Page 1 of 1

^^^{{{JUST IN}}}^^^:በኬንያ እየተካሄደ ያለው የሠላም አፈፃፀም ንግግር በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል!!! WEEY GUUD !!!

Posted: 11 Nov 2022, 10:00
by tarik
Natnael Mekonnen
25m ·
በኬንያ እየተካሄደ ያለው የሠላም አፈፃፀም ንግግር በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል::
የደቡብ አፍሪካ-ፕሪቶሪያውን የሠላም ስምምነት ተከትሎ፤ ከዕለተ ሰኞ ጀምሮ ለአምስት ቀናት በመንግሥት እና በህወሓት ታጣቂ አመራሮች መካከል በኬንያ-ናይሮቢ ከተማ ላይ በሚገኘውና ካረን ሞራን ማዕከል ውስጥ በዝግ እየተካሄደ ያለው የሠላም ንግግሩ አፈፃፀም በዛሬው ዕለት ይቋጫል ተብሎ ይጠበቃል። በንግግሩ ማጠቃለያ ላይ በሁለቱ ወገኖች መካከል ስለነበረው ሂደትና ስለውጤቱ ለጋዜጠኞች መግለጫ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል። ሠላሙን ሁሉ ለእናት ኢትዮጵያ እንመኛለን‼