Page 1 of 1

ቋንቋና ጎጠኝነት

Posted: 18 Dec 2022, 19:52
by Selam/
ቋንቋ ከመግባቢያነቱ ባሻገር፣ አንዱ የማንነት መግለጫ ባህላዊ እሴት ነው። ታዲያ በተለያዩ የኢትዮዽያ ሕዝቦች መካከል ግንኙነትን ለማጠናከርና መግባባትን ለማጎልበት፣ በሁሉም አካባቢ ሁለት ሦስት ቋንቋ በተማሪ ቤቶች መስጠት እንዲሁም የሥራ ቋንቋ ማድረግ አሁን ያለውን ጎጠኝነትንና አለመግባባትን የሚያረግብና የሚያስተነፍስ ይመስለኛል።

Re: ቋንቋና ጎጠኝነት

Posted: 18 Dec 2022, 22:13
by Horus
Selam/ wrote:
18 Dec 2022, 19:52
ቋንቋ ከመግባቢያነቱ ባሻገር፣ አንዱ የማንነት መግለጫ ባህላዊ እሴት ነው። ታዲያ በተለያዩ የኢትዮዽያ ሕዝቦች መካከል ግንኙነትን ለማጠናከርና መግባባትን ለማጎልበት፣ በሁሉም አካባቢ ሁለት ሦስት ቋንቋ በተማሪ ቤቶች መስጠት እንዲሁም የሥራ ቋንቋ ማድረግ አሁን ያለውን ጎጠኝነትንና አለመግባባትን የሚያረግብና የሚያስተነፍስ ይመስለኛል።
Selam,
አይምሰልህ፤ ድሮ በነበረው ናቹራል ሂደት በጉርብትና፣ በገበያና በመፈቃቀር የተመሰረተ ቢሆን ኖሮ ቋንቋ ቦንድ አንድነት ወይም አንድ ኮሚኒቲነት መፍጠሪያ ይሆን ነበር። ቋንቋ በመሰረቱ እስኪል ነው፣ ማለትም ክህሎት ነው ። ክህሎት ወይም እስኪል ደሞ ተግባር ላይ መዋል አለበት ።

አንድ ያላየሀው ትልቅ ነገር ቋንቋ አሁን የፖለቲካ መሳሪያ ሆኖዋል ። ስለዚህ ሁለት ጎሳዎች በፖለቲካ የሚጣሉ ወይም የሚቃረኑ ከሆነ ቋንቋው ሺ ግዜ በትምህርት ቢሰጥ ተማሪው ፈተና ካለፈ በኋላ ይረሳዋል ። አንድ አማራ ወጣት ኦሮሞኛ የሚናገረው ኦሮሞን ስለሚወድ ነው እንጂ ቋንቋውን ስለ ተማረ አይደለ። ለምሳሌ ትግርኛን ቋንቋ ውሰድ። 27 አመት ኢትዮጵያን ገዝተው፣ ስንትና ስንት የትግርኛ ሚዲያ አቁመው አንድ ትግሬ ያልሆነ ሰው ትግርኛ አይናገርም ። እኔ አንድ የትግርኛ ፕሮግርም ከፍቼ አላውቅም ። ባላገር ሳድግ ትልቅ ቅዳሜ ገበያ አለ ብዙ ጎሳዎች የሚደባለቁበት ብዙ ብዙ ሰው ባይሊንጓልና ትራይ ሊንጓል ነው ። አሁን ያ ቆሞዋል ።

ስለዚህ ያንተ ቲሲስ ይሰራ የነበረው በህዝቦች መሃል የጎሳ ፖለቲካ ከመግባቱ በፊት ነው ። ከዚህ በኋላ አይሰራም። እንዲያውም በቋንቋዎቹ መሃል ያለው ግምብ እየጠነከረ ይመጣል። የሚፈጠረው ይህ ነው። ኢትዮጵያ የቋንቋዎች ጌቶ ነው የምትሆነው ። ምን ማለቴ መሰለህ?

አሁን እያንዳንዱ ቋንቋ እየተጻፈ ነው ። ተጽፎም ትምህርት ቤት የሳጠል ። እያንዳንዱ ጎሳ የራሱ ሚዲያ ማለትም ጋዜጣ፣ ቲቪ፣ ዘፈን፣ ሲኒማ፣ መጽህፍት ወዘተ አለው፣ ይኖረዋል ። አንድ ሰው ከራሱ ጎሳ ሚዲያ ውጭ መጠቀም፣ ማየት፣ መስማት፣ መዝፈን ያቆማል ። ሁሉም ጎሳ በራሱ ሰፈር ቋንቋና ካልቸር ውስጥ ይታጠራል ።

ከዚያ በተረፈ የኣማርኛ ቋንቋ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ ናቹራል ቋንቋ ከሆነ ቆይቷል ። ስለዚህ ዘመናዊ ኢትዮጵያ የሚባሉት የሚናገሩዋቸው ሁለት ቋንቋዎች አማርኛና እኢግሊዝኛ ሆነው ይቀጥላሉ ። ይህ አንድ ሰው ስለፈለገውና ስለጠላው አይደለም ። የኢትዮጵያ ሪያሊቲዎች ወደ አይምሮ ገብተው የሚገለጹበት ቁጥር አንድ ክህሎት ስለሆነ ነው። እኔ ትህምርት ቤት ፈረሳይኛ ተምሬ በተስውነ እናገረው ነበር ። የኔ ኮግኒቲቭ እስትራክቸር የተሰራው በንግሊዝኛ ስለሆነ አሁን ባብዝኛው ረስቼዋለሁ ።

ልብ በል የሰው ልጅ ማንበብ አለበት ። ለማንበብ የንባቡ ይዘት ታሪክ መሆር ለበት ያ ካልቸር የምንለው ነው ። በዛሬ የጎሳዎች ጥላቻና ፖለቲካዊነት አንድ የጋሞ ሰው ስራዬ ብሎ የካፋ ካልቸር ለመማር የሚገፋው ሞቲቪሽን የለም ። ስለዚህ እነሺምለስ ብዙ ሪሶርስ ያባክናሉ እንጂ በፖለቲካ ፕሬሸር፣ በጉልበት፣ በጥላች ፣ በአምስገደድ የኦሮሞ ቋንቋም ሆነ ካልቸር የሚማር ሰው አይኖርም፣ ቢኖርም ጥቄት ጥቅም ያላቸው ሰዎች ናቸው፣ ይሆናሉ!

Re: ቋንቋና ጎጠኝነት

Posted: 19 Dec 2022, 08:46
by Selam/
የምትለው በጣም ይገባኛል - ግን ማወቅ ያለብህ ይኸ አሁን ያለው ወያኔ የወለደው እኩይ የጎጠኝነት አሰራር አይዘልቅም። አብጦና ተነፍቶ አንድ ቀን በከፊልም ይሁን በሙሉ መፍረሱ አይቀርም። ከዚህም በተያያዘ፣ የወያኔ እርዝራዦችም ይዋል ይደር እንጂ ከፖለቲካው መሰላል ላይ ወደታች መዝቀጣቸው አይቀርም።

ስለዚህ ዘላቂም ይሁን አይሁን የቋንቋ ልውውጡን የሆነ ቦታና ጊዜ ላይ መጀመሩ አይከፋም። እኔ በበኩሌ ቁቤ በግዕዝ ፅሁፍ ቢሰጥ ዛሬ ማጥናት እጀምራለሁ። ኦሮምኛ ለመማር ዙሪያ ጥምጥም መሂዱ በሁሉም መንገድ ያስወገድኩት የቅኝ ገዥዎች እጅ ውስጥ በፈቃደኝነት መውደቁ ስለሚመስለኝ ያሳፍረኛል። እንዲያውም እደኔ እንደኔ በሆንማ ኖሮ፣ አይደለም ቁቤ፣ በግብር ከፋይ የህዝብ መገናኛ ላይ በተሰባበረ እንግሊዘኛና ዝብርቅርቅ ባለ ጉራማይሌ ቋንቋ የሚጨማለቁትን እንደ ዶር ደረጀ ያሉትን የሀሳብ ባሪያዎች ፵ መግረፍ ይገባ ነበር። :lol:
Horus wrote:
18 Dec 2022, 22:13