Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15453
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የሆረስ አገላለጽ በጣም ትደንቀኛለች- <<ትግሬ ተዋግቶ ተዋግቶ በእራሱ ያቆማል።>> አባባሉ ይህንም ሳይጨምር አይቀርም <<በእራሱ ጊዜ ደግሞ ወፈፍ አድርጎት ደግሞ ያገረሽበታል።>>

Post by Abere » 13 Nov 2022, 18:39

የሆረስ አገላለጽ በጣም ትደንቀኛለች- <<ትግሬ ተዋግቶ ተዋግቶ በእራሱ ያቆማል።>> አባባሉ ይህንም ሳይጨምር አይቀርም <<በእራሱ ጊዜ ደግሞ ወፈፍ አድርጎት ደግሞ ያገረሽበታል።>> የእብድ ፀጉር ቅቤ አይዝም ይባላል። ታርቀናል- አልታረቅንም :lol: :lol: :lol: ትግሬ ሳይሆን ይህን ጦርነት ማቆም የምንችለው ሌሎች ኢትዮጵያዊያኖች ነን። የዚህ ውል ደግሞ የወያኔን እጭ የሆነውን የዴደቢት ህገ-መንግስት አሽቀንጥሮ በመጣል የግጭት ገንዳ የሆነውን የጎሳ ክልል ማፈራረስ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42840
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሆረስ አገላለጽ በጣም ትደንቀኛለች- <<ትግሬ ተዋግቶ ተዋግቶ በእራሱ ያቆማል።>> አባባሉ ይህንም ሳይጨምር አይቀርም <<በእራሱ ጊዜ ደግሞ ወፈፍ አድርጎት ደግሞ ያገረሽበታል።>>

Post by Horus » 13 Nov 2022, 22:26

አበረ ይላል፤ "ትግሬ ሳይሆን ይህን ጦርነት ማቆም የምንችለው ሌሎች ኢትዮጵያዊያኖች ነን።" እጅግ እጅግ ትክክል!

ይህውልህ አበረ! ብልጽግና የሚባለው ፓርቲ እንደ ድሮ ነጻ ሆነው የተደራጁ (ለስሙም ቢሆን) ድርቶች ፌዴሬሽን ግምባር ኢህ አ ዴግ ሳይሆን ወጥ ፓርቲ ነው ። ማለትም በመርህ ደረጃ የፒፒ አባላት እንደ ግለሰብ ነው አባል የሆኑት ። ለዚህ ነው አቢይ በፈለገ ግዜ አንድ የጋሞ፣ ያማራ ወይም ጉራጌ አባል ገምግሞ ከፓርቲው የሚያባርርው!

አሁን በዚህ የመንግስትና ትግሬ ድርድር ሁሉም ነገር እንደ ተባለው ሆንኪ ዶሪ ሆነ እንበል! የትህነግ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? በእርግጠኝነት የሚሆነው የሚከተለው ነው። ዛሬ ትግሬን የሚገዙት በነፍስ ወከፈ ፎርም ሞልተው የብልጽኛ አባል ሆነው የትግሬ ክልል ቅርንጫፍ ይሆናሉ ። ይህን ካደረጉ አመት ባልሞላ ግዜ ውስጥ አቢይ የማይፈልጋቸውን ትግሬዎች ሙልጭ አድርጎ በግምገማ ይሸኛቸዋል ! ለዚህ ነው እኔ የዛሬ ስንት ወር ጥህነግ በፍጹም ብልጽግናን አይዋሃድም ያልኩት ። እኔ ትህነግ ፒፒን ከተቀላቀለ የሰላም ሞት ሞተ ማለት ነው ብያለሁ ።

ትህነግ የሚፈልገው ትላንት ያለውን ነው፤ እሱም ለብቻው በምርጫ ቦርድ የታወቀ በሰላማዊ ዘዴ የሚታገል የትግሬ ፓርቲ ሆኖ በትግሬ ክልል ውስጥ ለመወዳደር ነው !!! እንደ ሚያሸንፍ ደሞ 100% ነው ። ለዚህ ነው በፍሬሚንግ ደረጃ ትህነግ ከትግሬ መንግስትም፣ ከትግሬ ጦርም ነጻ ነኝ ያለው ትላንትና!!! ይህ ማለት ደሞ ትህነግ እስከ ዛሬ ለሰራቸው ወንጀሎች ሁሉ ተጠያቂ አይሆንም ማለት ነው ። መሪዎቹም ወደ ፊት መከሰስ አይችሉም ፣ ንብረታቸውም መመለስ አለበት ማለት ነው !!

ብቻ ምን ያረጋል ይህን ጂል ፒፒ ቀስ እያሉ ትብታብ ውስጥ እያስገቡት ነው ።

ስለሆነም ዛሬ ላይ አቢይ የትግሬን ችግር ተረክቦ ትግሬን መመገብ የእሱ ራስ ምታት እንዲሆን ፈቅዶ ፈርሟል ። አሁን እርዳታና አገልግሎት ከመስጠት ወደ ኋላ ቢያፈገፍግ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ኪሳራ ላይ ይወድቃል ። ትህነግ ባንጽሩ ያሸንፋል ።

ስለዚህ በትግሬ ሽግግር መንግስት ወቅት የሚሆነው ሆኖ የትግሬ ምርጫ ሲደረግ ህጋዊው ከፒፒ ወጭ ያለው የትግሬ ፓርቲ ማለትም ትህነግ አሸንፎ ትግሬን ወክሎ አዲሳባ ይመጣል ። ይህ እንዳይሆን አቢይ ሊያደር የሚችለው ትህነግ ወይም ባዲስ ስም የሚጠራው ትህነግ በምርጫ ቦርድ ተቀባይነት እንዳያገኝ ማድረግ ነው። ያ እንዴት እንደ ሚሆን አላቅም። ዛሬ ትህነግ ያሸባሪነት ታፔላው ሁሉ የተነሳለት ይመስለኛል ።

ብቻ ምን ያደርግልሃል! በዚህ ረቂቅ የቼስ ጨዋታ ፒፒ ከወዲሁ ንጉሱና ንግስቲቱን እያስበላ ነው ።

ቁም ነገሩ ...

ይህ እጅግ ረምጅ ተከታታይ የትግሬ ድራማ ፍጻሜ የሚያገኘው ልክ ባልከው መንገድ ነው! "ትግሬ ሳይሆን ይህን ጦርነት ማቆም የምንችለው ሌሎች ኢትዮጵያዊያኖች ነን።"

Post Reply