Page 1 of 1

ስለአዲስ አበባ ፖሊስ ያየሁት ጉድ ፡ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ

Posted: 29 Dec 2022, 06:30
by Abaymado
አንደኛው ፡ ጦርነቱ በጣም በተፋፋመበት ወቅት እያንዳንዱ ፖሊስ መምሪያ ከየክፍለከተማው ያሉትን ፖሊሶች እንዲያዘምት ታዞ ኢንደነበር ይታወቃል፡፡ እናም ቀላል የማይባሉ ፖሊሶች ጥሪ ይደርሳቸዋል፡፡ መጀመርያ ከደረሳቸው ዋናዎቹ የወላይታ ተወላጆች ነበሩ፡፡ እናም ይህ ጥሪ ሲደርሳቸው ብዙዎቹ አዲስ አበባን ለቀው ወደ አገራቸው ገብተው ተደብቀው ነበር፡፡
አንዳንዶቹ የወላይታ ተወላጆች ከተደበቁበት ሲመለሱ ወደ እስር ቤት ተላልፈው ነበር፡፡ የሚገርመው ወደ ጦር ግንባር እንዲዘምቱ ከተወሰነባቸው የአማራ ተወላጆች ብዙዎቹ መዝምታቸው ነው፡፡ ምንም ሳያመነቱ ወደ ማሰልጠኛ ካምፕ ገብተዋል፡፡ አንዳንዶቹ በአሁኑ ሰአት ሽሬ ላይ እንደሚገኙ ነው የሚነገረው፡፡

ሁለተኛው ፡ አንድ የፖሊስ አባል የአማራ ተወላጅ በፌስ ቡክ ላይ በጻፈው ፖስት ምክንያት ከስራ እንዲታገድ ሆኗል፡፡ ልጁ ፌስ ቡክ ላይ የለጠፈው “ወንድሞቼ እየሞቱ ነው፡ ” የሚል ፖስት ነበር፡፡ ልጁ ያንን ለምን እንደጻፈ አላቅም፡፡ ከዚህ በፊት ከልጁ ጋር ስለ ጦርነቱ ስናወራ “እኔ ትግራይ አለቀች” ስል እሱ በተቃራኒው ነበር የሚያወራው፡፡ እንዴት የመንግስት ወታደሮች እንዳለቁ ነው የሚነግረን፡፡ የሱ አኳሃን ቢገርመኝም ትግሬ መስሎኝ ነበር፡፡

እና ፌስቡክ ላይ የጻፈውን አይተው ፡ ይጠራና ከስራ እንደተገለለ ይነግሩታል፡፡ ይሄ አሁን ምን ይሉታል? መንግስት ከትግሬ ጋር እየተደራደረ ባለበት ሰአት ልጁን ከስራ ማገድ ምን ይሉታል? ሌሎች ፖሊሶችን ለምን ብዬ ስጠይቅ? ሌላ ችግር ሳይኖርበት አይቀርም ተብሎ የታመነ ይመስለናል አሉኝ፡፡ ልጁ ትግሬ ካልሆነ ለምን ብላቸው መልሳቸው እንደገባኝ ከኦሮሞ ጋር ያለው ግጭት ጋርም ሊሆን እንደሚችል ነው የጠረጠርኩት፡፡