በቀጣይም በውይይቱ እና በድርድሩ የተገኘውን ድል ሕገ-መንግሥቱን መሠረት በማድረግ ዳር ለማድረስ በትጋት መሥራት እንደሚገባ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገልጸዋል EBC
Posted: 20 Nov 2022, 11:11
ችግሮችን በውይይት እና በድርድር መፍታት የሥልጣኔ መገለጫ ነው፦ አቶ አገኘሁ ተሻገር
*********************
ችግሮችን በውይይት እና በድርድር መፍታት የሥልጣኔ መገለጫ ነው ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ።
አፈ-ጉባኤው ይህን የገለጹት 17ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ በአማራ ክልል በኦሮሞ ልዩ ዞን በከሚሴ ከተማ በተዘጋጀው የበዓል ዝግጅት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
አፈ-ጉባኤው፣ “በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተከስቶ የነበረውን የእርስ በእርስ ጦርነት በሰለጠነ መንገድ በውይይት እና በድርድር ለመፍታት በመቻላችን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ሰላም ውዳድነታቸው እና አሸናፊነታቸውን በዓለም አደባባይ ያስመሰከሩበት ነው” ብለዋል።
በቀጣይም በውይይቱ እና በድርድሩ የተገኘውን ድል ሕገ-መንግሥቱን መሠረት በማድረግ ዳር ለማድረስ በትጋት መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ለሰላም መከበር ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነው፣ በቀጣይ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም እና ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ለመመለስ በጋራ መረባረብ ይገባል ብለዋል።
“ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም” ከሚለው የዘንድሮው መሪ ቃል እንደምንረዳው የደመቀው ብዝኃነታችን እና የተገመደው ኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችን ሰላማችንን የሚያጸና ሲሆን ሰላማችን በጽኑ መሠረት ላይ ሲገነባ ችግሮቻችንን ተሻግረን ብልጽግናችንን እናረጋግጣለን ሲሉም ገልጸዋል።
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል የማንነታችን መስታወት፣ ታሪኮቻችንን እና እሴቶቻችንን የምናበለጽግበት የጋራ መድረካችን እንዲሁም ባህሎቻችንን እና መልካም ትሥሥራችንን ለመላው ዓለም በአደባባይ የምናሳይበት የሕብረብሔራዊነት ምልክታችን ነው ብለዋል አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር።
ይህ ሁሉ እውን የሚሆነው ታዲያ ብዝኃነታችንን አምነን ስንቀበል እና ለኅልውናውም በአብሮነት ስንታገል ነው ማለታቸውን ከፌዴሬሽ ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Please wait, video is loading...