Page 1 of 1

አብን የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ አማራጭ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍ አስታወቀ። በሰላም ንግግር ሕገ-መንግሥታዊ መርሆች መጠበቅ እንዳለባቸውም አብን ጠቁሟል። EBC

Posted: 01 Nov 2022, 19:55
by sarcasm
አብን የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ አማራጭ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍ አስታወቀ። በሰላም ንግግር ሕገ-መንግሥታዊ መርሆች መጠበቅ እንዳለባቸውም አብን ጠቁሟል።

አብን የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ አማራጭ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍ አስታወቀ
*************************

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ አማራጭ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍ አስታወቀ።
ፓርቲው በወቅታዊ ጉዳይ በሰጠው መግለጫ፣ ከአሸባሪው ህወሓት ሥሪት እና ባህሪ አንፃር ቡድኑ ሰላምን አማራጭ እንደማያደርግ ገልጿል።
ቡድኑ ለዓመታት በጭቆና ሥራዓት እና ሕዝብን በጠላትነት ጭምር በመፈረጅ ሲንቀሳቀስ የነበረ መሆኑን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ መልካሙ ሹምዬ ተናግረዋል።

በ3 ዙር ባደረገው ወረራ በአማራ እና አፋር ክልሎች ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ያስከተለው አሸባሪው ህወሓት፣ ለዳግም 4ኛ ዙር ወረራ ጊዜ መግዣ እና የእፎይታ ጊዜ እየፈለገ እንደሆነም ገልጸዋል።

አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት እና ተቋማት አሸባሪው ህወሓት እንዲያገግም ፍላጎታቸውን እና ድጋፋቸውን በአደባባይ እያሳዩ መሆኑን በመግለጫው ተነሥቷል።

በደቡብ አፍሪካ እየተደረገ ባለው በሰላም ንግግር ሕገ-መንግሥታዊ መርሆች መጠበቅ እንዳለባቸውም አብን ጠቁሟል።
በአማራ እና አፋር የወደሙ ተቋማትን መልሶ ከመገንባት አንፃር ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባም የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ አንሥተዋል።

በሙሉ ግርማይ
Please wait, video is loading...

Re: አብን የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ አማራጭ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍ አስታወቀ። በሰላም ንግግር ሕገ-መንግሥታዊ መርሆች መጠበቅ እንዳለባቸውም አብን ጠቁሟል። EBC

Posted: 01 Nov 2022, 20:02
by ethiopian
Nobody will save you - we crashed your back bone !!! Oromara fuccked you up BIG time

Dr. Peace

Re: አብን የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ አማራጭ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍ አስታወቀ። በሰላም ንግግር ሕገ-መንግሥታዊ መርሆች መጠበቅ እንዳለባቸውም አብን ጠቁሟል። EBC

Posted: 02 Nov 2022, 11:16
by Abere
sarcasm,

የአብንን ማህተም የሰረቀ ሰው ነው ይባላል እንደዚህ አይነት መግለጫ የሚሰጠው። This is the job of a hacker. የአብን ህጋዊ እና ኦፊሴላዊ የአቋም መግለጫ አይደለም። አብን ሙሉ በሙሉ የአማራ ወኪሎች ማለት እነ ጀኔራል ተፈራ ማሞን የተመረጡበትን የአማራ ወኪል እንጅ ሌላ አያውቅም - አልተቀበለምም። ይህ የተለጠፈው በብልጽግና በኩል ነው። You are busy try treating the symptom, not the cause. The TPLF's constitution is a null and void thing for the Amhara people - the demographic majority of the country. It is technically null and void. You must find somewhere to sell this cheap trick.