ላይ ቀርቦ ክርስትና የተነሳ ሰው ኦሮሞነቱን ይነጠቃል ብሎናል፣

አንድ ሀቅ አለ፤ የኦሮሞ ማህበረሰብ በተፍጥሮው በcultural intolerance የታወቀ ነው፤ የሚያውቀው መዋጥ (assimilation) ብቻ ነው፤ ብዝሀነት (pluralism) የሚባል ነገር የለም፤ የኦሮሞን መስፋፋት በወፍ በረር የሚያውቅ የምለው ይገባዋል፤ ይህ የኦሮሙማ አካል ነው፣ እንዲህ ባለ ማህበረሰብ አፈጣጠር ውስጥ ሀይማኖትን ስትደርብበት ሁሉም ነገር ያከትማል፤ like it or not; the Oromo nationalism has no room for other religions but Muslim፣ ክርስቲያን ሁነህ ኦሮሞ መሆን አትችልም፣ ይህው ነው!!፣
ሲጠቃለል:-

ኦሮሙማ ideology ነው፣ ኦሮሙማ ማለት አንድ መሆን ሳይሆን አንድ አይነት ማድረግ/መሆን ማለት ነው፣ አንድ ቋንቋ፣ አንድ ባህል፣ አንድ ኃይማኖት ወዘተ፣ ኦሮሙማ ብዝሀነትን አይታገስም፣ አያከብርም፣ በኦሮሙማ አስተምሮ ኦሮሞነት ኃይማኖት አለው፣ እስልምና! ይህ ideology ኦሮሞን ራሱ አይጠቅምም፣ እነሱ አሀዳዊ ብለው የሚገልፁት ኦሮሙማን ነው፣

ብዙ የኦሮሞ ተወላጆች ኦሮሙማን የተመለከተ የራሳቸው interpretation ሊኖራቸው ይችላል፣ እኛ ተፅፎ ያገኝነው ግን ከላይ የተገለፀው ነው፣ የተፃፈውን ከሞላ ጎደል መሬት ላይ አይተነዋል፣ የሽመልስ አብዲሳ አስተዳደር ኦሮምኛ ቋንቋንና ባህልን ሌላው ላይ ለመጫን ይህን ያህል መዋከብና መቋመጥ የለበትም፣ just make it appealing to other ethnic groups. ወዶና ፈቅዶ የራሱ ያደርገዋል፣ በፖሊሲ የታቀፈ assimilation በሌላው አለም ተሞክሮ ከሽፏል፣ ይህን አዲዋሎጂ ዘመኑን እንዲዋጅ አድርጋችሁት ከሆነ አሳዩን፣ ካልሆነ አትጨቅጭቁን፣ አዋ ኦሮሙማ ይውደም!