Page 1 of 1

Agames Nightmare Obosanjo:የሰላም ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው!!! WEEY GUUD !!!

Posted: 04 Nov 2022, 16:07
by tarik
Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

የሰላም ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው-ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የሰላም ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ሲሉ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ተናገሩ፡፡

የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዝዳንትና የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ለኢዜአ እንደተናገሩት በደቡብ አፍሪካ የተካሄደው የሰላም ስምምነት ግጭትን በማስቆም ለዘላቂ ሰላም መስፈን አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው፡፡

ስምምነቱም ችግሮችን በዘላቂነት በውይይት እንዲፈቱ የሚያስችል በመሆኑ ሁሉም አካላት ለተፈጻሚነቱ በጥበብና አገር ወዳድነት ስሜት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በደቡብ አፍሪካ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በህወሓት መካከል ሲካሔድ የቆየው ውይይት የኢትዮጵያ ህዝቦችን የጋራ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ስምምነቱ በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የታጠቀ ሀይል ሊኖር እንደማይችል ያስቀመጠ ሲሆን፣ የህወሓት ታጣቂዎችም ትጥቅ የሚፈቱ ይሆናል።

በትግራይ ክልል መሰረታዊ አገልግሎት እንዲጀመርም ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡