Page 1 of 1

ሂደቱን ሳይሆን ምንጩን መታገል ያስፈልጋል

Posted: 21 Dec 2022, 09:13
by kibramlak
ሂደቱን ሳይሆን ምንጩን መታገል ያስፈልጋል

አብይ አህመድ ስልጣን ከጨበጠ ጊዜ ጀምሮ በዚች ሀገር የደረሰው ግፍና መከራ ተዘርዝሮ አያልቅም፣፣ ከትህነግ 27 አመት የግፍ ዘመን ያለማጋነን በ100 ወይም በ200 እጥፍ ቢበልጥ እንጅ አያንስም፣፣ የንሮ ውድነቱን ካነሳን ከ200 እስከ 1000 እጥፍ የታየበት ክስተት ነው፣፣ የደህነትን ጉዳይ ካነሳን በጀምላ በየጊዜው ያለማቋረጥ የሚጨፈጨፈው ቢደመር በደርግ እና በትህነግ ዘመን ያለቀውን ህዝብ በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ነው፣፣ ስለ ፍትህ ካነሳን አሁን ስልጣኑን የጨበጡ በጎሳ እና በሙስና የሰከሩትን የሚያገለግል እንጅ ተራውን ህዝብ ያገለለ መረን የለቀቀ የዘረኞች ስርአት ለመሆኑ አሁን እየሆነ ያለው ሁሉንም በአንድ ጎሳ የመጠቅለል ስካር ማስረጃ ነው

ስለዚህም ጎሰኞች እስካሁን እንደታየው የተለያየ አጀንዳ እየሰጡ የህዝቡን ማህበራዊ ህይወት ደህንነት ከድጡ ወደማጡ ( መቀመቁ) ያለማቋረጥ እየከተቱት ይገኛል፣፣ አብይ አህመድ፣ ህዝብን ማንበርከክ እና መግዛት የሚቻለው የህዝብን ከመጠን በላይ ማደህየት ነው ብሎ የሚያስብ ለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎች መጥቀስ ይቻላል፣፣ የጎሳ ፖለቲካ ዘርፈ ብዙ አጀንዳዎችን ለመስጠት ይመቻል፣፣ ለተከፋፈለ የፖለቲካ ስርአት ብዙ የሚያጋጭ እና የሚያናውጥ አጀንዳ ለመስጠት ለጎሰኞቹ በጣም ቀላል ነው ፣፣

ስለዚህ መፍትሄው ይህ ሁሉ የማያልቅ አጀንዳ ላይ ጊዜና ጉልበትን ከመጨረስ፣ ከስር መሰረቱ (ምንጩ) ላይ ማተኮር እና መዋጋት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፣፣ ምንጩን ስንታገል የጎሰኞቹን instrument ወይም ገዢ መሳሪያ ላይ ስናነጣጥር ህዝብ ለጎሰኞች አጀንዳ መስጠት ይጀምራል ማለት ነው፣፣ አጀንዳው ደግሞ የጎሳ ፌደራሊዝምን እና አከላለልን ማፍረስ ይሆናል፣ ስለ ኢትዮጵያ የሚታገል ሁሉ በአንድነት ይህን አጀንዳ ይዞ ከታገለ ጎሰኞችን መቀልበስ የሚቻልበት እድል ከፍ ያለ ይሆናል፣፣ ምክንያቱም ብዙዎች በጎሳ ስርአት የሚተዳደሩ ክልሎች ስርአቱን የግድ ስለማይደግፉት፣፣

Re: ሂደቱን ሳይሆን ምንጩን መታገል ያስፈልጋል

Posted: 26 Dec 2022, 04:20
by kibramlak
አብይ አህመድ ብዙ የኦባማን ንግግሮች ቃላት ሳይቀር ኮቲ አድርጎ ተናግሯል፣ ይህን ግን ለምን እንደዘለለው ስለ ሰውየው ኦነጋዊ አቋም ሊያስረዳ ይችላል፣

https://vm.tiktok.com/ZMF7XQgHP/

Re: ሂደቱን ሳይሆን ምንጩን መታገል ያስፈልጋል

Posted: 27 Dec 2022, 12:45
by Assegid S.
ሠላም Kibramlak;

ከፃፍከው ምክረ-ሓሳብ ጋር እኔም እስማማለሁ። በሃገራችን ታሪክ፦ የትኛውም የለውጥ አብዮት እሳት ከበላው ነፍስ ይልቅ የዶ/ር አብይ በረዶ ያረገፈው ህይወት የትየሌለ ነው። ሰውየው “እኔ ከሌላው የተሻልኩ mild ነኝ” የሚለውን እሳቤ በህዝብ ዘንድ ለማስረፅ ... ሌላው ሰይጥኖ millions ቢጨርስ በዝምታና ደስታ ከማለፍ ውጪ ሐዘን አይሰማቸውም።

አንተ ያወዳደርከውን የኣገዛዝ ዘመን በተመለከትም ... በመጠኑም ቢሆን ደጋፊ ይሆናል ብዬ ያሰብኩትን ቪድዮ ከታች post አድርጌያለሁ።

እውነት ለመናገር፦ የኢትዮዽያ ህዝብ “እገነጠላለሁ!”፣ “የራሴን ክልል እፈልጋለሁ!” የሚለውን የትኛውንም ብሔር “እረፍ - ኣንድነት ይበጀናል” ብሎ ከመማጸን … የራሱን ብሔር (በየትኛውም ክልል ውስጥ የሚኖሩትን ማለት ነው) ተፈጥሮዋዊና ትውልዳዊ መብት ( ህልውና) አስጠብቆ “መልካም መንገድ!” ብሎ ነው መሸኘት ያለበት። በመገንጠል መፍራት ያለበት ጎሰኛ "በእገነጠላለሁ" ሲያስፈራራ ማየት እጅግ ያሳፍራል። አሁን የምናያቸው የኦሮሞ ብሔርተኞችም ቢሆኑ ኦሮሚያን ከኢትዮዽያ ገንጥሎ 196'ኛ ሀገር ከማድረግ ይልቅ ከኣፍሪካ ነጥሎ ስምንተኛ ኣህጉር መፍጠር ይቀላቸዋል። ዛሬ ኣንድ ኦሮሚያ የሚባል ሀገር ብትሰጣቸው ነገ 14 ቦታ ከፋፍለው አህጉር ይዘውልህ ይመጣሉ።

እንደ እኔ ሓሳብ እና አንተም እንዳልከው፦ ህዝባችን "ሂደቱን ሳይሆን ምንጩን ከመታገል" ጎን ለጎን ከድርጊት ይልቅ ውጤትን በሚገባ አጢኖ ልመናና ምልጃን ማቆም አለበት። እኔ የከበት በረት የሆነው ብኣዴንን አምርሬ የምጠላው በዚህ - ተለማማጭና ተላላኪ ስብዕናው ነው። ሌላው ቢቀር በኦሮምያ ክልል ውስጥ የምናየውን መጠን ያለፈ ክፋት ለማስቆም አጥንት ባይኖረው እንኳ አጥንት ያላቸው ኣካላት የሚደራጁበትን አጥር እና ድጋፍ በክልሉ ውስጥ መንፈግ አልነበረበትም። ግን ምን ዋጋ አለው … ሆዳም ሥጋ እንጂ ልብ አይገዛም!

መልካም ሁን ወንድሜ ክብር-ኣምላክ

Re: ሂደቱን ሳይሆን ምንጩን መታገል ያስፈልጋል

Posted: 30 Dec 2022, 08:04
by kibramlak
ሰላም ወንድሜ አሰግድ

ስለ አስተያየትህ እና ስለ አካፈልከኝ ቪድዮ አመሰግናለሁ ፣፣ በቪድዮው የሚናገረው የፍልስፍና ባለሙያ ነጭ ነጩን ነው የተናገረው፣፣ የብአዴንን ቱባ ቱባ ሆዳሞች በቁማቸው የበከቱ ከኦሮሙማው አራጅ በበለጠ የአማራውን ህዝብ ለማስጨረስ ቆርጠው የተነሱ ናቸው፣፣ አገኘሁ ተሻገር የሚባል ሰካራም እና ሴሰኛ አንድ ሴተኛ አዳሪ ሲጋበዝ ብቻ ብዙ የሚወሸክት እና ያመነውን አሳልፎ የሚሰጥ የሰው ውዳቂ መሄኑን በቅርበት እማውቃቸው እና እብረውት ከነበሩት የሰማሁትን ነው፣፣ ሁሉንም ስብስብ መቅፀፍት ቢወርድባቸው ስንት ህይወት ይታደግ ነበር፣፣ ስልጣን ላይ ብቻ ለመኖር ሱሉ እኮ ነው ህዝብን ለመታደግ የሚደረግን እንቅስቃሴ ሁሉ ለማጥፋት የሚታገሉ፣፣

ስለወለጋው ጥቃት አገኘሁ ሲጠየቅ እኮ "ምን ላድርግህ ከኦሮምያ ክልል ጋር ሂድና እይ" ብሎ የመለሰ ጭንጋፍ እኮ ነው፣፣
Assegid S. wrote:
27 Dec 2022, 12:45
ሠላም Kibramlak;

ከፃፍከው ምክረ-ሓሳብ ጋር እኔም እስማማለሁ። በሃገራችን ታሪክ፦ የትኛውም የለውጥ አብዮት እሳት ከበላው ነፍስ ይልቅ የዶ/ር አብይ በረዶ ያረገፈው ህይወት የትየሌለ ነው። ሰውየው “እኔ ከሌላው የተሻልኩ mild ነኝ” የሚለውን እሳቤ በህዝብ ዘንድ ለማስረፅ ... ሌላው ሰይጥኖ millions ቢጨርስ በዝምታና ደስታ ከማለፍ ውጪ ሐዘን አይሰማቸውም።

አንተ ያወዳደርከውን የኣገዛዝ ዘመን በተመለከትም ... በመጠኑም ቢሆን ደጋፊ ይሆናል ብዬ ያሰብኩትን ቪድዮ ከታች post አድርጌያለሁ።

እውነት ለመናገር፦ የኢትዮዽያ ህዝብ “እገነጠላለሁ!”፣ “የራሴን ክልል እፈልጋለሁ!” የሚለውን የትኛውንም ብሔር “እረፍ - ኣንድነት ይበጀናል” ብሎ ከመማጸን … የራሱን ብሔር (በየትኛውም ክልል ውስጥ የሚኖሩትን ማለት ነው) ተፈጥሮዋዊና ትውልዳዊ መብት ( ህልውና) አስጠብቆ “መልካም መንገድ!” ብሎ ነው መሸኘት ያለበት። በመገንጠል መፍራት ያለበት ጎሰኛ "በእገነጠላለሁ" ሲያስፈራራ ማየት እጅግ ያሳፍራል። አሁን የምናያቸው የኦሮሞ ብሔርተኞችም ቢሆኑ ኦሮሚያን ከኢትዮዽያ ገንጥሎ 196'ኛ ሀገር ከማድረግ ይልቅ ከኣፍሪካ ነጥሎ ስምንተኛ ኣህጉር መፍጠር ይቀላቸዋል። ዛሬ ኣንድ ኦሮሚያ የሚባል ሀገር ብትሰጣቸው ነገ 14 ቦታ ከፋፍለው አህጉር ይዘውልህ ይመጣሉ።

እንደ እኔ ሓሳብ እና አንተም እንዳልከው፦ ህዝባችን "ሂደቱን ሳይሆን ምንጩን ከመታገል" ጎን ለጎን ከድርጊት ይልቅ ውጤትን በሚገባ አጢኖ ልመናና ምልጃን ማቆም አለበት። እኔ የከበት በረት የሆነው ብኣዴንን አምርሬ የምጠላው በዚህ - ተለማማጭና ተላላኪ ስብዕናው ነው። ሌላው ቢቀር በኦሮምያ ክልል ውስጥ የምናየውን መጠን ያለፈ ክፋት ለማስቆም አጥንት ባይኖረው እንኳ አጥንት ያላቸው ኣካላት የሚደራጁበትን አጥር እና ድጋፍ በክልሉ ውስጥ መንፈግ አልነበረበትም። ግን ምን ዋጋ አለው … ሆዳም ሥጋ እንጂ ልብ አይገዛም!

መልካም ሁን ወንድሜ ክብር-ኣምላክ

Re: ሂደቱን ሳይሆን ምንጩን መታገል ያስፈልጋል

Posted: 30 Dec 2022, 08:08
by kibramlak
ትግሉ በትክክል እንደዚህ ነው መሆን ያለበት፣፣ የችግሮች ሁሉ መነሻ ላይ ነው ማተኮር ያለብን

አቡሽ እውነት በጣም ታላቅ ሰው ! አውጡት ከፓርላማው