የኢሶዴፓ ም/ፕረዚዳንትና የኢትዮጲያ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ህብረትን ሊቀመንበር ዶ/ር ራሄል ባፌ የሻቢያ ፍቅር ካለብሽ በአፋር በኩል መመላለስ ትችያለሽ
Posted: 02 Jan 2023, 09:49
By Ethiopia Hagere (Facebook page)
ራሄል ባፌ : የትግራይን ኢትዮጲያዊነት ባትቀበዪ እንኳን የሻቢያ ፍቅር ካለብሽ በአፋር በኩል መመላለስ ትችያለሽ!!!
አቶ ሬድዋን ሁሴን ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ የሰላም ስምምነቱን አስመልክቶ ማብራሪያ አቅርበዋል። ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችም ጥያቄ ተነስቶላቸዋል።
ጥያቄ ካነሱት መካከል የፖለቲካ ፓርቲዎች ህብረትን የሚመሩት ዶክተር ራሄል ባፌ አንዷ ናቸው። ዶክተር ራሄል በስብሰባው ባነሱት ጥያቄ እና በተሰጣቸው መልስ ዙሪያ ዛሬ ለመሳይ መኮንን ቃለመጠይቅ ሰጥተዋል። ባነሱት ጥያቄ ማፈር እና አንገታቸውን መድፋት ሲገባቸው ጭራሽ ጥያቄዬ አልተመለሰልኝም ብለዋል።
በወቅቱ ያነሱት እና ዛሬው አስረግጠው የደገሙት እጅግ አሳፋሪው ሀሳባቸው የሚከተለው ነው :-
"ወልቃይትን ለትግራይ መስጠት ሀገሪቷን ከኤርትራ እና ከሱዳን ጋር እንዳትገናኝ ማድረግ ስለሆነ ጉዳዩ የአማራ እና የትግራይ ክልል ሳይሆን የመላው ኢትዮጲያውያን የድንበር ጉዳይ ነው" የሚል ነው።
እቺ ሴት ስሟ ላይ ዶክተር የሚል ተቀፅላ ያላት፣ የኢትዮጲያ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ህብረትን በሊቀመንበርነት የምትመራ እንዲሁም የአንድ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ምክትል የሆነች "ፖለቲከኛ" ነኝ ብላ የምታስብ ነች።
በጥያቄ መልክ የሰነዘረችው ሀሳብ የመጀመሪያ እና ትልቁ ስህተት (እኔ ወንጀል እለዋለው) ትግራይን ከኢትዮጲያዊነት ፍቆ የጣለ ሀሳብ መሆኑ ነው። ወልቃይት የትግራይ ስትሆን ኢትዮጲያ ከኤርትራ እና ከሱዳን የምትገናኝበት ድንበር አይኖራትም ብሎ ለመደምደም መጀመሪያ "ትግራይ የኢትዮጲያ አካል አይደለችም" ብሎ መደምደም የግድ ይላል።
እቺ ሴቲዮ በአደባባይ ይሄን ድምዳሜዋን ለመግለፅ የደፈረችው የትግራይ ኢትዮጲያ አለመሆንን ደምድማ በመጨረሷ ነው። የአንድን ህዝብ በጅምላ ኢትዮጲያዊነት መካድ ደግሞ ስህተት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ጭምር ነው።
ሁለተኛው ስህተት ደግሞ "ትግራይ ኢትዮጲያ አይደለችም" የሚለውን ብትደመድም እንኳን ወልቃይት የትግራይ በመሆኗ ኢትዮጲያን ከኤርትራም ሆነ ከሱዳን ከመገናኘት አያግዳትም። ሴትዮዋ የሻቢያ ፍቅር ካስጨነቃት ፍቅሯ እስኪወጣላት በአፋር በኩል መመላለስ ትችላለች።
ወደ ሱዳን ማቅናት ከፈለገችም ከወልቃይት በመለስ በሺ ኪሎሜትሮች የተዘረጋ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር አለላት። ከዚህ ውጪ ኢትዮጲያ ኢትዮጲያ የምትባለው የአማራ ክልል ከኤርትራ ጋር ሲዋሰን ብቻ ነው የሚል አቋም ካላት ደግሞ ከኤርትራ ብቻ ሳይሆን ከጅቡቲ፣ ከሱማሊያ እና ከኬንያ ጋር ከሚዋሰኑት ክልሎችም ርስት እየቆረሰች ለአማራ ክልል ማስረከብ ሊኖርባት ነው።
ይሄን ለማድረግ ደግሞ ፓርቲዋ መንግስት እስኪሆን በትንሹ 200 አመት ካልታገሰች በቀር ዛሬ ላይ መላው ኢትዮጲያውያን የጋራ አጀንዳቸው የሚያደርጉላት አይመስለኝም።
ፓርቲዋ ለመንግስትነት ሲበቃ (የሚበቃ ከሆነ) ዛሬ እንዳለችው የአንድ ብሄርን የርስት ጥያቄ የመላው ኢትዮጲያውያን ጥያቄ ማድረግ ትችላለች። ለጊዜው ግን የመላው ኢትዮጲያውያን የጋራ ጉዳይ በገዢውም ሆነ በተቃዋሚውም ጎራ የተሰገሰጉ እንደሷ አይነቶቹ ፖለቲከኞች እንዴት ከጫንቃችን ላይ ይውረዱልን የሚለው ነው።
እነዚህ ስህተቶች ተነቅሰው የወጡት ሀሳቧን ከላይ ከላይ በማየት እንጂ በመሰረታዊ የሀገሪቷም ሆነ አለም አቀፍ ህጎች ቢመዘን የሴቲዪቷን አሳፋሪነት የበለጠ አጉልቶ ማሳየት ይቻላል። የፅሁፉ አላማ የወልቃይትን ጉዳይ ከህግ፣ ከህዝብ ወይ ከታሪክ አንፃር ማየት ባለመሆኑ አልፈዋለው።

Please wait, video is loading...