Page 1 of 1
በተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና ሬድዋን ሁሴን የተመራ የልዑካን ቡድን የትግራይን ሕዝብ ይቅርታ ለመጠየቅ ዛሬ መቀሌ ገብቷል
Posted: 26 Dec 2022, 08:00
by Thomas H
Re: በተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና ሬድዋን ሁሴን የተመራ የልዑካን ቡድን የትግራይን ሕዝብ ይቅርታ ለመጠየቅ ዛሬ መቀሌ ገብቷል
Posted: 26 Dec 2022, 08:39
by Thomas H
ይቅርታ መጠየቅ ተገቢ ቢሆንም ወንጀለኞች ግን ለፍርድ መቅረብ አለባቸው:: ከዚህ የልዑካን ቡድን ውስጥ እንኳን የተወሰኑት መቀሌ ፍርድ ቤት መቅረብ አለባቸው ባይ ነኝ ::

Re: በተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና ሬድዋን ሁሴን የተመራ የልዑካን ቡድን የትግራይን ሕዝብ ይቅርታ ለመጠየቅ ዛሬ መቀሌ ገብቷል
Posted: 27 Dec 2022, 09:58
by Thomas H
Fasil Yenealem
የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ከደገፉት መካከል ግንባር ቀደሙ ነኝ። ስምምነቱ ዘላቂነት እንዲኖረው፣ በስምምነቱ ውስጥ የተቀመጡት ቀዳሚዎቹ ነጥቦች ማለትም ትጥቅ መፍታትና ትግራይን በመከላከያ ስር ማድረግ ከፖለቲካ ግንኙነት በፊት ተግባራዊ መደረግ ነበረበት ብዬ ግን አምናለሁ። ከዚህ ቀጥሎ የፖለቲካ ግንኙነቱና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ መምጣት ነበረበት። አሁን ከፈረሱ ጋሪው የቀደመ መሰለኝ። ይህ አካሄድ መተማመንን ፈጥሮ ወደ ሰላም ቢወስድ ግን ደስታውን አልችለውም።
ችግራችንን በራሳችን እንፈታለን አደራዳሪዎችም አያስፈልጉም ተብሏል። ጥሩ ነው። ግን አሁን ባለው ዝቅተኛ የመተማመን ደረጃ ይህ የሚሆን አይመስለኝም ።
በፕሮቶኮልም ጉዳይ ቢሆን ህወሃት እንጅ ወደ አዲስ አበባ መምጣት የነበረበት፣ መንግስት አልነበረም ወደ መቀሌ መሄድ የነበረበት። የሃይል ሚዛን ግንኙነቱ "ፖወር ሪሌሽን" በግልጽ መቀመጥ አለበት። አሁን ግን እንደምናየው ህወሓት አሸንፎ፣ መንግስት ደግሞ ይቅርታ አድርጉልኝ ብሎ ለመጠየቅ የሄደ ነው የሚመስለው።
ፖለቲካ እኮ አስገራሚ ሁኔታ (Surprising effect) ለመፍጠር ብለህ የምትሰራው አይደለም። ብዙ ደም ፈሷል። ብዙ ቅያሜዎች ተፈጥረዋል። ቁስሉ እንዲጠግግ ብቻ ሳይሆን፣ ድጋሜ ወደ ግጭት እንዳንገባ፣ ብዙ ሂደቶች በቅደም ተከተል መታለፍ አለባቸው። የመከላከያ ሰራዊቱ፣ ልዩ ሃይሎች፣ ፋኖ፣ የትግራይ አጎራባች ክልል ህዝብ፣ በጦርነቱ የተጎዱ ቤተሰቦች፣ የኤርትራ መንግስትና ሌሎችም በዚህ ሂደት ያለፉት ሁሉ፣ ስለሂደቱ በደንብ ተረድተው፣ አምነው፣ ይቅር ብለውና ተባብለው፣ አዲስ ታሪክ ለማስጀመር መነሳት አለባቸው። አንድ ሚሊዮን ያላነሰ ህዝብ ከሁሉም ወገን ያለቀበትን ጦርነት እንዳልተካሄደ ቆጥረህ፣ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ድራማ መሬት ላይ ያለውን እውነትና ስሜት ልትለውጠው አትችልም። Politics is too serious a matter that needs a serious strategic thinking, not a day to day a PR stunt .
የደቡብ አፍሪካው የእርቅና የሰላም ሂደት ከታለፈ በኋላ እንኳን ዛሬም ድረስ ያልሻሩ ብዙ ቁስሎች ይነሳሉ። ከዚህ አካሄድ ልምድ መውሰድ ይገባል ። በግሌ ማንኛውም የተበደለ ሰው በዳዩን ሰባት ጊዜ ሰባ ይቅር ማለት ይጠቅመዋል እንጅ አይጎዳውም ብለው ከሚያምኑ ወገኖች ነኝ። ግን ደግሞ በገሃዱ ዓለም እንደምኖርም አውቃለሁ።
በነገራችን ላይ ከእነ ደብረጽዮን ጋር ከተገናኘህ በኋላ፣ ፣የህወሓት የበታች ሹሞችን አስሮ ማስቀመጥ ትክክል አይመስለኝም ። ቢያንስ ቢፈቱ ጉራማይሌ አካሄድ ከመከተል ያድናል።