Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37236
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

((VERY FISHY)):Why Give A Defeated Terrorist 30 Days 2 Disarm?Should've Been"Unconditional Disarmament"!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 02 Nov 2022, 20:23

Natnael Mekonnen

ሰበር መረጃ ከፕሪቶሪያ
በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የሰላም ውይይት የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም እና ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንዲፈታ ስምምነት ላይ ተደረሰ
በደቡብ አፍሪካ ለስምንት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የሰላም ድርድር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት እና ዘላቂ ሰላም በሚያረጋግጥ መልኩ በስምምነት መቋጨቱን ከውስጥ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ለሁለት አመታት የዘለቀው የሰሜኑ ጦርነት መቋጫ እንደሚሆን የተገመተ የሰላም ስምንነት ፊርማ በዛሬው እለት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በኢትዮጵያና በህወሓት ተደራዳሪዎች መፈረሙን ያስታወቁት ምንጮች ፤ ውይይቱ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ባስጠበቀ፣ የሕግ የበላይነትን ባረጋገጠ እና ለውጭ ጣልቃ ገብነት እድል በማይሰጥ መልኩ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል።
ቁልፍ የስምምነት አጀንዳዎች፦
1. ህወሓት ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱን፦ በስምምነቱ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንደሚፈታ፤ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በ24 ሰዓት ውስጥ አመቺ ቦታ መርጠው ንግግር ያደርጋሉ፤
2. ስምምነቱ በተፈረመ አምስት ቀናት ውስጥ የሁለቱ ወገን ወታደራዊ አመራሮች የትጥቅ ማስፈታት ሂደቱ የሚመራበትን ዝርዝር አፈጻጻም በጋራ በማውጣት ተግባራዊ ሥራዎችን መሥራት ይጀምራሉ፤
3. የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በተገናኙ አስር ቀናት ውስጥ ህወሓት ያሉትን ሁሉንም የቡድን እና ከባድ መሣሪያዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያስረክባል፤
4. ስምምነቱ በተፈረመ ሰባት ቀናት ውስጥ የፌደራል መንግሥት መቀሌን ተረክቦ በከተማው ውስጥ እና ዙሪያ ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያ ያስፈታል፤
5. በአጭር ቀናት ውስጥ አሁን ያለው የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር ይቋቋማል። በሚዋቀረው ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥም የትግራይን ሕዝብ የሚወክል አካል ይሳተፋል፤
6. የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጎረቤት ሀገራት የሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎችን ደኅንነትና ሰላም የሚያረጋግጥ ስምሪት የሚያደርግ ይሆናል። መከላከያ ሠራዊቱ በማንኛውም የትግራይ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ሕግ የማስከበር ስልጣኑን ከህወሓት ሙሉ በሙሉ ይቀበላል። ህወሓት ለተግበራዊነቱ ምንም አይነት እንቅፋት እንደማይፈጥር ተስማምቷል።
7. የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የማኅበራዊ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ ሁኔታዎች ያመቻቻል፤ ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፤
8. ህወሓት ያለ ፌደራል መንግሥት እውቅና ከማንኛውም የውጭ አካል ጋር ግንኙነት ማድረግ ያቆማል። እንዲህ አይነት ተግባር የሚፈጹ ግለሰቦች ካሉ በሀገሪቱ ሕግ የሚጠየቁ ይሆናል።