Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Right
Member
Posts: 4824
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Solomon Shumeye detained for 5 hrs. EI

Post by Right » 17 Dec 2022, 16:36

ሰለሞን ሹምዬ ከአምስት ሰዓታት እስር በኋላ ተለቀቀ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
December 17, 2022


በሃሚድ አወል

ዛሬ ቅዳሜ ረፋድ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለው ሰለሞን ሹምዬ፤ ከአምስት ሰዓታት እስር በኋላ 10 ሰዓት ከ40 ገደማ መለቀቁን ቤተሰቦቹ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ ። ሰለሞን ዛሬ አምስት ሰዓት ገደማ ላይ በፖሊስ ከተያዘ በኋላ፤ በአዲስ አበባ ገነት ሆቴል አቅራቢያ ወደሚገኘው “የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ መወሰዱን” እህቱ ትግስት ሹምዬ አስታውቃ ነበር።

“ገበያኑ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነው ሰለሞን ከእስር ከተፈታ በኋላ ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጋር ባደረገው የስልክ ቆይታ፤ እንዴት እንደተለቀቀ እና በፖሊስ ሲያዝ የነበሩ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለቀረቡለት ጥያቄዎች አጭር ምላሽ ሰጥቷል። ሰለሞን ከእስር ስለተለቀቀበት ሁኔታ ሲገልጽ “ምንም የነገሩኝ ነገር የለም። ስንፈልግህ እንጠራሃለን አሉኝ” ሲል ሂደቱን አስረድቷል።

Thread


Ethiopia Insider

@ethiopiainsider

“ገበያኑ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነው

ሰለሞን ሹምዬ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ።ሰለሞን በቁጥጥር ስር

የዋለው ዛሬ ቅዳሜ ታህሳስ 8 ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ

ቤቱ መሆኑን እህቱ ተናግራለች።