Abraha Desta
4h ·
እኛ ተጋሩኮ ህወሓት በደለን ብለን እንቃወመዋለን፤ ሌሎች መሪዎች እንፈልጋለን እንላለን። የአማራ ህዝብ አለ አይደለም እንዴ እስካሁን በብአዴን ሚተዳደረው?! ህወሓትኮ ባይጠቅምም የራሱ ሐሳብ አለው። ብአዴንኮ ህወሓት አማራን ለመግዛት ጠፍጥፎ የሰራው አሻንጉሊት ነው። የአማራ ህዝብ እስካሁን በነዚህ ተላላኪዎች እጅ ነው። ለወደፊትም ተስፋ የለውም፤ ምክንያቱም ብአዴን ቀጥሎ ከሚመጣው መንግስትም ለውጥ ተቀብሎ አማራን የማስገዛት ዕድል አለው። ቢያንስ ተጋሩኮ በህወሓት መጎዳታችን ገብቶናል፤ መሪዎች የመቀየር ዕድል አለን። አማራስ? ከአማራ ጋር ስንነፃፀር እኛ ተጋሩ ተመስገን ማለት አለብን። ህወሓትን ባንፈልግ እንኳ ከብአዴን በመቶ ዕጥፍ ይሻላል።