ቀዝቃዛው ጦርነት - ትግራይን የመገንጠል እና የማስገንጠል ማመቻቸት ስራ --- > ወልቃይት ሁመራ ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት የመውስድ ሹክሹክታ።
ቀዝቃዛው ጦርነት - ትግራይን የመገንጠል እና የማስገንጠል ማመቻቸት ስራ --- > ወልቃይት ሁመራ ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት የመውስድ ሹክሹክታ።ህዝብ እንደሚያውቀው ወልቃይት እና ሁመራ ጉዳይ ወያኔን ለ27 አመታት እንቅልፍ ያሳጣው በመጨረሻም ከአዲስ አበባ እንድባረር ያደረገ ነው። የድፋን አማራ ህዝብ ሳይሆን በመጀመርያ እራሱ የወልቃይት እና ሁመራ ህዝብ የትግራይ አካል አለመሆኑን በረጅም የትግል ሂደት አረጋግጧል። ወልቃይት ሁመራ ጎንደሬ ስለመሆኑ የትግራይ ህዝብ ከልቡ ያውቃል። ይሁን እንጅ ዐባይ ትግራይ የሚባል ቅዠት ለመፈጸም ሲባል ወልቃይት ሁመራ የግድ ትግሬ መሆን አለበት። ወያኔ ተሸንፋም ይሁን አሸንፋ ይህ ጥማቷ መሳካት የግደታ ነው። ለዚህ ደግሞ ተገንጣዮች በእከክልኝ ልከክልህ ውለታ በመንግስትነት ሽፋን ህዝብ ሊያታልሉ አገር ሊያስገነጥሉ ከፍተኛ ገሃድ ሴራ ለመፈጸም ደፋ ቀና እያሉ ነው። የወልቃይት እና ሁመራ ጉዳይ ኢትዮጵያን የማስገንጠል ጉዳይ መሆኑ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ሊረዳው ይገባል።