.
.
.
-
Assegid S.
- Member
- Posts: 950
- Joined: 11 Aug 2013, 07:11
- Contact:
Re: ሕዝብ ሲተፋህ እንዲህ ነው
"ባቢሎናውያን"ን በ"አበቤውያን" ተክቶ የማዳመጥ መብታችሁ በER ሕግ የተጠበቀ ነው!
Hereunder, I've transcribed some part of the speech ... by Pastor Cherinet?
Hereunder, I've transcribed some part of the speech ... by Pastor Cherinet?
… አሁን ሀገራችን ላይ የሚታየኝ እንደ ተውሳክ የተቀመጠ ነገር አለ። እኛን ሊሆን የሚፈልግ፤ ባለ ሀገር ሊሆን፣ ባለ ባንዲራ ሊሆን የሚፈልግ የሚታየኝ ተውሳክ አለ። ተውሳክ ደግሞ የሆነ የሆነ ነገር ወስደህ ድራሹን ነው ማጥፋት ያለብህ። ከተውከው ግን ይገርምሃል የናቅከው ኮሶ ሊገድልህ ይችላል። ጨርሶ ጤናህን ሊነሳህና ሊያጠፋህ ይችላል።
… በማህበረሰባችን ግራ መጋባት አለ። ግራ መጋባትን የሚያመጣው ደግሞ ውሸት ነው፤ ውሸት፦ የተደበቀ hidden የሆነ ኣጀንዳ ነው። ስለዚህ ውሸታም ሰዎች፣ በሀገር ላይ ያላችሁ ሰዎች hidden የሆነው ፕሮግራማችሁን እግዚአብሔር አይቶታል። መቆም አትችሉም።
… እነዚህ ሰዎች እንደ ባቢሎናውያን ናቸው። ትውልድ ሁሉ ጠፍቶ እግዚአብሔር ከትውልድ ጋራ ኣዲስ ቃልኪዳን ከገባ ቦኃላ ልክ መኖር ሲጀምር መጡና ሰናዖር ምድረበዳ ላይ ተገናኙ፣ ከዛ ኣንድ ፕሮግራም አወጡ፣ ምን አሉ መሰላች ሁ፦ “በምድር ላይ ሳንበተን ስማችንን እናስጠራ!” ስለዚህ “ወደ እግዚአብሔር የሚያደርስ ከተማ እንስራ” አሉ። ይኼ hidden የሆነ ፕሮግራማቸውን ተመልከቱ - “ስማችንን እናስጠራ! የእኛን ስም እንትከል! የእኛን ፕሮግራም እንትከል! የተፈጠርንበት አይደለም፣ አምላክ የሰጠን አይደለም እርሱን ትተነው እኛ የእራሳችንን መንግስት እናቁም”
… ባቢሎናውያን የትዕቢት ተምሳሌቶች ናቸው። በትዕቢት ማን-አለብኝነትን ይዘው ለሚንቀሳቀሱ ሰዎች እነዚህ ምሳሌ ናቸው። “ስሜ ዘሬ” ለሚሉ ሰዎች ምሳሌ ናቸው። ለትቢዕተኞች ምሳሌ ናችው። ለዓመፀኞች ምሳሌ ናቸው። “እኔ - የእኔ” ለሚሉ ምሳሌ ናቸው። “የእኛ” ለሚሉ ምሳሌ ናቸው። “ዘሬ - ስሜ” ለሚሉ ሰዎች ሌላ ፓርቲ አይደለም ሥላሴ ነው የሚነሳው። ስለዚህ በጣም የተንቀዠቀዣችሁ ፋራዎች - የመጨረሻ ፋራ ሰዎች ይታዩኛል። ምንም የማይሰለጥኑ ፋራዎች፣ ከትላንትና አትማርም ወይ? አፈር ድሜ - ደቼ የበሉ ሰዎችን አላየህም ወይ?
… ያሰቡት አይሆንም፤ ያሰቡት አለመሆኑ ብቻ አይደለም፥ ሲነሱ የነበራቸውን ዋናቸውንም ያጣሉ። አሁን በኢትዮዽያ ምድር ላይ የተነሳችሁ ሰዎች ሥላሴ ነው የሚነሳው። “የእኛ - የእኔ” የምትሉ ሰዎች እግዚአብሔር ይነሳል። ፋራዎች ተመለሱ! ሰገጤዎች ተመለሱ! በጣም ብዙዎቹ ከሀገር-ቤት ነው የመጡት፥ ተመለሱ! ኣንድ ጎደኛዬ ይላል፦ “ፋራ ኬክ አይብላ፥ ከበላ እራሱን ይነካዋል” ። ኧረ እንደዚህ አይደረግም! በጣም በጣም shame ነው! ሰው ይታዘበናል በሉ። እናንተ የማታዩት እርሱ የሚያያችሁ በጣም ብዙ ሰው አለ።