Page 1 of 1

ባህል እንደ ኦስሞሲስ

Posted: 22 Dec 2022, 17:59
by Naga Tuma
አይኖች ከፋቹ ትምህርት ቤት ኣንድ የማይረሳ ትምህርት የምያስተምረዉ የሰዉ ዘር የራሱን ምግብ መፍጠር እንደማይችል ነዉ። ለምሳሌ የገብስ እና የስንዴ ዘሮችን ዘርቶ ማጨድ እንጂ የሁለቱን እህል ዘሮች ፍሬዎች መፈጠር ኣይችልም።

በተፈጥሮ ዕፅዋቶች ናቸዉ የራሳቸዉን ፍሬ የሚፈጥሩት። ኦስሞሲስን እና ፎቶስይንተሲስን በመገልገል።

የባህልን እንደ ኦስሞሲስ ተምሳሌት ካሰብኩኝ ሰንብቻለሁ። ኢትዮጵያ የእንግሊዘኛ ቋንቋን የሚችሉ ምሁራንን ከዉጪ ብትቀጥር የሚል ዜናን በኣጋጣሚ ስሰማ ነዉ ተምሳሌቱ የመጣልኝ። ገንቢ ይሁን ኣይሁን በዉል ኣላዉቅም።

በቅርቡ ሁለት ምሁራን እዚሁ መድረክ ላይ ሲዋያዩ ተምሳሌቱን ኣስታወሱኝ። ኣንዳቸዉን ለተምሳሌቱ እንደምሳሌ ኣስቤ የነበረ መሆኑ መልሶ ገረመኝ።

ሁለት የኢትዮጵያ ወይም የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ምሁራን ምሁራዊ መናበብ በሰፊዉ የተለመደ ኣይመስለኝም። በሰፊዉ የምያስፈልግ ነዉ። ጥልቅ ዕዉቀት ጭር ሲል ኣልወድም።

እንደዚህ አይነት ምሁራን ፍሬዎች ናቸዉ። ዕፅዋት ኦስሞሲስን እና ፎቶስይንተሲስን ተጠቅመዉ ፍሬ የምያፈሩ ከሆነ ምሁራን ፍሬዎችን ለማፍራት የባህል ኣስተዋጽኦ ምን ያህል ነዉ?

ልጅ ሲወለድ ወይም ስትወለድ ባዶ ሰሌዳ ወይም ብላንክ ስሌት ነዉ ወይስ ኣይዴለም የሚለዉ ጥያቄ ሙሉ በሙሉ የተመለሰ ኣይመስለኝም።

ልጅ ባህል ዉስጥ ያድጋል። ኣብሮ ከተወለደዉ ባህል በላይ ዉስጡ የተወለደዉ ባህል የዳበረ ነዉ። ስለዚህ በዛ በዳበረዉ ባህል ሲጸረጽ ያድጋል ማለት ነዉ። ይህንን ሂደት ነዉ ባህል እንደ ኦስሞሲስ የምለዉ።

የባህል ኣስተዋጽኦ ጭምር የምሁርነት ፍሬን የምያፈራ ከሆነ የባህልን ኣስተዋጽኦ ለብቻዉ ለይቶ መገንዘብ ይቻላል? ኣስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

ኣንድ ምሳሌን ግን ማስተዋል ይቻላል። ከምናዉቀዉ ባህል መሃል የወጡትን እና ከዉጪ ሃገር ወይም ድያስፖራ የወጡትን ፍሬዎች ብስለት ማነጻጸር ይቻላል።

ካልተሳሳትኩ እንደምሳሌ የጠቀስኳቸዉ በአካል ያማላዉቃቸዉ ሁለት ምሁራን ከምናዉቀዉ ባህል መሃል የዉጡ ፍሬዋች ናቸዉ። እንደሁለቱ ምሁራን መናበብ የሚችሉ ከዉጪ ሃገር ወይም ድያስፖራ ባህል ማሃል በቀላሉ ማፍራት ይቻላል?

መልሱን ኣላዉቅም። ስላማላዉቅ ነዉ ይህን የምቀባጥረዉ።

Re: ባህል እንደ ኦስሞሲስ

Posted: 01 Sep 2023, 18:51
by Naga Tuma
ይህን ርዕስ ስጀምር ኢትዮጵያ የኮሌጅ ተማሪ ሆኜ ከኣንድ ጓደኛዬ የሰማሁትን ኣስደሳች ታሪክ እያስታወስኩም ነበር። ኢትዮጱያዊዉ ዶክተር ጌታቸዉ ቦለድያ (ቦለዳ?) እንግሊዝ ሃገር ዉስጥ ኦክስፎርድ ዩኒቨርዚቲ ሲማር ምን ያህል ጎበዝ ተማሪ እንደነበረ ጓደኛዬ ነገረኝ። የሰማሁት እዉነት እንደሆነ ነዉ የገባኝ።

ከዛን ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ያልተመለሰ ጥያቄ በኣእምሮዬ ዉስጥ ኣለ። ኦክስፎርድ ዩኒቨርዚቲ ከተቋቋመ ኣሁን ወደ ኣንድ ሺህ ዐመታት ሊጠጋ ነዉ። እ አ አ በ1096 የተቋቋመ ነዉ። ኣጼ የኩኖ ኣምላክ ሳይነግሱ ሁለት መቶ ዐመታት ገደማ በፊት።

ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘመናዊ የሚባለዉ ከፍተኛ ትምህርት ከተቋቋመ ኣንድ መቶ ዐመታት ሆኖታል ማለት የሚቻል ኣይመስለኝም። ምናልባትም እንደነ ዶክተር ጌታቸዉ ቦለድያ ኢትዮጵያ ዉስጥ የዘመናዊዉ ከፍተኛ ትምህርት ቀያሽ ነበሩ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ጥያቄዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ የመጀመርያዉ የዘማናዊ ከፍተኛ ትምህርት ቀያሾች የሚባሉት፣ ከኢትዮጵያ ባለሃገር ወይም ተቆርቋሪ ከተማ ተነስተዉ እንደነ እንግሊዝ ሃገር ዉስጥ የሰነበቱ እና ዝና ያላቸዉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዉስጥ ከእንግሊዝ ዜጋዎች የላቀ ዉጤት ካገኙ ለስኬታቸዉ የሃገር ባህል ምን ያህል ሚና ቢጫወት ነዉ?

በመጀመርያ መመለስ ያለበት የሃገር ባህል ዘመናዊ የሚባል የማስተማር መማር ሂደት ዉስጥ ጉልህ የሆነ ሚና ኣለዉ ወይ ነዉ።

ካለዉ ከመቼ ጀምሮ ሲዳብር የነበረ ባህል ነዉ በየቤቱ ልጆችን ለእንደዚህ ዐይነት ስኬት ለማዘጋጀት ሚና ሊኖረዉ የቻለዉ? ከጥንታዊት ግብጽ ዘመን ጀምሮ የነበረ እና የዳበረ ባህል ያልተስተዋለ ሚና ኣለዉ ማለት ኣይቻልም?

ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ ከሳንስክሪት ዘመን ጀምሮ የዳበረ ባህል ያላቸዉ ህንዶች እንደ እነኦክስፎርድ ዩኒቨርዚቲ ሲደርሱ ከእንግሊዞቹ ለላቀ ዉጤት ለማብቃት ሚና ኣለዉ ማለት ኣይቻልም?

እነዚህ ከበርካታ ምሳሌዎች ሁለት ናቸዉ።

የሚቻል ከሆነ ባህል እንደኦስሞሲስ ገና የሚወደስ ኣይሆንም?