Page 1 of 1

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ ጀምሮ ወደ ሽሬ ከተማ በቀን አንድ በረራ ማድረግ ይጀምራል። ወደ መቐለ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ በቀን ወደ 3 ከፍ ያደርጋል EBC

Posted: 29 Dec 2022, 11:24
by sarcasm
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ ጀምሮ ወደ ሽሬ ከተማ በቀን አንድ በረራ ማድረግ ይጀምራል
***********************


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ (ታኅሣሥ 24 ቀን 2015 ዓ.ም) ጀምሮ ወደ ሽሬ ከተማ በቀን አንድ በረራ ማድረግ እንደሚጀምር ገለጸ።
አየር መንገዱ ወደ መቐለ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ በቀን ወደ ሦስት ከፍ የሚያደርግ መሆኑንም አብስሯል።

በተከታታይም የመንገደኛ ፍላጎት ቁጥርን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን የሚያደርገውን የበረራ ምልልስ ብዛት እንደሚጨምር ገልጿል።

በመሆኑም ደንበኞቹ ባሉበት ቦታ ሆነው ድረ ገጹን እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችንን ተጠቅመው ምዝገባ ማድረግ እና ትኬት መቁረጥ የሚችሉ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል።

Please wait, video is loading...