Page 1 of 1

መሬት ተንቀጥቅጦ .. .. .. [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Posted: 29 Dec 2022, 09:22
by Meleket
መሬት ተንቀጥቅጦ .. .. .. [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]
(የሃዋርያት ስራ 16:26)


ጳውሎስና ሲላስ ቀደምቱ ምስክር፡
በእግዝሄር ተኣምር፡
መሬት ተንቀጥቅጦ እንደወጡ ከእስር፡
የሃዋርያት ስራ ገልጾ ሲዘረዝር . . .

በአፍሪካ ቀንዷ በየዋሆች ሃገር፡
በኣማኞቹ ምድር በጀግኖቹ ሰፈር፡
በነ ፈንቅልና ባባ ጥመር መንደር፡

አሁን በኛ ዘመን፡ በ21ኛው፡
ተደገመ ታሪክ ልክ እንደ ወዲያኛው፡. . .

የሰው ልብ ሊያስቅሩ ሕዝብ ሊያስሸፍቱ፡
እንቶኔ እና እንቶኒት ሴራ ፈተፈቱ፡
በዲያብሎስ 'ምክር' ተንኮል ፈተፈቱ፡
መንፈሳዊ አባትን ድፍን ሁለት ወራት እንትን ውስጥ ከተቱ፡

ወደር ስሌለው አምላክ ቸርነቱ፡
ወሰን ስሌለው የእግዚኣብሔር ምህረቱ፡
መሬት ኣንቀጥቅጦ ልክ በሳልስቱ፡
ኣቡነ ፍቕረና ኣባ ምሕረተኣብ ደምቀው ከበፊቱ፡
ይበልጥ በእምነት ጸንተው አሁን ከበፊቱ፡
በህዝብ እንባና በጸሎት ተፈቱ፡

ይብላኝ ለእንቶኔዎች ነገር ለዶለቱ፡
ነጩን ጥቁር ብለው ደከሙ ለከንቱ። :mrgreen:

አቡነ ፍቅረማርያም ሓጎስ ጳጳስ ዘመንበረ ሠገነይቲ እና ኣባ ምሕረተኣብ እስጢፋኖስ ቆሞስ ቤተ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሚካኤል ሠገነይቲ እንኳን ለዚህ ኣበቃችሁ፡ በማለት መንፈሳዊ ኣባቶቻችን በዕለተ ቅዱስ ገብርኤል በመፈታታቸው ደስ እንዳለን ለመግለጥ ነው፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

ይህን የተወዳጁን የአቡነ ፍቅረማርያም ሓጎስ ፎቶ "የዓመተ 2022 ምርጥ ፎቶ" ብለነው እንደነበር ይታወቃል :mrgreen:


https://www.volcanodiscovery.com/earthq ... iopia.html

https://crisis24.garda.com/alerts/2022/ ... ion-dec-26

"ክብር ለመንፈሳዊ ኣባቶቻችንና እናቶቻችን በሙሉ!" ... "ዘለዓለማዊ ክብርና ምስጋና ለሥላሴ" . . . ታሪክም እማደል እዬጻፍን ያለነው . . . :mrgreen: