Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42840
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አባይ እንደ ኮሬንቲ

Post by Horus » 09 Nov 2022, 21:36

ሃባይ አቢ አባት አባይ
ያለም ፈጣሪ ብርሃነ ፀሃይ
አባይ የኢትዮጵያ ኩራዝ
አይነ ኩሉ ያገር መቅረዝ
የእናታችን ነዳጅ እንጨት
ከሰል ቅጠል ፈሳሽ እሳት
የማግኔት ልጅ አባ ንደት፤
እመ ሙቀት ነፍሰ ፍጡር
የስልጣኔ ነጂ ሹፌር
አባ ብርሃን ያለም ኢምር፤
የምድራችን ዕጹብ ፈፋ
ሃይለ ነገር ፍካተ ፏ ፋ
አባይ የጽልመት ጽኑ ጠላት
የሰማየ ሰማያት በራት።

ሆረስ ዘኢትዮጵያ
ፌብሯሪ 22 2022

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14414
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: አባይ እንደ ኮሬንቲ

Post by Abe Abraham » 10 Nov 2022, 10:42

Horus wrote:
09 Nov 2022, 21:36
ሃባይ አቢ አባት አባይ
ያለም ፈጣሪ ብርሃነ ፀሃይ
አባይ የኢትዮጵያ ኩራዝ
አይነ ኩሉ ያገር መቅረዝ
የእናታችን ነዳጅ እንጨት
ከሰል ቅጠል ፈሳሽ እሳት
የማግኔት ልጅ አባ ንደት፤
እመ ሙቀት ነፍሰ ፍጡር
የስልጣኔ ነጂ ሹፌር
አባ ብርሃን ያለም ኢምር፤
የምድራችን ዕጹብ ፈፋ
ሃይለ ነገር ፍካተ ፏ ፋ
አባይ የጽልመት ጽኑ ጠላት
የሰማየ ሰማያት በራት።

ሆረስ ዘኢትዮጵያ
ፌብሯሪ 22 2022

የኣንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኣማርኛየን ይዤ ግጥምህን ሳነብ የበቀይ ያሉትን ቃላቶች ትርጉም ፈልጌ ፡ በቅደም ተከተል ፡ የሁለቱን ተሳክቶልኝ በእግረ መንገዴ - በትግርኛ እንደምንለው - ወደ " ውታፍ ነቃይ " ከየት መጣ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ኣመራሁ ።

የሚገርመው ኣረቦች ፡እንደሚባለው፡ የመቅረዝ ትርጉም ከፋርሰኛ የወሰዱት ቃል " ሸምዒዳን " -- ( ከሻማ-ኣማርኛ/ሽምዓ-ትግርኛ ) ግኑኙነት ያለው የሚመስል -- ቃል ሲኖራቸው ዋነኛው የኣረብኛ ቃል ( ማሲላ)ና የኣማርኛው መቅረዝ በቀጥታ ከሻማ የሚለውን -- ሴማዊ መሰረት ያለው ቃል -- ግንኙነታቸው ኣይታየህም ። መቅረዝ ከየት መጣ ? ከግእዝ ነው ወይ ?

-

Horus
Senior Member+
Posts: 42840
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አባይ እንደ ኮሬንቲ

Post by Horus » 10 Nov 2022, 14:20

Abe Abraham wrote:
10 Nov 2022, 10:42

ሰላም አቤ ኣብርሃም፣
ግሩም ጥያቄ!
እኔ አረብኛ ስለማልችል በጣም ዲሳድቫንቴጅ አለብኝ፤ እናም አረብኛ በምትችሉ ላይ እቀናለሁ ። ያሰመርክባቸው ቃላት ኩራዝ፣ መቅረዝ፣ ፋ እና ፏ ከሁለት ኢቲሞሎጂ ይቀዳሉ ።
ኩራዝና መቅረዝ አማርኛና ግዕዝ ከመሆን በተቀር አንድ ናቸው። ኡር ከሚለው ጥንታዊ ሴም ቃልና ከዚያ በፊት ራህ/ራዕ ከሚለው የቀምጥ (ጥንታዊ ኮፕት) ቃል የወረደ ነው ። እሱም ብርሃን (ፀሃይ) ማለት ነው ። ዑር ማለት በዕብራይስጥ ብርሃን ማለት ነው ። ለምሳሌ እኛ እሁድን ዑርሰበት ነው የምንለው ። ስለዚህ ኩራዝ፣ ኡራዝ፣ ቁራዝ (መቁራዝ/መቅረዝ) እያሉ እዝቦቻችን እንደ ልሳናቸአ ድምጽ አጠቃቀም ለየት አደረጉት እንጂ ሁሉም ብርሃን ማለት ነው ።

ፋ እና ፏ የሚለው እጅግ ጥንታዊ ነው ። ይህም ከግብጽ ተነስቶ በሴም ቋንቋም በላቲም ውስጥ አለ ። ባ፣ ፓ፣ ወይም ፋ መከፈት፣ መገለጽ፣ መታየት፣ ሻይን ማድረግ ማለት ነው። ፍካት ያው ፈካ (በራ) ማለት ነው። አብርሃም በሚለው ስምህ ውስጥ ያለው ባ እሱ ነው! በራ (shining light) ማለት ነው። ዛሬ ፋኖስ፣ ፋና የምንለውና ፈረንጆች ፌኖማ፣ ኤፒፋኒ፣ ፌኖሜና የሚሉት አንድ ቃል ነው። እጅግ ብዙ እርባታ ያለው ስረቃል ነው ። ለምሳሌ በግዕዝ ቦ (ሆነ) የምንለው እሱ ነው፤ ተከሰተ፣ ታየ፣ ሆነ ማለት ነው ቦ ነገር ይሏል በግዕዙ! ።

ኢምር ጉራጌኛ ነው፤ እጅግ ውብ የሆነ የኮከብ ብርሀን ነው፣ ውብ የጸሃይ ብርሃንም ዬምር/ኢምር ይባላል።
በራት በጉራጌኛ እንደ ችቦ፣ ኩራዝ፣ የሚያዝ ብርሃን ነው ።
ፈፋ በጉራጌኛ አንድ አስገራሚ እጹብ ድንቅ ትዕይንት ማለት ነው ።
ኬር
Last edited by Horus on 10 Nov 2022, 14:47, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42840
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አባይ እንደ ኮሬንቲ

Post by Horus » 10 Nov 2022, 14:45

አቤ አብርሃም፣
የረሳሁት ነገር!

ሻማ ትክክል ነህ፣ እሱም ብርሃን ማለት ነው ። አንዱ ትልቁና በመላ ቅርብ ምስራቅ ከጥንት ጀምሮ ያለው የጸሃይ (ብርሃን) ስም ሰምስ፣ ሸምስ (እኛ ሰማይ የምንለው) ነው ። ለምሳሌ ጻሃይ የምለው ስረ ቃሉ ሸማስ/ሸምስ ነው። ስለዚህ ሻማ በትክክል ድሮ የጸሃይ ብርሃን ነበር ። ጧፍ ማለት ግን ከላይ በጠቀስኩት ባ፣ ፋ፣ ፏ ከሚለው የመጣ ነው ።

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14414
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: አባይ እንደ ኮሬንቲ

Post by Abe Abraham » 13 Nov 2022, 17:16

Horus wrote:
10 Nov 2022, 14:45
አቤ አብርሃም፣
የረሳሁት ነገር!

ሻማ ትክክል ነህ፣ እሱም ብርሃን ማለት ነው ። አንዱ ትልቁና በመላ ቅርብ ምስራቅ ከጥንት ጀምሮ ያለው የጸሃይ (ብርሃን) ስም ሰምስ፣ ሸምስ (እኛ ሰማይ የምንለው) ነው ። ለምሳሌ ጻሃይ የምለው ስረ ቃሉ ሸማስ/ሸምስ ነው። ስለዚህ ሻማ በትክክል ድሮ የጸሃይ ብርሃን ነበር ። ጧፍ ማለት ግን ከላይ በጠቀስኩት ባ፣ ፋ፣ ፏ ከሚለው የመጣ ነው ።
Etymology is extremely important. It gives sense to words. The meaning of some words are self-evident while others demand from you more search and delving. Take for instance the word predicament and its long history of transformation!!

ያለነው ኣርእስት ስለ ቃላቶች ስለ ሆነ " ጨ " የሚባለው ፊደል እንዴት ብሎ ለምሳሌ በ " ጨለማ " ና " እንጨት " ገባ ? ሁለቱ ቃላቶች መሰረታቸው ሴማዊ ሲሆን ሴማውያን ግን " ጨ "ን ኣይጠቀሙም ።

-

Horus
Senior Member+
Posts: 42840
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አባይ እንደ ኮሬንቲ

Post by Horus » 13 Nov 2022, 17:55

Abe Abraham wrote:
13 Nov 2022, 17:16

አቤ ሰላም!
ቀ፣ ጨ፣ ጸ፣ ጠ፣ ጰ፣ የሚባሉት የወፍ ድምጾች የሴም ቋንቋ ድምጾች አይደሉም ። የኢትዮጵያ ሴም ቋንቋዎች ከአገውኛ የወሰዱት ነው ። ይህ ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሰዋስው እራሱ የአገውኛ ነው እንጂ የሴም አይደለም። ለምሳሌ በአረብኛ ወይም በእብራይስጥ "አቤ አብርሃ ጠየቀ ጥያቄ" ነው የሚሉት ። ማለትም ሳብጀክት .. ቨርብ .. ኦብጀት ነው ። እኛ ግን "አቤ አብርሃም ጥያቄ ጠየቀ" እንላለን ። ማለትም ሳብጀክት .. ኦብጀክት .. ቨርብ ። ይህ የኩሽ (አገውኛ) ሰዋስው ነው ።

ጥያቄህን ለመመለስ "ጨለማ" ውስጥ ያለው 'ጨ' ካገውኛ የመጣ ነው ። የቃሉ ሴሚቲክ ስር 'ከል' የሚለው ነው 'ጨል' የሆነው ። ከል ጥቁር ማለት ነው ። በሃዘን ከል (ጥቁር) ልብስ ይለበሳል። በሂንዲ ሳንስክሪትም 'ካሊ' ማለት ጥቁር ወይም ጨለማ ማለት ነው ።

የእንጨት ኢቲሞሎጂ ገና ሪሰርች ስላላደረኩት 'እንጨ፣ እንከ፣ ወይም እከ' ከምን እንደ ተነሳ ዛሬ ልነግርህ አልችልም ። እንጨ ወስጥ ያለው 'ነ' በዘልማድ ቃላትን ለማቅለል የገባ ነው እንጂ ዋናው ቃል 'እጨ' ወይም 'እከ' ነው ። ስሩን ሳገኘው እነግርሃለሁ ።

ልብ በል ፤ ከል .. ቀል .. ጨል ወዘተ ። ቀልም የዚያ ዘር ነው ። ለምሳሌ ነጭ ነገር ድሮ ቀለም የለው ይባል ነበር ። ከል፣ ጥቁር፣ ጨለማ ነገር ግን ቀለም አለው!!!
ኬር

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14414
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: አባይ እንደ ኮሬንቲ

Post by Abe Abraham » 13 Nov 2022, 18:35

Horus wrote:
13 Nov 2022, 17:55

I think that you are already there. Look what I have found reading a Hebrew-English vocabulary list :

‛āfār = dust
‛ēs = tree

ዕጸ doesn't that sound familiar to us ? I am talking about the ዕጸ(plant) in ዕጸ-ፋርስ !! In Tigrigna እንጨት is ዕንጸይቲ/ዕንጨይቲ with your N inserted between the two main letters.

-

Horus
Senior Member+
Posts: 42840
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አባይ እንደ ኮሬንቲ

Post by Horus » 13 Nov 2022, 23:09

አቤ አብርሃም፣
ብራቮ! የተማረ ይግደለኝ! በትክክል ዲኮድ አደረከው ። 'ከ' የሚለው ያሉት sound shifts የሚከተሉት ናቸው ። 'ከ'፣'ሀ' ፣ 'ገ' ፣ 'ጀ' ፣ 'ቸ' ፣ 'ሸ' ፣ 'ሰ' ፣ 'ጸ' ፣ 'ጠ' 'ጨ' 'ቀ' ፣ 'ተ' ... ከጎሳ ጎሳ፣ ከቋንቋ ቋንቋ የፊደሉ ምስል (ምልክት) ድምጾቹን የለዋውጣል ። ለምሳሌ ያረብኛው 'ክህ' ከነዚህ አንዱ ነው ።

ስለዚህ በትክክል እንዳልከው 'es' ... 'ek' .. 'ech' (enche/እጽ/እንጸ/ እንጨ/ ... ነው ። እንጨት ሰፊክስ ላይ ያለው 'ተ' በግዕዝ የብዝሃነት (ፕሉራላይዝ) ማድረጊያ፣ የትቅል ስምና የነገር ስም ማድረጊያ ነው ። ለምሳሌ ነጻ .. ነጻነት፣ መጽሃፍ .. መጻህፍት ። እናም ዛሬ አስተማርከን! እንጨት እጽ ማለት ሲሆን እጭ የሚለውን ድምጽ የሰጡት አገዎች ናቸው ። አመሰናለሁ!

Naga Tuma
Member+
Posts: 7414
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: አባይ እንደ ኮሬንቲ

Post by Naga Tuma » 16 Nov 2022, 19:16

ሆረስ እና ኣቤ ኣብረሃም፥

በማላዉቀዉ ጥናት ዉስጥ ጥልቅ ማለት ኣይሁንብኝና እንደዚህ ኣይነት ጥናቶች እና ዉይይቶች ለምናቀነቅነዉ የኢትዮጵያ ህዳሴ ወይም ግስጋሴ መሰረት ወይም ዕጽ ናቸዉ ብዬ ኣስባለሁ። ምሁራዊ ዉይይታችሁ ለሀዳሴዉ ወይም ግስጋሴዉ ጥሩ ተስፋን ይሰጣል።

Post Reply