Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ወልቃይት ሬድዋን ሁሴን ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት የሚመራው ተራ ፋይል አይደለም፣

Post by Ejersa » 03 Jan 2023, 06:12

ወልቃይት ፌዛንት አይደለችም፣ መንፈቅ ትግሬ፣ መንፈቅ ጎንደሬ ልትሆን አትችልም፣ [በነገራችን ላይ "ፌዛንት" የምትባል ደሴት የምትገኝው ስፔንና ፈረንሳይን በሚለየው በዳሶዋ ወንዝ ላይ ነው፣ ደሴቷ ከወንዙ መሀል በመገኝቷና አወዛጋቡ በመሆኗ ስድስት ወር ፈረንሳይ፣ ስድስት ወር ስፔን ያስተዳድሯታል]፣

ወልቃይት አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ሲዳማ....የወደዳትና የመረጣት ሊኖርባት የሚችል የህዝቦች የጋራ መኖሪያ (condominium) እንጂ ሁለት የክልል አስተዳደሮች በጣምራ በአንድ ጊዜ የሚረግጧት territorial condominium አይደለችም፣ ልትሆንም አትችልም፣

ወልቃይት የግጦሽ መሬት አይደለም፣ የወልቃይት ፋይል ሬድዋን ሁሴን ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚመራው ተራ ፋይል አይደለም፣

የወልቃይትን ጥያቄ የግዛት ወይም የርስት ማስመለስ ጥያቄ አይደለም፣ የተደረገው ፀረ ቅኝ ግዛት ትግል ነው፣ ከቅኝ ግዛት የከፋ፣ የዘር ማፅዳት፣ የዘር ማጥፋት ያስተናገደ አስከፊ ኩነት ነው፣ በዘግናኝነቱ ታሪክ ዝንተ አለም የሚያነሳው፣ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሊደገም አይደለም ሊታሰብ የማይገባ ወንጀል ነው፣

ብዙ የቅኝ ግዛት ታሪኮችን ሰምቻለሁ (አንብቢያለሁ)፣ ቅኝ ገዥዋች በትምህርት ቤት እና በህዝባዊ መገልገያ ቦታዋች ህዝቡ ቋንቋቸውን እንዳይጠቀሙ ይከለክሉ እንደነበር ተነግሯል፣ ሰዎች መንገድ ላይ ጭምር ቋንቋቸውን እንዳይጠቀሙ የከለከለ ቅኝ ገዥ መኖሩን ግን አልሰማሁም፣ ቅኝ ተገዥዋች የሚሰሙትን ዘፈን የመረጠ ቅኝ ገዥ መኖሩን አላውቅም፣ ወያኔ ግን አድርጎታል፣

ወልቃይት ውስጥ ተደረገ እየተባለ ሲነገር sensationalize ለማድረግ ቅመም ጣል የሚያደርጉበት ይመስለኝ ነበር፣ ምንም አይነት motive የሌላቸውን የወልቃት ተወላጆችን በግሌ አናግሬ ሳበቃ "መች በበቂ ደረጃ ተነገረና!" ማለቴንም አልደብቃችሁም፣

የወልቃይት ጉዳይ ውስብስብ ነው፣ በብዙ መልኩ የተለየ ነው፣ ለዛም ነው ኮሎኔል ደመቀን ጠርተው የወልቃይትን ፋይል ከመተከል ፋይል ጋር ደርበው ሲሉት ዘይትና ዉሀ አይቀላቀልም ብሎ የመለሰላቸው፣

[በነገራችን ላይ የወልቃይ ጉዳይ ትኩረት ያገኝውና ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን በአጋርነት ማሰለፍ የቻለው የራሱ narrative ስለነበረው ነው፣ የወልቃይት narrative ከሀገሪቷ grand political narrative ጋር የተቃኝ ነው፣ ጥያቄው "የወልቃይት የአማራ #ማንነት" ጥያቄ ነው፣ የሀገሪቷ grand narrative ደግሞ የማንነት narrative ነው፣ የማንነት ፖለቲካ ነው፣ "ርስት" የሚሉት ነገር አሁን ነው የመጣው፣ መተከል ይገባናል የሚሉ ሰዎች ናቸው የበረዙት፣ አሁንም ቢሆን የወልቃይት ጉዳይ የሰው (የህዝብ) ጉዳይ ነው፣ የማንነት ጥያቄ ነው፣ መሬቱ በdefault የሚመጣ ተሳቢ እንጂ ቀዳሚ (ተራኪ) አይደለም]

እኔ የኢትዮጵያ ብሔርተኛ ነኝ፣ ይህ መሬት የዚህ ብሔር ነው ማለት አልችልም፣ አልፈልግም፣ የፖለቲካ እምነቴ አይፈቅድልኝም፣ ከወልቃይት ጥያቄ ጎን ያሰለፈኝ ህዝቡ ላይ የተፈፀመው ግፍ ነው፣
የወልቃይት የማንነት ጥያቄ እና ትግል ራሱን የቻለ አንድ የታሪክ ምዕራፍ ነው፣ ታሪክ ዕልባት አድርጎበታል፣ መራር ትግል ጠይቋል፣ በደም ተፅፏል፣ በመሰዋትነት አሸብርቋል፣ የወልቃይት ትግል የወያኔን ወንበር የነቀነቀ በመጨረሻም የከነበለ ትግል ነው፣ ይህ የጎንደር፣ የአማራ፣ የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ ነው፣

የወልቃይት ጥያቄ ተመልሷል፣ የወልቃይት ጉዳይ ተመልሶ ሊነሳ የሚችለው በመላው ኢትዮጵያ አዲስ የአስተዳደር ወሰን ሲተገበር ነው፣ ህዝበ ውሳኔ (referendum) ካስፈለገ ሊደረግ የሚችለው ከ30 ዓመት በኋላ ነው፣ የዛኔ ነገሮች neutralize ስለሚሆኑ ፍትሀዊ ህዝበ ውሳኔ ሊደረግ ይችላል፣

ወልቃይትን በተመለከተ ልንወያይበት የሚገባው የአካባቢያዊ አስተዳደርን (local administration) በተመለከተ ነው፣ እዚህ ላይ መወያየት ተገቢ ነው፣ እኔ እንደ አንድ የኢትዬጵያ ብሔርተኛ የወልቃይት መስተዳድር የስራ ቋንቋ አማርኛና ትግርኛ እንዲሄን እፈልጋለሁ፣ አንድ ራሱን በትግሬነት የሚገልፅ የወልቃይት ነዋሪ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቱ ሳይሸራረፍ፣ ከአማራው ሳይንስ ወልቃይት ውስጥ እንዲኖር እታገላለሁ፣ ህዝቡ አምኖትና ወዶት እስከመረጠው ድረስ አንድ የወልቃይት ነዋሪ ትግሬ የክልሉ ምክር ቤት ውስጥ በትግረኛ ሀሳቡን ሲያስረዳ ማየት እመኛለሁይህ ሁሉ አማራው በሌላው የሀገራችን ክፍል የተነፈገው መብት ነው፣ ሌላውን ህዝብ ግን እይነፍግም፣

የወልቃይት ህዝብ በማያሻማ መልኩ ተናግሯል፣ ከትግራይ የሚመጣ ጥሩ ጎረቤት እንጂ ከአደዋ የሚመደብ የምስለኔ አስተዳደር አንፈልግም ብሏል፣

Ohad Benami - ኦሃድ ቤንዓሚ

pushkin
Member+
Posts: 9690
Joined: 23 Jul 2015, 06:10

Re: ወልቃይት ሬድዋን ሁሴን ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት የሚመራው ተራ ፋይል አይደለም፣

Post by pushkin » 03 Jan 2023, 09:39

Ejersa wrote:
03 Jan 2023, 06:12

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: ወልቃይት ሬድዋን ሁሴን ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት የሚመራው ተራ ፋይል አይደለም፣

Post by Sam Ebalalehu » 03 Jan 2023, 11:20

ይህ አጭር ፅሁፍ እስከዛሬ ስለወልቃይት ተፅፎ ካነበብኩት ለየት ያለ ይዘት አለው። ወድጄዋለሁ። በተለይ የመጨረሻው ሁለት አረፉተነገሮች የወደፊቱን ተንባይ ናቸው ባይ ነኝ።

Post Reply