Page 1 of 1

ኤርትራን መንካ እንደማይታሰብ ኢትዮጵያ አስታወቀች፣ “ውለታን መርሳት ነውር ነው”

Posted: 01 Jan 2023, 11:10
by Zmeselo


ኤርትራን መንካ እንደማይታሰብ ኢትዮጵያ አስታወቀች፣ “ውለታን መርሳት ነውር ነው”

https://ethio12.com/2023/01/01/2309-164/

JANUARY 1, 2023


ውለታን መርሳት ነውር ነው
በሚል የመንግስት ቁርጥ ያለ አቋም የተገለጸው “ተቃዋሚ” ፓርቲዎችን በመሰብሰብ
የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ ለምን አይወጡም
በሚል ተደራራቢ ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ነው።
በሦስተኛው ዙር አገሪቱን ለመጨረሻ ጊዜ ለማፍረስ በተካሄደው ጦርነት
አሉ አቶ ሬድዋን
የፌዴራል መንግሥት በቆቦ በኩል ባለው ዳገት ወደ ላይ መውጣት ስላዳገተው፣ ትህነግ ያለውን መልክዓ ምድራዊ ጠቀሜታ ተጠቅሞ ቆቦን ተቆጣጥሮ ነበር
ሲሉ ኤርትራን እንደ ጠላት በማየት ጥያቄ ላቀረቡት ምስላዊ ማብራሪያ ሰጡ።

ይህ ሲሆን ወቅቱ ክረምት መሆኑ ችግሩን እንዳባባሰው ካስታወሱ በሁዋላ
በዝናብ ምክንያት በምዕራብ በኩል ተከዜን የኢትዮጵያ ሰራዊት ማቋረጥ ባለመቻሉ፣ አቅጣጫ ቀይሮ ያለስጋት በዛላምበሳና በአዲግራት በኩል ተከዜን እንዲሻገር የኤርትራ መንግሥት በመፍቀዱ ጦርነቱ ሊቀለበስ ችሏል
ሲሉ ኤርትራ ክህደት ተፍጽሞበት የታረደውን የኢትዮጵያ አለኝታ ሰራዊት ተቀብላ ከማስተናገዷ በተጨማሪ ያበረከተችውን የማይረሳ አስተዋጾ ገለጹ።

ኤርትራ ባትተባበር ኖሮ ምን ሊፈጠር ይችል እንደነበር ሲገልጹ
ለአጭር ጊዜም ቢሆን በራቸውን ባይፈቅዱልን ኖሮ ይኼንን ጦርነት መቀልበስ አይቻልም ነበር፡፡ እንደ አገር ከባድ ፈተና ውስጥ እንወድቅ ነበር
በማለት
ውለታ መርሳት ነውር ነው
ያሉበትን አንድ ምክንያት ገልጸዋል።

ይህንኑ አሳብ በወታደራዊ ቋንቋ ሌተና ጀነራል ባጫ ደበሌ
በቆቦ በኩል ወደፊት የሚገፋ እብድ የለም። ከተፈጥሮ ጋር ውጊያ አይታሰብም። በሌላ አቅጣጫ እናስኬደዋለን
ማለታቸው ይታወሳል።

የጠቅላይ ሚንስትር አብይ የደህንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን መንግስት ኤርትራ ላይ የያዘውን አቋምና የአቋሙን አግባብነት የሚያሳይ ማብራሪያ ከሰጡ በሁዋላ፣
የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ ይውጣ የሚሉት አካላት ለኢትዮጵያ አዝነው አይደለም
ሲሉ ወቅሰዋል።

ወቀሳቸውን ሲያጠናክሩ
ኤርትራ ትውጣ የሚሉ አካላት ሱዳን 50 ኪሎ ሜትር አልፎ ድንበር ወሮ በነበረበት ወቅት አፋቸውን ዘግተው ነበር
ሲሉ ስለ ብሄራዊ ጥቅምና አገር መውደድ የሚገለባበጠውን የአንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አቋም ለማሳየት ሞክረዋል።

ከሃምሳ በላይ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች በተገኙበት ስለ ሰላም አተገባበርና አካሄድ መረጃ ለመስጠት በተካሄደ ውይይት ላይ “ኤርትራ ትውጣ” በሚል ለተነሳው ጥያቄ አቶ ሬድዋን መልሳቸው ከላይ በተገለጸው ምክንያት ብቻ አልቆሙም። ግብጽን አንስተው የትርምስ ገመዱንና እቅዱን በምሳየት
ይህ ሁሉ ሲሆን የት ነበራችሁ?
ሲሉ ሞግተዋቸዋል።
… ግብፅ በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ መድባ ለጋምቤላ፣ ለኦነግ ሸኔና ለትህነግ ጭምር በአየርና መሬት ወደ ኢትዮጵያ መሳሪያ እያስገባች ስታስታጥቅ፣ ተቃዋሚዎቹ ፓርቲዎች ምንም አላላችሁም
ሲሉ ፈትነዋቸዋል።

አክለውም
ይህ [የተቃዋሚዎች አቋም] የሚያሳየው እንቅስቃሴው መንግሥትን የሚያዳክም ሲሆን ዝምታ፣ መንግሥትን የሚያግዝ ሲሆን ደግሞ ጩኸት ማብዛት የሚወዱ በመኖራቸው ነው
ሲሉ የሁከቱና የመንግስት መዳከምን መሰረት አድርገው እንደሚንቀሳቀሱ ነግረዋቸዋል።

ሬድዋን
ኤርትራ እኛን አስቸገረን ካላልን ምን አሳሰባቸው?
ሲሉ ጠይቀው፣
ኤርትራ ባስቸገረን ጊዜ እኛ ራሳችን በቃን እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ካሳሰባችሁ ሱዳን ትውጣ ብላችሁ መግለጫ አውጡ
ሲሉ መንግስትና ኤርትራ ተናበው እንደሚሰሩ፣ ይህ የማይናወጥ አብሮነት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

ፍትሃዊ አቋም ማራመድ ሲጀመር
ኤርትራ ትውጣ ብትሉ እኛ መረዳት እችላለን
ሲሉ ጉዳዩ ላይ ያለው መነሸዋረር እንዲጠራ አሳስበዋል።

መክረዋል።

ግልጥ ያለውን የመንግስትን አቋም ሲያስታውቁ
በእኛ [በኢትዮጵያ] አስታኮ የኤርትራ መንግሥትን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም፡፡ ቢያንስ ከተፈጠረው የሰላም ስምምነት አንፃር እኛ እንዳንፈርስ አግዘውናል
ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ትህነግ መንግስትንና ኤርትራን ለማጣላት ሂሳብ እያሰላ የመንቀሳቀስ ስልት እንደሚከተለ ገልጸን መዘገባችን የሚታወስ ነው። የኤርትራ መንግስት ደግሞ
ትህነግ ስጋት እስከሆነ ድረስ ለደህንነታቸው ሲሉ ከገቡበት ለቀው እንደማይወጡ ሲያስታውቁ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።
አቶ ሬድዋን ይህንኑ የኤርትራን አቋም ግንዛቤ ውስጥ በመክተት፣ ከዛም በላይ በመናበብ እንደሚሰሩ ግልጽ በማድረግ ዲፕሎማሲያዊ ሃረግ አክለዋል።
የጋራ ጠላት የነበረን ቢሆንም
አሉ የደህንነት አማካሪው፣
ትጥቁን የፈታ የትህነግ ታጣቂ ግን ኢትዮጵያዊ ነው
ሲሉ ትህነግ ካልታጠቀ ስጋት እንደማይሆን አስታውቀዋል።

ትጥቅ መፍታቱ ኤርትራናም ሆነ በትግራይ ዙሪያ ያሉትን ወገኖች ሰላም እንደሚሰጥ ከስምምነቱ በሁዋላ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር። በዚሁ ማዕቀፍ ውስጥ ሆነው
… ስለዚህ አቅማችን ባለበት እስኪጠናከር ትህነግ መጀመሪያ ትጥቁን መፍታት ይጀምርና እንደማንወጋ ስናረጋግጥ፣ ከጀርባችን ያለው አካል ማንም ይሁን ማን ይውጣልን ማለት እንችላለን
ሲሉ አምክንዮ የተሞላው ምላሽ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያና ኤርትራ የደንነትና ወታደራዊ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።

ወልቃይትን አስመልክቶ ከግራና ቀኝ በተዘዋዋሪ መንገድ ለሚነሳው ጥያቄ ምላሽ እንዲሆን ባስበ መልኩ ይመስላል አቶ ሬድዋን የተናገሩት። ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የሱዳን መውጪያ በርም ልክ እንደ አሰብ ሁሉ እንዳይወሰድ በሚኡል ስጋታቸውን ጨምረው ላነሱት
ከጅምሩ የጦርነቱ ዓላማ ወልቃይትን ማስመለስና ትህነግን ማጥፋት አልነበረም
ሲሉ ነው አቶ ሬድዋን ያስታወቁት።

የጦርነቱ ዋና ዓላማ የአገሪቱን ሉዓላዊነት ማስከበርና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ማስፈን እንደነበር አስታውቀው፣
ትህነግን እንደ ፖለቲካ ኃይል የማጥፋት ዓላማ ያለው ሰው ይኖራል፣ ነገር ግን የፌዴራል መንግሥቱ ዓላማ አይደለም
ሲሉ ትህነግን ማቀፍም ሆነ መግፋት የትግራይ ህዝብ ውሳኔ እንጂ የሌሎች አካላት እንዳልሆነ አመልክተዋል።

ከላይ እንደገለጹት ትጥቅ የፈታ ትህነግ ኤትዮጵያዊ ነው።

ወልቃይት በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል ያለ ፀብ በመሆኑ በሁለት ክልሎች መካከል ያለው ፀብ ደግሞ የሚፈታው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚመራው ሥርዓት በህግና ህግ ብቻ እንደሆነ አመልክተዋል። የፌደራል መንግስት ባለው የህግ አግባብ የህግ ጨዋታውን ገለልተና ሆኖ ማስፈጸም እንጂ ሌላ ተልዕኮ ሊኖረው እንደማይችል ባለሙያዎችም ሲናገሩ ነበር።
የፌዴራል መንግሥትን አቅም ተራ በተራ ጡንቻ እየተፈታተን አንዳችን ሌላችንን ማንበርከክ ይቁም
ሲሉ ጉልበት መፍትሄ እንደማያመጣና አንዱ ሲደክም ሌላው ሲበረታ፣ የሚገኝ ድል አስተማማኝ እንደማይሆን ገልጸዋል።
ወልቃይትን ከዚህ ቀደም ትህነግ ጡንቻ ስለነበረው በጉልበት ወስዷል
ሲሉ ያልፈውን አካሄድ ፍትሃዊ እንዳልነበር ያወሱት አቶ ሬድዋን፣ ዛሬ ትህነግ ሸብረክ ሲል ጡንቻ ያለው አካል ይውሰድ ካልን መጪው ትውልድ 20 ዓመት ጠብቆ ድንገት ጡንቻ ካገኘ ዳግም ይወስደዋል።
ስለዚህ ዘላቂው መፍትሔ ጡንቻ ሳይሆን ሕግና ሥርዓት ነው
ሲሉ ጉዳዩ በህግ አግባብ መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባ ይፋ አድርገዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኤርትራ ወታደሮች ከሽሬና አክሱም ለቀው ድንበር ወደ ራሳቸው ድንበር መጠጋታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ሮይተርስ ከአቶ ጌታቸው ማረጋግጫ እንዳላገኘ፣ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ተጠይቀው ማረጋገጫም ሆነ ማስተማመኛ እንዳልሰጡት ያስታወቀው፣ ነገር ግን ዕርዳታ ሰራተኞች እንደነገሩት ገልጾ ሮይተርስ ምስክርነቱን ሰጥቷል።

የትህነግ ታጣቂዎች መሳሪያቸውን ባስረከቡ መጠንና ለማናቸውም የአግወሪቱም ይሁን የጎረቤት መንደሮች ስጋት መሆናቸው በተመናመነ ቁጥር ኤርትራ ወታደሮቿን እንድትስብ ከመንግስት ጋር በስምምነት እንደሚሰራ ግለጸን መዘገባችን ይታወሳል። በዚህ ዜናችን የኤርትራና ኢትዮጵያ ወታደሮች ሰላማታ በመቀያየር ምሽግ መረካከባቸውን ነበር የገለጽነው። አቶ ሬድዋን እንዳሉት
የእኛ ወገን የምንላቸው የሕወሓት ሰዎች ለ30 ዓመታት ታገልኩለት ያሉትን ሕዝብ ለ30 ዓመታት እየቀለበ፣ እየጠበቀ፣ አብሮ እየሠራና እያረሰ የኖረውን ሠራዊት ከጀርባው አርደው ሜዳ ላይ ሲጥሉት የታደጉት እነዚህ ሰዎች ናቸው፡፡ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ውለታን መርሳት ነውር ነው
ሲሉ አቶ ሬድዋን ኤርትራ ላይ እጃቸውን ለሚቀስሩ ማሳረጊያ ሰጥተዋል።

ከሰላም ስምምነቱ ዜና ደስታና ፈንጠዝያ ጎን ለጎን
መላከላከያን ያረዱ፣ ያሳረዱና የተባበሩ ላይ ፍትህ ሊበየን ይገባል
የሚሉ ድምጾች የተሰሙትም ለዚሁ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ በትግራይ፣ በአፋርና አማራ እንዲሁም በተዘዋዋሪ በሌሎች አካባቢዎች በንጹሃን ላይ ጭፍጨፋ የፈጸሙና ያስፈጸሙ፣ የህዝብ ንብረትና ማህበራዊ መገልገያዎችን ያወደሙ፣ የጅምላ ግድያ ያስፈጸሙ ወዘተ ላይ ብሄር፣ ሰፈር፣ ቋንቋና ማንነት ሳይለይ ህግ እንዲጸናባቸው ፍትህ ወዳ ዜጎች እየጠየቁ ነው።

ድንገት ወደ መቀለ ባመራው የመንግስት ልዑክ ውስጥ የፍትህ ሚኒስትሩና የእርቅ ኮሚሽን አባላት መካከታታቸው በህግ ተጠያቂነት አግባብ ከትህነግ አመራሮች ጋር ለመነጋገር እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች እየገለጹ ነው።

በዜናው የተጠቀሱት አቶ ሬድዋን ያተናገሩት ከሪፖርተር ቃል በቃለ የተወሰደ ነው።

Re: ኤርትራን መንካ እንደማይታሰብ ኢትዮጵያ አስታወቀች፣ “ውለታን መርሳት ነውር ነው”

Posted: 01 Jan 2023, 11:27
by Zmeselo



Greetings, Eritreans!

I want to make it known to you, that the history just written with the blood sacrifice of the honourable Eritrean Defence Forces is something that will always have a special place in the hearts of Ethiopians & that it has laid the foundation to a higher level of brotherhood.

History that I never thought I'd experience in my lifetime, has just been made. Going forward, until that day that all Ethiopians will remember & honor it and until we place a memorial worthy of it, I as an individual Ethiopian would like to say: thank you.

And I'd like to clarify too that this isn't just my personal wish, but all Ethiopians'.

Happy New Year!

Ohad Benami
Addis Ababa
Ethiopia.

Re: ኤርትራን መንካ እንደማይታሰብ ኢትዮጵያ አስታወቀች፣ “ውለታን መርሳት ነውር ነው”

Posted: 01 Jan 2023, 11:45
by sarcasm

Re: ኤርትራን መንካ እንደማይታሰብ ኢትዮጵያ አስታወቀች፣ “ውለታን መርሳት ነውር ነው”

Posted: 01 Jan 2023, 12:16
by Weyane.is.dead
Vermin, stop polluting this thread with your low iq posts.
rodent wrote:
01 Jan 2023, 11:45

Re: ኤርትራን መንካ እንደማይታሰብ ኢትዮጵያ አስታወቀች፣ “ውለታን መርሳት ነውር ነው”

Posted: 01 Jan 2023, 12:53
by Zmeselo



Re: ኤርትራን መንካ እንደማይታሰብ ኢትዮጵያ አስታወቀች፣ “ውለታን መርሳት ነውር ነው”

Posted: 01 Jan 2023, 13:02
by Zmeselo




Re: ኤርትራን መንካ እንደማይታሰብ ኢትዮጵያ አስታወቀች፣ “ውለታን መርሳት ነውር ነው”

Posted: 01 Jan 2023, 13:22
by Union
That is right. It is on the land of mighty Amara!

Re: ኤርትራን መንካ እንደማይታሰብ ኢትዮጵያ አስታወቀች፣ “ውለታን መርሳት ነውር ነው”

Posted: 01 Jan 2023, 13:57
by Digital Weyane
ለጁንታ ዎገኖቼ ውለታን መርሳትና መካድ ባህላዊ ጨዋታቸው ነው። ክህደትን እንደ ትልቅ ጀብዱ ይቆጥሩታል። የገዛ ኡናቶቻቸውን ለሆዳቸው ሲሉ ይሸጣሉ። ትግራዋይ ተብዬ ከነሱ ጋር በመቆጠሬ አፍራለሁ። :roll: :roll:

Re: ኤርትራን መንካ እንደማይታሰብ ኢትዮጵያ አስታወቀች፣ “ውለታን መርሳት ነውር ነው”

Posted: 03 Jan 2023, 04:04
by Meleket
Ohad Benami ሰላምታው ደርሶናል፡ ምስጋናውንም ተቀብለናል። ትግርኛህንም ወደነዋል። :mrgreen:

ወዳጃችን Ohad Benami "ፊዚካል ዲማርኬሽን" ከተደረገ እኮ፡ እያልክ ያለሀው ለዘመናት ሊታወስ የሚገባው ሓውልት ተሰራ ማለት ነው፡ ያውም 146 ቦታዎች ላይ። ስለሆነም የኛ የኤርትራውያን ምንም ዝንፍ የማይለው ኣቋማችን፡-

"ኢትዮጵያውያን ጎረቤቶቻችን ሆይ ፍቅራችንን ከልብ የምትፈልጉ ከሆነ፡ በርካታ ዜጎቻችን የተሰውበትን ዓላማ ዳሩ ላይ ኣድርሱልን፤ በፍቅር ስሜትም "ፊዚካል ዲማርኬሽን" ኣሁኑኑ ተግባር ላይ ይውል ዘንድ የበኩላችሁን በጎ ሚና ኣበርክቱ የሚል ነው። :mrgreen:

https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=308857& የኤርትራ እና የኢትዮጵያ 146ቱ የጋራ ፈርጦች!

https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=308353& ይድረስ ተኢትዮጵያው ጠቅላዪ ኣብዪና ተህወሓቱ ደብረጽዮን እንዲሁም ተመላው የኢትዮጵያ ህዝብና የመንግስት አካላት


Zmeselo wrote:
01 Jan 2023, 11:27



Greetings, Eritreans!

I want to make it known to you, that the history just written with the blood sacrifice of the honourable Eritrean Defence Forces is something that will always have a special place in the hearts of Ethiopians & that it has laid the foundation to a higher level of brotherhood.

History that I never thought I'd experience in my lifetime, has just been made. Going forward, until that day that all Ethiopians will remember & honor it and until we place a memorial worthy of it, I as an individual Ethiopian would like to say: thank you.

And I'd like to clarify too that this isn't just my personal wish, but all Ethiopians'.

Happy New Year!

Ohad Benami
Addis Ababa
Ethiopia.
"146ቱ የጋራ ፈርጦቻችን የዘላቂ ሰላማችን ዋስትኖችም ቋሚ ሓወልቶችም ናቸው!" ቢለናል እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር። :mrgreen: