Page 1 of 1
እናትዋ ጎንደር [VIDEO]
Posted: 13 Jan 2023, 14:24
by Revelations
Re: እናትዋ ጎንደር [VIDEO]
Posted: 13 Jan 2023, 14:37
by Revelations
እናትዋ ጎንደር ሙሉ የሙዚቃው ግጥም
በባልቴት ውበት ሁሌም ወይዘሪት
ማይነጥፍ ጅረት ጎህ ለነፃነት
ፈጣሪ ጦቢያን ሲከልላት
የምሰሶዋን ስም ጎንደር አላት
እንዳለች አለች ታተይ ሙሽሪት
ሒያጅና መጭን እንደታዘበች
እስኪ እህህ ልበል ጥቂት ባንች ቦታ
ታንጀትሽ ላይ ሆኘ ኸልብሽ በአንድ አፍታ
እንዴት ነው አዘዞ ጮማ በልቶ ጠጅ
ታንች የሚያደርሰኝ መግደርደርሽ እንጅ
የአባት የማረጉን ወግ ወጉን አዳብላ
አሳድጋኛለች እሹሩሩ ብላ
የምድር መዳኛው ታጠነ አርባራቱ
መሥዋአት አቅርቡ ስለት ለታቦቱ
ሴት አረሆ
አረ በፈጠረህ አረ እንዴው በሞቴ
እስኪ ተወኝ ባክህ ላታፅናናኝ እቴ
ይልቅስ ውሰደኝ ካለበት እትብቴ
መፅናኛየ እሷ ናት ልሒድ ወደ እናቴ
የዋልያ ቀንዱን መሥሎ ሹርባዋ
ሰልመም ብላ መጣች አረግ እናትዋ
ልቧም ካልፈቀደ ደስም ካላላት
በካሳ አትጨክንም በፋሲል በላት
በጎንደሮች መዳፍ ስጎርስ እዛም እዛም
ተመልሼ መጣሁ በእጄም ሳልጠቀም
ክፋ እስለምደሽኝ ጮማና ወርች
እናና ተጎዳሁ እኔ ስርቅ ካንች
የበሽታን ነገር ለሐኪም ይሰጡታል
የአጋንንትን ነገር ፀበል ይገቡታል
የጎንደርን ናፍቆት እንዴት ያረጉታል
እነ ቴቴ ጉርሻ አረ እንደምናችሁ
እነ ዋዋ ጉርሻ አረ እንደምናችሁ
ጉብ ጉብ አለብኝ አፈር ልብላላችሁ
የመሣፍንቱ እናት እቴቴ ማንአህሎሽ
ጉድ ጉድ በይልኝ ጥምቀት መጣሁልሽ
እንደ ህማማቱ የአንችው ፆመኛሽ
በባዶ እግሬ እምብርክክ የምሳለምሽ
መሠንቆ ተናገር ጀግንነቱን አውራ
አርግፎ የሚጥል ተሰማይ አሞራ
ድንበር ጠባቂ ነው በጠላቱ አይሞትም
መሣሪያው ደም መላሽ እንደ ታናሽ ወንድም
Re: እናትዋ ጎንደር [VIDEO]
Posted: 13 Jan 2023, 14:50
by Fed_Up
10 "like” ቢቻል እገጨው ነበር ... አንዷን ላይክ ግን ሁለቴ ሳላስብ ገጭችዋለሁ::
ድንቅ ሰራ ነው!!
Re: እናትዋ ጎንደር [VIDEO]
Posted: 14 Jan 2023, 02:38
by Revelations
Re: እናትዋ ጎንደር [VIDEO]
Posted: 14 Jan 2023, 02:42
by Noble Amhara
Relaxing song with right frequency is very close to traditional music... The higher frequency songs are less natural and traditional like Dagne Walle Newer songs.
Re: እናትዋ ጎንደር [VIDEO]
Posted: 15 Jan 2023, 17:31
by Revelations
Re: እናትዋ ጎንደር [VIDEO]
Posted: 15 Jan 2023, 22:02
by Revelations