Page 1 of 1

የማትሄድ መበለት በየዕለቱ ትሰናበት!

Posted: 15 Nov 2022, 15:21
by Horus
እስቲ የኢ አር ቅኔ ቀመስ ታዳሚዎች ይህችን ረቂቅ አባባል ፍቷት :idea: :idea: :?: :lol:

https://www.yahoo.com/news/icrc-humanit ... 06134.html

Re: የማትሄድ መበለት በየዕለቱ ትሰናበት!

Posted: 15 Nov 2022, 15:38
by Wedi
Horus wrote:
15 Nov 2022, 15:21
እስቲ የኢ አር ቅኔ ቀመስ ታዳሚዎች ይህችን ረቂቅ አባባል ፍቷት :idea: :idea: :?: :lol:

https://www.yahoo.com/news/icrc-humanit ... 06134.html
ባሏ ፡ የሞተባት ፡ ሴት

Re: የማትሄድ መበለት በየዕለቱ ትሰናበት!

Posted: 15 Nov 2022, 15:50
by Abere
ይችን የጥንት እንጉርጉሮ አስታወስከኝ። ከመበለቲቱ ምሳሌዊ አነጋገር ጋር ምንልባት መሳ ይሆን?!

እሄዳለሁ ማለት - እኖራለሁ ነው፥
የሚሄድማ ሰው - እብስ ጥርግ ነው።

ሆረስ የዘምድ ድብድን ጨርቅ ይጨርሳል ይባላል። የወያኔ እና የኦነግ ድብድብ(ጨዋታ ፍትጊያ) ምንም ጥሩ ነገር ወይም ቅቤ ላይወጣው ሚልዮኖችን አስጨረሰ- አፈናቀለ። የዐባይ ትግራይ ህልመኞች - ህልም እልም ህልም እልም ያሉ መልሰው ደግሞ ያልማሉ።

Horus wrote:
15 Nov 2022, 15:21
እስቲ የኢ አር ቅኔ ቀመስ ታዳሚዎች ይህችን ረቂቅ አባባል ፍቷት :idea: :idea: :?: :lol:

https://www.yahoo.com/news/icrc-humanit ... 06134.html

Re: የማትሄድ መበለት በየዕለቱ ትሰናበት!

Posted: 15 Nov 2022, 15:55
by Horus

Re: የማትሄድ መበለት በየዕለቱ ትሰናበት!

Posted: 15 Nov 2022, 16:12
by Horus
ወዲ፣
በፍጹም አልደረስክበትም!

በትክክል የፈታው አበረ ነው፤ ፍቺው ያለው "የሚሄድማ ሰው - እብስ ጥርግ ነው።" እሚለው ነው ። መበለት አንዲት ቀላዋጭ በድሜ ጠና ያለች ሴት ናት ። በእንግድነት አንድ ሰው ቤት እያደረች ነው ። ዛሬ እሄዳለሁ ትልና መሰናበቻ ከበላች በኋላ ሃሳቧን ለውጣ ታድራለች ። ደሞ በማግስቱ ዛሬ መነሳት አለብኝ ትልና የመንገዷን ካበሏት በኋላ ባንድ ምክንያት ሃሳቧን ለውጣ ታድራለች! ያ ሲሆን ነው ያገሬ ነገር አዋቂ 'የማትሄድ መበለት በየለቱ ትሰናበት' የሚለው ። ታዲያ ይህቺ መበለት ዛሬ ላይ ማናት?

Re: የማትሄድ መበለት በየዕለቱ ትሰናበት!

Posted: 15 Nov 2022, 16:44
by Horus
ይህቺ መበለት መቼ ነው የምትሄደው?