ያልተዘመረለት ጀግና-በኢትዮጵያና በምዐራቡ አለም(ዋና ተላላኪያቸው የሆነው ወያኔና ኦኤልኤፍ ሸኔ-secondary banda) መካከል እየተደረገ ባለው ጦርነት ውስጥ ሚናው ብዙም...
Posted: 19 Nov 2022, 11:40
በኢትዮጵያና በምዐራቡ አለም(ዋና ተላላኪያቸው የሆነው ወያኔና ኦኤልኤፍ ሸኔ-secondary banda) መካከል እየተደረገ ባለው ጦርነት ውስጥ ሚናው ብዙ ያልተወሳለት ጀግና( በተለምዶ ያልተዘመረለት ጀግና)
--------------------------------------------------------------------------------
ካለፋት ቅርብ፣ በተለይ 2 ፣ አመታት ጀምሮ ኢትዮጵያ በርካታ የጦርነት አውድማዎች/ ግምባሮች በጀግናው የመከላከያና ጥምር ጦረ በጀግንነት እያሸነፈች ትገኛለች። እነዚህን የጦር አውድማዎች እየመሩ የሚገኙ ደግሞ ብዙ ህይወታቸውን ለሀገራቸው አሳልፈው ለመስጠት ወደ ሁኋላ የማይሉ ከተራ ወታደር እስከ እስከ ፊልድ ማርሻል ርከን ድረስ ያሉ ጀግኖች ሲኖሯት ፤ ሌሎች ደግሞ በተለያዩ በየተሰማሩባቸው የሙያ ዘርፎች ሀገርን የማገልገል ጀግንነትን የተላበሰ ሚና እየተጫወቱ ያሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ እሙን ነው። በዚህ መሀል በተለየ አቅም ፣ጥረትና ውጤት በማስመዝገብ በዘልማድ "ያልተዘመረላቸው ጀግኖች" የምንላቸው ነገር ግን እውቅና ያልሰጠናቸው ወይም የነፈግናቸው ህዝብ አንቂዎች፣ጋዜጠኞችንና ሌሎችም የህብረተሰባችን አካላትን እናገኛለን። ከነዚህም መሀከል ከፍተኛ ትግልና መስዋትነት የከፈለና እየከፈለ ያለ ጀግና እንዳንዘነጋ ለማስታውስ ወደድኩኝ ፣ መምህር/የሰብዐዊ መብት ተሟጋቹ ስዩም ተሾመ። ስዩምን መቼም ለወያኔዎች ማስተዋወቅ ለቀባሪው ማርዳት ነው፣ ለሌሎቻችን ግን ባጭሩ ስኬቱን በሚያንፀባርቅ ሁኔት የሚገርም ፅናት፣ትግስት፣ትህትና ግዙፍ የሞራል ልዐልና ያለው እንቁ ዜጋችን ነው ። የስዩም ዩትዩብ ፣ፌስቡክ፣ትዊተር አካውንቶቹ ከነ-በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ተከታዮቹ ስንት ጊዜ እንደተዘጉበት ታቃላቹ? - ይሄ ብቻውን ደግሞ ስለ ስዩም እልፍ ይናገራል። ፣በወያኔ ስርዐት ከማስተማር ስራውስ ወደ እስር ቤት ተጥሎ እንደነበርስ?፣ወያኔን በመጨረሻ ካዲስ አበባ አሽቀንጥሮ ለመጣ ትልቅ ሚና የተጫወተው የኦሮ-አማራ ጥምረት አፍላቂ መሁኑንስ?በርግጥ ከኦሮ-አማራ በፊት ወያኔን ለመጣል ብዙ ቅድመ ስራዎች በተለያዩ ቡድኖች ተሰርተዋል። እንደኔ እንደኔ ስዩም ብዙ ላገር ዉሏል። ከወትሮው በሀገራችን ለየት ባለ ሁኔታ ፣ ስዩም አስተማሪ ነኝ ተምሪያለሁ ብሎ ሳይመፃደቅ አንዳንዴ የህብረተሰቡ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ ዝቅና ጠለቅ ብሎ በመግባት ማብራሪያና ገንቢ ጥቆማዎችን በመሰጠት፣በሌል በኩል ደሞ ፣ በኔ አመለካከት ትልቅ ስራ ብዬ የምወስደው ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ፣ በውጭ የሚኖሩትንም ጨምሮ ስለ ምስራቅ አፍሪካና አለም አቀፍ ጂኦፖለቲክስ በመተንተን ከፍተኛ የሆነ የአስተሳሰብ ለውጦችን አምጥቷል ብል ማጋነን አይመስለኝም። ለማወቅ ፣ እውነትና ውሸትን ለመለየት ለሚፈልግና ፈቃደኛ ለሆነ ሁሉ ስዩም በቂ ማስረጃዎችን ያቀርባል በዚህም በብዙ ሀገር ወስጥና ውጪ የሚኖሩ አድማጮቹን ቀልብ ስቧል ፣ በኔ እምነትም የብዙ ሀሳብ ብዥታዎችንም አጥርቷል። ለዚህ ስራው እና ታላቅ ስብዕናው ተገቢውን ስፍራ ሊሰጠው ይገባል።
ጀግኖቹን የማያከብር ትውልድ የጀግና መሀን ይሆናል!!
ስዩም ሙሁር ነው ፤ስዩም ጀግና ነው!
Thank you Seyoum for your hardwork and information with great value!
TheManWhoSawTomorrow