Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Axumezana
Senior Member
Posts: 19217
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: Shocking : ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ለመቀጠር በቅድሚያ 180, 000 ብር ጉቦ ተጠየቀ

Post by Axumezana » 19 Nov 2022, 03:36

ይኸ፥ ሙስና፥ ድሮም፥ የነበረ፥ ቢሆንም፥ በአብይ፥ ጊዜ፥ ደግሞ፥ ክንፍ፥ አውጥቶ፥ እየበረረ፥ ነው፥ አብይ፥ ወንበሩን፥ ለመጠበቅ፥ 24/7 ተግቶ፥ እንደሚሰራ፥ ሙስናን፥ ለመዋጋት ደግሞ፥ እንዲሁ፥መስራት፥ አለበት።

ዛሬ፥ ሙስና፥ የበዛበት፥ ምክንያት።

- ትክክለኛ፥ የስራ፥ ምዘና፥ የለም
- አለቃና፥ ሰራተኞች፥( ከላይ፥ ወደ፥ ታች) ሁሉም፥ ሙሰኞች፥ ናቸው፥ ተሰማምተው፥ ነው፥ የሚበሉት።
- ጠያቂም፥ ተጠያቂም፥ የለም።
- ባለጉዳዮች፥ ተገደው፥ ጉቦ፥ እንዲከፈሉ፥ ሲደረጉ፥ አብየት፥ የሚሉበት፥ የለም፥
- ለመንግስት፥ ገንዘብ፥ አዋጡ፥ የሚሉ፥ የቀበሌ/የሰፈር፥ ሹመኞች፥ በመንግስት፥ ስም፥ ያለደረሰኝ፥ በየሰፈሩ፥ ሲሰበስቡ፥ የሚቆጣጠር፥ የመንግስት፥ አካል፤ የለም።
- ጉበኞች፥ በፓለቲካ፥ ታማኝነታቸው፥ ከለላ፥ ያገኛሉ።

አዳዲስ፥ አሰራሮች፥ ከአለም፥ አቀፍ፥ ልምድ፥ ተቀስሞ፥ በኤንፎርሜሽን፥ ቴክኖለጂ፥ ታግዞና፥ ተገልጋዩን፥ህብረተሰብ፥ ማዕከል፥ ያደረገ፥ የስራ፥ ምዘና፥በመስራ፥ ቤት፥ በዲባርትመነንት፥ በየአንዳንዱ፥ ሰራተኛ፥ ለማድረግ፥ የሚያስችል፥ ስርአት፥ ቢኖርና፥ ተግባራዊ፥ ቢደረግ፥ ምዘናውም፥ የሚደረገው፥ ማንም፥ በማያውቃቸው፥ (ህቡእ፥የሆኑ) ከየመንግስት፥ መስራቤቱ፥ ውጭ፥ ሆነው፥የየአንዳንዱን፥ መስርያቤት፥ ዲባርትመንትና፥ ሰራተኛ፥ የስራ፥ክንውን፥ መመዘን፥ከተቻለ፥ ዛሬ፥ በየጨለማ፥ ውስጥ፥ሁኖ፥ እየተሰራ፥ ያለው፥ ሙስና፥ ያበቃለታል፤ ለምሳሌ፥
እንድ ፥ ግብር፥ ከፋይ፥ ግብር፥ በዛብኝ፥ ብሎ፥ ለገቢዎች፥ ቢያመለክት፥
ገቢዎች፥ ለአመልካቹ፥ የአመለከተበት፥ የመለያ፥ ቁጥር፥ በኮምፒተር፥ ተመዝግቦ፥ ይሰጠዋል፥ መርምሮ፥ ውሳኔ፥ ለመስጠት፥ ስንት ፥ ቀን፥ እንደሚፈጅበትም፥ ጊዜ፥ ገደብና፥ ጉዳዪን፥ የሚፈጽመው፣( የሚያስፈፅመው) ሰራተኛ፥ስም፥ ዲፓርትመንቱ፥ የአመልካች፥ ስምና፥ አድራሻ፥ አብሮ፥ይገለፃል፥ ምርመራው፥እንዳለቀ፥ የምርመራው፥ ውጤት፥ ይመዘገባል፥ ያለቀበትም፥ቀን ተመዝግቦ፥ ደምበኛውም፥ ውሳኔ፥ያገኛል። በህቡእ፥ ጉዳዮን፥የሚከታተለው፥ የመንግስት፥ድርጅትም፥ ከአመልካቹ፥ ጋር፥ በስልክ፥ በኢሜል፥ በቴክስት፥ያለውጉዳዩ፥ እስኪዘጋ፥ ደረስም፥ሆነ፥ ጉዳዩ፥ ከተዘጋ፥ በኻላ፥ በህቡእ፥ የሚገናኝ፥ ሲሆን፥ ሙስና፥ መሰራቱን፥ / ሊሰራ፥ መሆኑን፥ ከተጠራጠረ፥ ከፍርድ፤ ቤትና፥ ከፖሊስ፥ ጋር፥ ሁኖ፥ ተጠርጣሪው፥ ላይ፥ እርምጃ፥ እንዲወሰድ፥ ያደርጋል።
በህቡእ፥ የሚከታተለው፥ ክፍል፥ ከገቢዎች፥ ጋር፥ አብሮ፥ ሙስና፥ እንዳይሰራ፥ የሚዘረጋው፥ የኢንፎርሞሽን፥ ሲስተም፥ ቀዳዳዎች፥ መደፈን፥ አለባቸው።

Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: Shocking : ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ለመቀጠር በቅድሚያ 180, 000 ብር ጉቦ ተጠየቀ

Post by Wedi » 19 Nov 2022, 05:07

Thomas H wrote:
18 Nov 2022, 22:46


Shocking : ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ለመቀጠር በቅድሚያ 180, 000 ብር ጉቦ ተጠየቀ


አዲስ አበባ በሚገኝ ንግድ ባንክ ለመቀጠር የተጠየቀው ጉቦ 180, 000 ብር ብቻ ከሆነ እጅግ እርካሽ ነው ማለት ነው፡፡

በክልል ከሚገኙ ከተሞች ውስጥ ባለ አንድ የንግድ ባንክ ውስጥ ለመቀጠር ያመለከተች የእኔ እህቴ 150 000 ብር ካልከፍለሽ አይሆንም ስለተባለች ለመክፈል ተስማምታ በሂደት ላይ ነች!!

ኢትዮጵያ እኮ በሙስና ተጨማልቃ እጅግ የምታሳዝን አገር ሆናለች!!

Post Reply