Page 1 of 1
የትግራይ ተወላጆች ብሶት - “አሁን እየመራ ያለው ሌባ ነው”
Posted: 01 Jan 2023, 14:16
by Selam/
Listen to the first speaker in particular. He is spot on!
Re: የትግራይ ተወላጆች ብሶት - “አሁን እየመራ ያለው ሌባ ነው”
Posted: 01 Jan 2023, 14:45
by Selam/
በጣም የተመቸኝ ውይይት ነው።
የትግራይ ተወላጆች የችግሩ ገፈት ቀማሾች ስለነበሩ፣ እውነቱን ፍርጥርጥ አድርገው ነው የተናገሩት። መንግስት የተቃወሙትን ሁሉ ስም ከማውጣትና ከማሰር ይልቅ፣ ልበ-ሰፊ ሆኖ የህዝብን ብሶት ማዳመጥ ቢችል፣ በተመሳሳይ በቀበሌና ክፍለ-ከተማ ውይይት ቢደረግ ሀገር ከመፍረስ ትድናለች የሰው ዕልቂትም ይቆማል። ችግሩ፣ መንግስት በፅንፈኞች ፣ ሆዳም ስናዳሪዎችና አናሳ ተረኞች የተሞላ ስለሆነ፣ ጆሯቸውን ደፍነው ወደ ገደል ይዘውን መሄድ ይመርጣሉ። ማስገደድና እምቢተኝነት የሚባለው አማራጭ የሚመጣው ይሄኔ ነው።
ኳሷ ያለችው መንግስት እጅ ነው። ማስመሰሉ፣ ማጭበርበሩ፣ ምናባክ ታመጣለህ የሚባል ድፍን የተረኛነት አፀያፊ አስተሳሰብ ይቁም!