ስለ ባህል ተምሬ ኣላጠናሁም። ስለ ሃይማኖትም ተምሬ ኣላጠናሁም። ነገር ግን ሁለቱንም እያያሁ እና እያስተዋልኩ ነዉ ያደኩኝ።
ከወጣትነት እድሜዬ ጀምሮ እስከኣሁን ያለ ክርከር ኣለ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እና ፕሮቴስታንት ሃይማኖቶች መካከል ያለዉ ክርከር። የእስልምናዉን ብዙ ኣላዉቅም። በሰፊዉ ኣከባቢዉ ኖሬ ስላላስተዋልኩ።
ብዙ ስዎች የሃይማኖት ድርጅቶች የማይመከሩ ናቸዉ የሚል ኣስተሳሰብ ኣላቸዉ።
ካልተሳሳትኩ ባህል ከሁላቸዉም ይቀድማል። ትክክል ከሆነ ሁላቸዉም ባህል ላይ መገናኘት ይችላሉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።
በመጠኑም ቢሆን የማዉቃቸዉ የኦርቶዶክስ እና ፕሮቴስታንት ሃይማኖቶች ከመተያየት መወያየት ኣይችሉም? ጠበል ኣልቀምስም የሚሉ የሃይማኖት መሪዎች እና መስቀል ሳሚ የሃይማኖት መሪዎች የሚተያዩ ናቸዉ ወይስ የሚወያዩ?
ከወጣትነት እድሜዬ ጀምሮ የነበረ ክርክር ኣሁን በምያሳዝን ሁኔታ ኣንድን ቤተሰብ ለሁለት ከፍሎ እንዲተያዩ ኣድርጓል።
ከኣመታት በፊት ኣንድ በስም እንጂ በኣካል የማላዉቀዉ ሰዉ ህብረተሰብ በሰበካ ዉስጥ ማለፍ ኣለበት የሚል ሀሳብ ጻፈልኝ። የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ፓስተር ነዉ ሲባል ኣንበቤ ነበር። ያኔ የነበረዉን የፖለቲካ አመለካከት ባልጋራም ኣላማዬ ነዉ ብሎ መታገሉን ኣከብራለሁ። በተለያየ የፖለቲካ ኣስተሳሰባችን ምክንያት ቃልቻ ቃሉን ቅኝ ገዝቷል ልያስብለኝ የሞከረ ነዉ። ዛሬም ያን ኣስተሳሰብ ይኑረዉ ኣይኑረዉ ኣላዉቅም።
ሳያስበዉ ህብረተሰብ በሰባካ ዉስጥ ማለፍ ኣለበት ያለዉን ገና ሳነበዉ ነዉ ያስደነገጠኝ። ሳያስበዉ መሆኑ ርእሱ ስለዛ ስላልነበር ነዉ።
እንደዛ ኣይነት ኣስተሳሰብ ብያስደነግጠኝም ኣልገረመኝም። ብቸኛ እንዳልሆነ ስለምገምት። አስተሳሰቡን ገና ለመጀመርያ ጊዜ ሳነብ ሀሳቡ እሱን ማሳመኑን ሳይሆን ማን እንደዛ እንዳሳመነዉ ማወቅ ነዉ የፈለኩኝ። መልስ ለማግኘት እያሰብኩ ሰነበትኩ።
የመለስኩለት ኣጭር መልስ ሊጣጣሙ የማይችሉ ልዩነቶች (እሪኮንሳለብል ድፍረንስ) እንደለን ነዉ። በተጨማሪም ስለ ኣዉሮፓ የጭለማ ዘመን (ዳርክ ኤጅ) እንድያስተዉል እና በዛን ጊዜ ኣዉሮፓ ዉስጥ ምን ኣይነት እድገቶች እንደታዩ እንድያጠና ያስተዋልኩትን ኣካፈልኩት። ከዛ በሁዋል መልስ ማግኘነቴን ኣላስታዉስም።
ህብረተሰብን በሰባካ ዉስጥ ማለፍ ኣለበት ማለት ህብረተሰቡን ወደ ጭለማ እየመሩ በዛ ዉስጥ እለፉ እንደማለት ሆኖ ነዉ የሚታየኝ። ለዚህ ነዉ እንደዛ ኣይነትን ምክር ከማን ሰምቶ እንዳመነ ለማወቅ የምፈልገዉ። ለሰዉ ልጅ ከኣእምሮ ባርነት በላይ ያለ በሽታ ያለ ኣይመስለኝም።
የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ኢትዮጵያ ዉስጥ በሰፊዉ የገባዉ እና የተስፋፋዉ ከኣድዋ ድል በሁዋላ ይመስለኛል። የሁለቱ ክስተቶች መጣመር መኖር እና ኣለመኖር ዛሬ ባይታወቅም ታሪክ የሚፈታዉ ይመስለኛል።
የዛሬ ሃይማኖት መሪዎች እያስተዋሉ ለመምራት ሊመከሩ ያማይችሉ ናቸዉ? በኣንድ በኩል ፁሙ ኣትብሉ ይላሉ። በሌላ በኩል ፁሙ ኣትጠጡ ይላሉ። መጥናችሁ ብሉ፣ መጥናችሁ ጠጡ ብለዉ ማስተማር ኣይችሉም?
ባህል ዉስጥ ይህን እያየሁ እና እየሰማሁ ነዉ ያደኩኝ። የገብስ ጠላ የሚጠመቅበት እና የገብስ አረቄ የሚወጣበት ቤት ነዉ ያደኩኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ ነዉ ስቀምሳቸዉ የኖርኩኝ። ኣንድም ቀን የቤተሰብ አባል ሰክሮ የታወቀበት ኣላስታዉስም። በወጣትነት አረቄ የጠመቁት ዛሬ የማይቀምሱ ኣሉ።
የአረቄ አወጣጥ እና የጨርቅ አሰራር እዉቀቶች ማን እንደጀመራቸዉ ባላዉቅም በልጅነቴ ኣይቻቻዉ ያደነቅኳቸዉ ናቸዉ። ስለዚህ ከባህል ራቁ ማለት ከእንደነዚህም ፈጠራዎች ራቁ እንደማለት ሆኖ ይታየኛል።
የተደራጁ ሃይማኖቶች ጠቃሚም ጎጂም ናቸዉ። በእኔ ኣስተሳሰብ ቀድሞ የተደራጀዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ወደ ባህል የበለጠ ቀረቤታ ያለዉ ይመስለኛል። የጥምቀት ቀን ታቦት ካደረበት ወንዝ አካባቢ ወደ ቤተ ክርስትያን ከገባ በሁዋላ የፈረስ ጉግስ ይጦፋል። ስለዚህ ሃይማኖት የት ቆሞ ባህል የት እንደሚጀምር መለየት ራሱ ኣስቸጋሪ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።
እንደገባኝ ከሆነ ኣዉሮፓ ዉስጥ ሬይነሳንስ የተጀመረዉ ከሃይማኖት ጎጂ ጎን በመላቀቅ ባህልን ኣጥንቶ ማሳደግ ነበር። ከዛ በሁዋላ ነዉ ሳይንስ የተስፋፋዉ።
ያንን ታሪክ በጥልቀት ሳላጠና ነዉ በአከባቢያችን ከባህል የመራቅን ሰበካ ኣስተዉዬ ስለኢትዮጵያ ባህል ሁለገብ ህዳሴ ሀሳብ ማንሳት የጀመርኩኝ። አዉሮፓም ሆነ ኢትዮጵያ የነባር ሃይማኖት ድርጅቶች ደካማ ጎን ማህበረሰቦችን ባራሳቸዉ ቋንቋ ማስተማር ጀምረዉ ኣለማስፋፋታቸዉ ነዉ።
የኢትዮጵያ ባህል እና ህዳሴ መነጣጠል የማችሉ ናቸዉ። የሁለቱም ህዳሴዎች ተመሳሳይነት እያደር እየጎላ የመጣ ይመስለኛል። ቀድሞዉኑ ከባህል ያልራቁት ግስጋሴ ላይ ነን ማለትም ይችሉ ይሆናል።