ሁለት ሕልም የሚያዩ ባንድ አልጋ ይተኛሉ
Posted: 12 Nov 2022, 13:45
የደቡብ አፍሪካው ስምምነት መሰረት የትግሬዎች ዉጊያ አላማ ቢስና የትም የማይሄድ ስለነበረ ሲሆን ያቢይ መንግስትም የትግሬን ችግር በዉጊያ እንደ ማይፈታው ይታወቅ ስለነበረ ነው። ይህም ስለሆነ ነው እኔ ሆረስ በስምምነቱ አሸናፊ የለም፤ ሁለቱም ተሸናፊዎች ናቸው ያልኩት ። ሁለቱም በሪያሊቲ የተሸነፉ ናቸው። ያ ደሞ ጥሩ ነገር ነው ። ትህነግና ፒፒ በሪያሊቲ ሲሸነፉና ለሪያሊቲ ሲምበረከኩ አንዱ ተነስቶ (በተለይ የፒፒ ቲፎዞች) እንደ አሸናፊ ሆያ ሆዬ ክልክል ነው።
አሸናፊ እንደ ሌለ የሚታወቀው ሁለቱ የጦር መሪዎች በኬኒያ ንግግር ሲያደርጉ የድምጻቸው ድክመትና መንቀጥቀጥ በውስጣቸው ያለውን አላሸናፊነት ስሜት ይገልጻል ። ጄ/ል ብርሃኑ ስለ ትጥቅ ማስፈታት ተናገረ፤ ታደሰ ስለ እርዳታ ተናገረ፤ ግን ሁለቱም የፈረሙት አንድ ቃል ነው ። ስለዚህ ትህነግና መንግስት በውዴታ አልተስማሙም፣ በግዴታ ነው ያለውን ሪያሊቲ የተቀበሉት ። ይህን ማለት ደሞ ከዛሬ ጀመሮ እና ወደ ፊት ሌላ መንገድ፣ ሌላ ጉዳይ እያንሱ ትግላቸውን ይቀጥላሉ ማለት ነው ።
ስለዚህ ነው ሁለት ህልም ያላቸው ሰዎች ባንድ አልጋ ይተኛሉ የሚባለው ። ቲፎዞዎች ግን በህልምና አልጋው መሃል ያለው ልዩነት አይገባቸውም! በውን የሚስማሙ ሁለት ሰዎች አንድ አይነት ሕልም ያያሉ! ሁለት ጠላቶች እንኳ አንድ አልጋ ላይ ሊተኙ ስለሚችሉ ።
ተዋግተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ ይባላል እንጂ ተዋግተው ተዋግተው አንዱ አሸነፈ አይባልም፣ በዚህ የትግሬ ዉጊያ! ታዲያ ያሸናፊነት ሆይ ሆይታ ምን አመጣው?