Page 1 of 1

ከኒስያ ካዉንስል እስከ ላዉዳቶ ሲ እና የኢትዮጵያ ፓስተር

Posted: 05 Jan 2023, 19:59
by Naga Tuma
በቅርቡ ኣንድ ጥያቄ ጠይቄ እስከ ኣሁን መልስ ኣላገኘሁም።

ያስጠየቀኝ የዛሬ ሰባት አማታት በፊት የካቶሊክ ቤተክርስትያን ፖፕ ያሳተመዉ ላዉዳቶ ሲ ነዉ። ላዉዳቶ ሲን ሳስተዉስ ደግሞ የኒስያን ካዉንስል ኣስታወስኩኝ።

የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እንደ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ዋና ጳጳስ እንዳለዉ ኣላዉቅም። ነገር ግን የኮንስታንትኖፖልን ጳጳስ እንደ ዋና ያያሉ የሚል ጽሑፍ ኣንበቤኣላሁ። እኚህ ጳጳስ እንደ ካቶሊኩ ፖፕ የለዉዳቶ ሲን ኣይነት ጽሑፍ ማዉጣት የሚችሉ ወይም የለመዱ መሆኑን ኣላዉቅም።

ዋናዉ ጥታቄዬ የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን እንደ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ዋና መሪ ኣለዉ ወይ ነዉ። ካለዉ ማእረጉ ምን ይባላል? ስለማላዉቅ ዋና ፓስተር ልበለዉ።

ቀጥሎ የመጣልኝ ጥያቄ በዋና ፓስተር የሚመራ የክርስትያን ማህበረሰብ ስለ ኒስያ ካዉንስል እና ላዉዳቶ ሲ እንዲሁም ከኒስያ ካዉንስል እስከ ላዉዳቶ ሲ ምን ያህል ያዉቃል ነዉ። ግዙፍ ጥያቄ ነዉ። ጥልቅ መልስ የምያስፈልገዉ ነዉ።

እንደሚገባኝ ከሆነ የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን ከካቶሊክ ቤተክርስትያን የወጣ ነዉ።

በኦርቶዶክስ እና ከቶሊክ ቤተክርስትያናት መካከል ያለዉን ልዩነት በጥልቀት ኣላዉቅም። ከመነሻዉ ጀምሮ ልዩነት እንዳላቸዉ ነዉ የሚገባኝ።

ከፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች ጋር ከወጣትነት ጊዜዬ ጀምሮ ስለሃይማኖት ተነስቶ ተወያይቻለሁ። ከእልምና ሃይማኖት ተከታዮች ጋርም ስለሃይማኖት ተነስቶ ሁለት ጊዜ ተከራክሬኣለሁ። በሃይማኖት ባንስማም በሁለት መሠረታዊ ሀሳቦች ላይ መግባባት የሚቻል ደረጃ ላይ ደርሰን ነበር።

እስከዛሬ ድረስ ኣዲስ ሀሳብ ተናግሮ ረታኝ የምል የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ በአካል ኣጋጥሞኝ ኣያዉቅም። ሁለቴ የታዘብኩት ፓስተር ኣጋጥሞኛል።

ኣንዴ ከቤተዘመድ ሰዉ ኣርፎ መጥቶ ቤቴ መጥቶ ሳይጠየቅ እንጸልይ ብሎ ተነሳ። ቀጭ ብዬ ቀና ብዬ ኣየሁት እና ያረፉት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ናቸዉ ኣልኩት። ተመልሶ ተቀመጠ። ያረፉት ምናልባት ፓስተሩ እስከዛሬ የማያዉቀዉ ታሪክ ኣላቸዉ። ኣይተዉ ታዝበዉ ወንድን የምያኮላሽ ሃይማኖት ኣይነት አባባል የተናገሩ ናቸዉ።

ሁለተኛዉ ጊዜ ዘመድ ቤት ተጋብዤ ሄጄ ነዉ። ያዉ ፓስተር ተነስተን እንጸልይ ኣለ። እኔ የሃይማኖቱ ተከታይ ስላልሆንኩ ቁጭ ኣልኩኝ። አትጸልዩ ኣላልኩም። እኔ ተነስቼ ከመሳተፍ ተቆጠብኩኝ። ጸሎት ትቶ እኔ እንድነሳ በተዘዋዋሪ መዝለፍ ጀመረ። ሰምቼ ዝም ኣልኩኝ። ባሰበት። ዝምታ ወርቅ ነዉ ኣልኩኝ፣ በሆዴ። ተዘዋዋሪ ዘለፋ ሰልችቶት ነዉ መሰለኝ ኣቆመ። ከዛም ለመናገር ተራ ኣግኝቼ በውቅቱ በአከባቢዉ ስለነበር ዉሃ እጥረት ከሳይንስ ጋር ኣያይዤ ትንሽ ሀሳብ ተናግሬ ኣቆምኩኝ። የነበረዉ ርእስ ከሳይንስ ጋር በቀላሉ ተገጣጠመልኝ። ካልዘነጋሁ ይህ ላዉዳቶ ሲ ሳይታወቅ በፊት ነበር።

ኣሁን የታዘብኩትን እዚህ ለመኮነን ኣይዴለም። ዋናዉ ጥያቄ የኢትዮጵያ ዋና ፓስተር የሚመራዉን ማህበረሰብ ከኒስያ ካዉንስል እስከ ላዉዳቶ ሲ ያለዉን ኣይ ኪዉ መፈተሽ ብቻ ነዉ። የእኔ ምኞት በጣም ከፈተኛ እንዲሆን ነዉ።

በዚሁ አጋጣሚ ስለ ኒስያ ከዉንስል ዉሳኔ አሳማኝነት እና ከኒስያ ካዉንስል እስካ ላዉዳቶ ሲ የለዉ መሠረታዊ እዉቀት መያዝ የብቃት ወይም እንተልጀንስን እና እንተልጀንስ ኮሸንት ወይም ኣይ ኪዉን ልዩነትን ያሳያል ባይ ነኝ።

ኣለማወቅ የመናቅ ምንጭ ነዉ።

የነበብኩኝ ታሪክ የምያመለክተዉ ለጎሰኝነት ምንጭ የሆኑት ሁለት ታሪካዉ መሪዎች ናቸዉ። ሙሴ እና ቶማስ ጀፈርስን።

ሙሴ ከፈርኦንነት መሪነቱ ስልጣን ሲባረር ያባረሩትን የተረገሙ፣ ያተቀበሉትን የተመረጡ ብሏል ተባለ።

ቶማስ ጀፈርሰን የቆዳን ቀለም ቀርቦ እዉቀትን ነዉ ፈተሽኩኝ ያለዉ። ማየት ኣልቻልኩም ብሎ ጎሰኝነት አሜሪካ ዉስጥ ህጋዊ እንዲሆን ምክንያት ሆነ።

ከእንደነዚህ ታሪካዊ ጫናዎች መላቀቅ በእዉቀት ነዉ። ለዚህ ነዉ የሚመራዉ ማህበረስ ከኒስያ ካዉንስል እስከ ላዉዳቶ ሲ ያለዉን እዉቀት መፈተሽ ኣስፈላጊ ነዉ የምለዉ።