የወልቃይት ጠገዴ ጉድይ ምን እየሆነ ነው?
ስለወልቃይት ጠገዴ የምንሰማቸው ዜናዎች አሳሳቢ ሆነዋል:: ለሁለት ዓመት ያለ መብራት በጨለማ እንዲኖር የተፈረደበት በፖለቲካ ፍላጎት እንጂ እውነት ችግሩን ለመቅረፍ ቢፈለግ ኖሮ መብራት ከጎንደር ማስቀጠል ይቻል ነበር:: ይባስ ብሎ ችግራይ ላይ መብራት ተለቆ ሳለ ወልቃይት ጠገዴ ላይ ግን እስካሁን በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ አካባቢዎች ማታ ማት መብራት ብቅ ትላለች:: ያ ሳይበቃ በእንቅርት ላይ ጆር ደግፍ እንደሚሉት አማራውን ገለውና አስገድለው የፈረጠጡ ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው ከሱዳንና ከችጋርይ ተመልሰው እንዲሰፍሩ ለማድረግ ዕቅድ እንዳለ እንሰማለን:: ኧረ ምንድነው እየሆነ ያለው?