Page 1 of 1
ቴዎድሮስ ካሳሁን አንድ ቀን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ይሆናል! (ጂጂ እንኳን ለዚህ አበቃሽ!!)
Posted: 05 Dec 2022, 01:03
by Horus
ቴዲ አፍሮ ማለት በትክክል የአይነኬ ኢትዮጵያዊያን ዝርያ ነው! ቴዎድሮስ ካሳሁን ገርማሞ እንደ ስሙ ነው! የስሞቹን ትርጉም የሚያውቅ ይመስለኛል ። ቴዎድሮስ ማለት 'የእግዚብሄር ስጦታ' ማለት ነው ። ቃሉ ግሪክ ሲሆን ቲዎ (ዴዩስ) እግዚአብሄር ማለት ሲሆን ዶሮስ ስጦታ ማለት ነው። ካሳ ተበቃይ ማለት ብቻ ሳሆን የጦር መሪ አጋዝ አበጋዝ የሚለው ቃል ስር ነው ። ገርማሞ በጉራጌኛ ግርማዊ ባማርኛ ነው ። ገርማሞ ባለ ግርማ፣ ግሬስፉል ማለት ነው ። በእውነት ከቴዲ የላቀ ግርማዊ ሰው የለም ።
ቴዎድሮስ የሚለው ስሙ ከጎንደሬዋ ቆንጆ እናቱ የመጣ ሊሆን ይችላል። አባቱም ቢሆን ግዕዝን ጥርት አድርጎ የተማረ ገጣሚ ባለቅኔ ነበር ። ካሁን ገርማሞ የአይበገሬ ኢትዮጵያዊያኖቹ ክስታኔ (ሶዶ) ጉራጌ ሲሆን አገሩ እንደቡየ ይባላል። እነዚህ ክስታኔዎች እነባልቻ ሰፎን፣ እነሃብተጎርጊስ ዲነግዴን እነገብረማሪያ ጋሪን፣ እነበቀለ ወያን የወለዱ ሕዝብ ናቸው ። በቃ ያ ነው ቴዲ አፍሮ ማለት! በኢትዮጵያዊነታቸው እንከን የማይወጣላቸው የጉራጌ ጎንደሬ ፍጡር ነው ።
ቴዲ አፍሮ እጅግ እጅግ የምወዳትን የጂጂን ችግር ላይ አንድ ነገር ያደረገ ነው ሲባል ስሰማ ሲቃ ነው የተናነቀኝ ። ቴዲ አፍሮ ከመላዕክት በታች ያለ የተቀደሰ ፍጡር ነው ። በእኔ ግምትና ጸሎት ይህ ሰው ወደ 60 አመት እድሜው ሲጠጋ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ለመሆን እራሱን ማዘጋጀት ይኖርበታል ! ኢትዮጵያን ከዚህ መከራ የሚያወጣ ሰው ነው !!!
Re: ቴዎድሮስ ካሳሁን አንድ ቀን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ይሆናል!
Posted: 05 Dec 2022, 15:05
by Horus
ሎሬት ባለቅኔ ቴዲ አፍሮ ከመላዕክት በታች ያለ ቅዱስ ፍጡር !!! ጂጂን ላገሯ ካበቃ ሌላው ታላቁ የቅድስናው ስራ ይሆናል ።
Re: ቴዎድሮስ ካሳሁን አንድ ቀን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ይሆናል! (ጂጂ እንኳን ለዚህ አበቃሽ!!)
Posted: 05 Dec 2022, 15:37
by Horus
Re: ቴዎድሮስ ካሳሁን አንድ ቀን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ይሆናል! (ጂጂ እንኳን ለዚህ አበቃሽ!!)
Posted: 05 Dec 2022, 15:42
by TGAA
Horus wrote: ↑05 Dec 2022, 15:37
Seconded!
Re: ቴዎድሮስ ካሳሁን አንድ ቀን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ይሆናል! (ጂጂ እንኳን ለዚህ አበቃሽ!!)
Posted: 05 Dec 2022, 15:53
by Horus
Tedy Afro, a Healer!!! Amazing !! Amazing!!! Just Like That!!! Only Mircle Makers With Divine Power Can Do Such Things!!! We Will Have Our Beloved Gigi ኤቦ ዬቦ !!!
Re: ቴዎድሮስ ካሳሁን አንድ ቀን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ይሆናል! (ጂጂ እንኳን ለዚህ አበቃሽ!!)
Posted: 05 Dec 2022, 16:04
by Horus
THE GLORIOUS REBIRTH OF THE BEAUTIFUL MUSICAL GENIUS - GIGI SHIBABAW !! TEDY AFRO THANK YOU !!
Re: ቴዎድሮስ ካሳሁን አንድ ቀን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ይሆናል! (ጂጂ እንኳን ለዚህ አበቃሽ!!)
Posted: 05 Dec 2022, 16:12
by DefendTheTruth
Horus wrote: ↑05 Dec 2022, 01:03
ቴዎድሮስ ካሳሁን አንድ ቀን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ይሆናል!
መንጋን መንዳት የምችል ከሆነ፣ እንኳን ፕረዚደንት ለምንስ ነዉ ንጉስ መሆን የማይችለዉ?
የመንጋ ዘመን፣ የድንቁርና ዘመን ነዉ ያለንበት ጊዜ፣
ፕረዚደንትም ሆነ ንጉስ ያስልጣን በመንጋዎቹ ሰፈር ብቻ ነዉ ስራ ላይ የምዉለዉ።
Re: ቴዎድሮስ ካሳሁን አንድ ቀን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ይሆናል! (ጂጂ እንኳን ለዚህ አበቃሽ!!)
Posted: 05 Dec 2022, 16:34
by Horus
ቀና በል! ቴዎድሮስ ካሳሁን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጀግናና መሪ የአርት ንጉሥ !!
Re: ቴዎድሮስ ካሳሁን አንድ ቀን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ይሆናል! (ጂጂ እንኳን ለዚህ አበቃሽ!!)
Posted: 06 Dec 2022, 05:42
by Selam/
አንተ ክስታኔ ጎንደሬ ብለህ ሸነሸንከው እንጂ፣ ‘ቅርጹም‘ ይዘቱም ኢትዮዽያዊ ብቻ የሆነ የዜጋ ምሣሌ ማለት ቴዲ ነው። እሱነቱም የተቀረጸው በቤተሰቡና ባደገበት ኅብረተሰብ እንጂ በዘር ገመዱ አይደለም።