- ሸቤ-የእስር ቤት ወጎች
28 juli 2016 ·
እስር ቤቶች ውስጥ በተለይ ራሳቸውን “ዱርዬ” ብለው የሚጠሩ እስረኞች የሚግባቡበት መንገድ አላቸው። ዱርዬዎች ሲጋራን “ፍሙ” ሐሺሽን ደግሞ “ባዬ” ሲሉ ይጠሩታል። ለሌሎች ነገሮችም ራሳቸው የሰጡት ስያሜ አለ።
“የባዬ ቦጭቅልኝ” ሲተረጎም “የሐሺሽ መግዣ ገንዘብ ስጠኝ” ማለት ነው።
“ሁለት ዳገት ተለመጠ” – “ሁለት ዓመት ተፈረደበት”
“ስድስት ስድስት። ፎግር ከች ብሏል” – “ተው ወይም አቁም። ሲቪል የለበሰ ፖሊስ መጥቷል።”
“አባው ፎርቲ ነው። ቀበሮው ራሷ ሳቢያም የሪጎራ ሰው ነች።” – “እሱ ዕድለኛ ነው ሚስቱ/ፍቅረኛውም ገንዘብ ያላት ብልሀተኛ ናት።”
“አቦ መርሽ ጩቤ ላይ ነን” - “ቁም ነገር እያወራን ስለሆነ ከአጠገባችን ሂድ።”
የየትኛውም ቋንቋ ቃላት እንደሚፈጠሩ፣ እንደሚጎለብቱና እንደሚሞቱ ሁሉ የእስር ቤትና የስርቆት ቃላትም ይወለዳሉ፤ ይሞታሉ። ልዩነቱ የእስር ቤትና የስርቆት ቃላት ውልደታቸውም ሆነ ሞታቸው ፈጣን መሆኑ ነው። ቀደም ሲል ፖሊስ መምጣቱን ለማሳወቅና ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ሌቦች የሚጠቀሙበት ስድስት ስድስት የሚለው ቃል ነይ በላት በሚለው ለመለወጥ የፈጀበት ከጥቂት ወራት የዘለለ አልነበረም።
እነዚህ ቃላት አንዳንዶቹ ከሌሎች ቋንቋዎች የተቀዱ ናቸው። ማች (ክብሪት) እና እሰፒዳም (ፈጣን) ከእንግሊዝኛ የተወሰዱ ሲሆን ለርኪ (ፍቅረኛ/ሴት) ከሕንድኛ፣ የካ (አንድ) ዱ (ሁለት) ከሕንድኛና ከፐርሽያ፣ አሪፍ (አዋቂ/ምርጥ)፣ አያርፍም (አያውቅም) ከዓረብኛ፣ ደቅሷል (ተኝቷል) ከትግሪኛ የተወሰዱና “ማሻሻያ” የተደረገባቸው ቃላት ናቸው።
ሌሎች ቃላት ደግሞ የራሳቸው “ታሪካዊ” አመጣጥ አላቸው። እንጨት ፈላጮች ኳታር ይባላሉ። እንጨት በመጥረቢያ ሲመታ “ኳ” የሚል ድምፅ ያሰማል። ከዚያም “ትርትር” ይላል። ፈላጩ ፈጣን ከሆነ ኳ ትርትር ኳ ትርትር ያደርገዋል። ልምድ ያለው ፈላጭ ከሆነ ደግሞ እንጨቱ ኳ ተረ ኳ ተር ይላል። ከዚህ በመነሳት ፈላጩ ኳታር ተባለ። ይህን ያዩት የጊቢው ሊጥ አቡኪዎች “ከማን እናንሳለን” በሚል ራሳቸውን “ዱባይ” ሲሉ ሰየሙ። በአንድ ጉዳይ ላይ አብዛኛው ሰው ከተስማማ ደግሞ “በሙሉ ድምፅ አልፏል” ለማለት “ኦባማ” ይባላል።
-
Abe Abraham
- Senior Member
- Posts: 14414
- Joined: 05 Jun 2013, 13:00
ስለ ኢትዮጵያችን እስር ቤቶች ድብቅ ገመናና ስለ አስደማሚው ?
https://nl-nl.facebook.com/profile.php? ... 9022068276