ወልቃይት ጸገዴ ሁመራና ራያ በሚመለከት ከየሳሕራዊ ( ስፓኒሽ ሰሃራ ) የረፈረንደም ሙከራ ምን ለመማር ይቻላል ?
Posted: 31 Dec 2022, 14:48
- ወልቃይት ጸገዴ ሁመራና ራያ በሚመለከት ከየሳሕራዊ ( ስፓኒሽ ሰሃራ ) የረፈረንደም ሙከራ ምን ለመማር ይቻላል ?
ስፓኒሽ ሰሃራ የሚባለው ኣገር በየኮሎኒያሊዝም ጊዜ በየእስጳኝ ቁጥጥር ስር ቆይቶ እስጳኞቹ ትተዉት ሲሄዱ ሞሮኮ ኣንድ ሚልዮን ሰዎችን ያቀፈውን የኣረንጓዴ ጉዞ ኣዘጋጅታ ቦታውን የራስዋን ኣካል ልታደርገው ቻለች ። የሳሕራዊ ሰዎች የተፈጠረውን ኣዲስ ሁኔታ ስላልተቀበሉ ለነጻነት ትጥቃዊ ትግላቸው ጀመሩ ።
ትግሉ እየሞቀና እየቀዘቀዘ ለብዙ ዓመታት ሲቀጥል መፍትሄ ይሆናል ተብሎ ለቀረበውን የረፈረንደም ሃሳብ ሞሮኮና የፖሊሳርዮ ( ሳሕራዊ ) ታጋዮች ቢቀበሉትም በኣተገባበሩ ኣለመረዳዳት ስለ ተፈጠረ የታሰበውን ጋህድ ሊሆን ኣልቻለም ። ለምን ?
ረፈረንደሙ ይደረጋል ተብሎ በሂደቱ ማን ነው የሚሳተፈው የሚል ቃል በተነሳበት ወቅት ሞሮኮ በመሬትዋ ለሚገኙና እስዋ ከምድረ-ሳሕራዊ የረጅም ጊዜ ግኑኝነት ኣላቸው ብላ የምታምን በዛ ያሉ ሰዎች በመዝገብ ኣስፍራ ስላቀረበች ፖሊሳርዮ የሞሮኮን ኣቀራረብ ሌብነት ያዘለ ነው ስላለች የህዝበ-ውሳኔ ጉዳይ ሳይጀምር ተቋረጠ ።
በተመሳሳይ በሚመስለው በዋልቃይት ጸገዴ ሁመራና ራያ የቲዲኤፍ ቅሪቶችን ኣስፍሮ በማታለል ኣማራን ርስቱን የመንጠቅ ሙከራ ኣለ ። ኣንገብጋቢ ጥያቄው ኣማራ በቁሙ ሊጫወቱበት ለሚያስቡ ሌቦችን ገጥሞ የማክሸፍ ዝግጁነት ኣለው ወይ የሚል ነው ።
ኣል-ማሲራ ኣል-ኸድራእ ( The Green March )


