Page 1 of 1

3 National Anthem- translation A NATION UNABLE TO GET OUT OF STUPIDITY

Posted: 20 Dec 2022, 12:23
by Right
የ3ቱን ክልሎች ክልላዊ የህዝብ መዝሙሮች – የአማርኛ ትርጓሜ አንብቡና – ፍርዱን ለህሊናችሁ ስጡት!
1. የትግራይ ክልል መዝሙር /የአማርኛ ትርጉም /

የማንወጣው ተራራ

የማንሻገረው ወንዝ የለም ፤

ፍፁም ወደኋላ የለም

መስመር ነው ኃይላችን

ህዝብ ነው ኃይላችን በጭራሽ አንሸነፍም!በፀሀይ ሀሩር እና በቁር ነፍሳችን ውሀ ይጥማት አለት ይሁን ትራሳችን ዋሻ ይሁን ቤታችን ሌትም ቀንም ጉዞ ይድከመንም ይራበንም ሆኖም መስመር ነው ኃይላችን ህዝብ ነው ኃይላችን በጭራሽ አንሸነፍም፤ በጅቦች እንከበብ መሬት ይክበበን የጠላቶቻችን ጥርስ ስጋችን ውስጥ ይቀርቀር!ስጋችን ላሞራ ደማችን እንደ ጎርፍ ይፍሰስ፤ አጥንታችን ይድቀቅ ዱቄት ሆኖ ይበተን መስመር ነው ኃይላችን ህዝብ ነው ኃይላችን በፍፁም አንሸነፍም፤የጦር መሳሪያ መርዝ ፋሽስታዊ ንዳድሚሊየን ጠላቶቻችን ፊታችን ላይ ይጉረፉ መስዋዕትነት መቁሰል እና ኪሳራም እንከፍላለን፤የከፋ መከራም ቢመጣ ወደን እንከፍላለንመስመር ነው ኃይላችን ህዝብ ነው ኃይላችን፤ በዚህ ሁሉ ጉዞ ግን አሸናፊዎች እኛ ነን። ☞ በማለት የትግራይ ክልል መንግስት በትግራይ ባሉ ትምህርት ቤቶች ላለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እስካሁን ድረስ ይዘምራል ።

2. የኦሮሚያ ክልል መዝሙር / የአማርኛ ትርጉም /ኦሮሚያ //2// የትልቅ ህዝብ ታሪክ እናትየኦሮሞዎች እምብርት ፥ የገዳ ስርአት አዳራሽ የህግና ስርአት መሬት ፥ የጨፌ ኦዳ እናትየብልጽግና ልምላሜ ፥ ሁሉን አብቃይ እናትየመቶ አመት እድፍ ፥ በደማችን አጠብንልሽበብዙ እልፍ እልቂት ፥ ባንዲራሽን ከፍ አደረግንደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ ፥ ስልጣንን መልሰን አገኘንሰላምና ዴሞክራሲ ፥ የሰብአዊነት መብትአስተማማኝ ልማት ፥ ዘላቂ ልማትከህዝቦች ጋር ሰላምና ፍቅርለመኖር ዋስትና ትልቅ አላማ አድርገንኃይላችንን አሰባስበን ፥ ተነስተናል ተማመኚብንኦሮሚያ አብቢ ፥ ለምልሚና ኑሪ!☞ በማለት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እንካሁን ድረስ በኦሮሚያ ክልል ይዘመራል ። አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ካልተዘመረ እየተባለ በተደጋጋሚ እየተነሳ ነው ።

3. የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መዝሙር የታታሪ ህዝቦች የታሪክ ማህደርየአኩሪ ባህል አምባ የድንግል ሀብት አፈርየህዝቦችሽ ተስፋ ለሟ ክልላችንበሰላም በፍቅር በልማት ጉዟችችን ተባብረን በስራ እንገነባሻለንየአማራነት ክብር ደማቅ አርማ ይዘን ፥ከሌሎች ህዝቦች ጋር እኩል ተከባብረን በፍቅር በአንድነት አብረን እንዘልቃለን ።☞ በማለት የአማራ ክልል ህዝብ መዝሙር ይቋጫል ፡፡ ይህ መዝሙርም ላለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እስከአሁን ድረስ በክልሉ ይዘመራል ።ለትውልዱ የጥላቻና የክፋት መርዝ እየጋተ ፥ ሀገርን የሚያፈርሰው ማን እንደሆነ ፥ የህዝብ ህሊና ፍርዱን ይስጥ!11