እንደ ዐብይ አህመድ ዐይነት ዝቅተኛ አእምሮ ባለው ሰው መመራት ለኢትዮጵያዊያን ስድብ ነው።
Posted: 01 Jan 2023, 11:32
እንደ ዐብይ አህመድ ዐይነት ዝቅተኛ አእምሮ ባለው ሰው መመራት ለኢትዮጵያዊያን ስድብ ነው።ይህን ማለት ድፍረት ወይም ስህተት መስሎ የሚታያቸው በዘልማድ ንጉስ አይከሰስም ሰማይ አይታረስም ብለው ለሚሰግዱ አይጥማቸውም። ግን ለምን ብሎ መጠየቅ አግባብ ነው - ከሜዳ ብድግ ብሎ ሰውን መንቀፍ ስህተት ስለሚምስል። ዐብይ የመሪነት ብቃት የሌለው መሆኑን በየወሩ ሳይሆን በየሳምንታቱ አሳይቷል። መምራት የማይችለው ጴንጤ ወይም ሙስሊም ስለሆነ ፤ኦሮሞ ወይም ቅይጥ ስለሆነ አይደለም። መምራት የማይችለው ለመሪነት የሚያበቃ የአእምሮ ጸጋ ስለሌለው ነው። የአእምሮ ጸጋ የለውም ማለት ጨርቁን የቀደደ ዕብድ ነው ማለት አይደለም። ያደረሳቸው የሚያሳያቸው፤የሚያሰባቸው ጥፋቶች ጨርቁን ከቀደደ ዕብድ በላይ ነው።የእዚህ ሰው ቋሚ የፓለቲካ ዕብደት መሪ ሃሳብ ጥፋት እና ግጭት ብቻ ነው። ለዚህ ዘላቂ የጥፋት አላማ በየዕለቱ ተለዋዋጭ አድርባይ የዕብደት መንገዶች ይከተላል። ሁል ጊዜ በዘላቂነት ማታለል ውሎ የሚያድር ይመስለዋል። ይህ የህሌና ድዊነት ነው። መልካም ስራ እና ብሩህ አእምሮ የቀና የስኬት ፍኖት ላይ ይጥላል። ጠማማነት የህሌና በሽታ ነው - ሊቀና እና ሊስተካከል የሚችል ደዌ አይደለም።