Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37233
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብዓዊ ደጋፍ አቅርቦት ክፍት መደረጋቸው ተገለጸ(((PP Must Slow Down, Never Trust Agames))!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 11 Nov 2022, 11:20

Natnael Mekonnen
17m ·
Good News ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብዓዊ ደጋፍ አቅርቦት ክፍት መደረጋቸው ተገለጸ
ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብአዊ ደጋፍ አቅርቦት ክፍት መደረጋቸውን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ለተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች የሰሜን ኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያቀርቡ ተቋማት የየብስም ሆነ የአየር ትራንስፖርት ክፍት መደረጉን ገልጸዋል።
በአፋር ክልል ከአብዓላ መቀሌ፣ በሁመራ በኩል ሽራሮ፣ ሽሬ አክሱም አድዋ፤ በጎንደር አዲ አርቃይ ማይጸምሪ ሽሬ እንዲሁም የወልዲያ አላማጣ መስመሮች ሁሉም ለሰብዓዊ እርዳታ ክፍት እንደሆኑ ተናግረዋል። በአፋር ክልል ከአብዓላ መቀሌ የሙከራ አገልግሎት የሰጠ ሲሆን በሁመራ በኩል ሽራሮ፣ ሽሬ አክሱም አድዋ በኩል ከገቡ 16 ከባድ መኪናዎች መካከል ሶስቱ የሕክምና ቁሳቁስ ይዘው መግባታቸውን አመልክተዋል። “ማንኛውም የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ተቋም በአየርና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ይችላል” ማለታቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡



Post Reply