Page 1 of 1

አጭር ስንኝ ለቴዲ ዮ!

Posted: 31 Dec 2022, 00:48
by Horus
ብርቃችን አይደለም
ሰላም ብለን እንጂ ትግስት ሚገዛን፣
ፍቅር ብለን እንጂ ዝምታ ሚገዛን፣
ቆመን እናውቃለን ግፈኛን ተቃውመን፣
ለጭቁን ተሟግተን ጨቋኝን ተዋግተን፤
ብርቃችን አይደለም ለፍትህ መታሰር ቆሞ ለመብታችን፣
በቃላችን ጸንተን ለነጻነት መሞት አይደለም ብርቃችን።

ሆረስ ኃይለ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ
ዲሴምበር 30 2022 ዓም

....................................